ዒባዳ ላይ ፅና ወደ ኋላ አትሽሽ
በፆም አሳምረህ ሲወጣ አታበላሽ
ረመዳን ሲወጣ ከጌታው የሚሸሽ
ምንኛ ሞኝ ነው የሰራውን አፍራሽ
የረመዳን ዓቢድ በፆም ብቻ ሰጋጅ
መስጂድ አጨናንቆ ሲወጣ ተወጋጅ
ረመዳን ሲወጣ ወደ ወንጀል ነጓጅ
መሆኑን አውጇል የእስረኛው ወዳጅ
እባክህ ወንድሜ ጌታን ሁሌ አምልክ
በሰላትህ ዘውትር ትሆናለህ ብሩክ
ከሸይጣን ወጥመድ ራቅ ለሱ አትንበርከክ
ዓላማህ ላይ ፅና እውነት ወንድ ከሆንክ
እህቴዋም ፅኚ በጌታሽ መንገድ ላይ
በሰላት በሂጃብ አትሁኝ ወላዋይ
ወንድን ምታሳስት አትሁኝ አማላይ
ራስሽንም ጠብቂ ከፋጂር አታላይ
እንዴት ያምር ነበር ረመዳን ነሻጣው
ፆሙ ተራዊሁ ድባቡ ሞቅታው
ቲላወቱል ቁርአን ብዛቱ የኺትማው
ተሰናብቶን ሄደ ሁሉም ተወጋጅ ነው
ቀድሞም ተነግሮናል ቶሎ እንደሚሄድ
አያመል መዕዱዳት ፈጥኖ ሚገባደድ
ለነገ ቤታችን በቂ ስንቅ ሳንሰንቅ ባግባቡም ሳንነግድ
ገባ ሲባል ወጣ እየተቻኮለ እያየን ሲነጉድ
ግን ተሰፋ አልጨለመም በረመዳን መውጣት
ሀጅም ተከትሏል ፆም በሄደ ማግስት
ሰላት ሁሌም አለ በቀንም በሌሊት
ሱና ፆምም አለ ዚክርም ማታ ጠዋት
በዒባዳ ፅና አታቁም ስራህን
ረሱልን ተከተል አታምፅ ወዳጅህን
በሱና ፆም በርታ አታቁም ሰላትክን
ፅናት እንዲሰጥህ ተማፀን ጌታህን
በፆም አሳምረህ ሲወጣ አታበላሽ
ረመዳን ሲወጣ ከጌታው የሚሸሽ
ምንኛ ሞኝ ነው የሰራውን አፍራሽ
የረመዳን ዓቢድ በፆም ብቻ ሰጋጅ
መስጂድ አጨናንቆ ሲወጣ ተወጋጅ
ረመዳን ሲወጣ ወደ ወንጀል ነጓጅ
መሆኑን አውጇል የእስረኛው ወዳጅ
እባክህ ወንድሜ ጌታን ሁሌ አምልክ
በሰላትህ ዘውትር ትሆናለህ ብሩክ
ከሸይጣን ወጥመድ ራቅ ለሱ አትንበርከክ
ዓላማህ ላይ ፅና እውነት ወንድ ከሆንክ
እህቴዋም ፅኚ በጌታሽ መንገድ ላይ
በሰላት በሂጃብ አትሁኝ ወላዋይ
ወንድን ምታሳስት አትሁኝ አማላይ
ራስሽንም ጠብቂ ከፋጂር አታላይ
እንዴት ያምር ነበር ረመዳን ነሻጣው
ፆሙ ተራዊሁ ድባቡ ሞቅታው
ቲላወቱል ቁርአን ብዛቱ የኺትማው
ተሰናብቶን ሄደ ሁሉም ተወጋጅ ነው
ቀድሞም ተነግሮናል ቶሎ እንደሚሄድ
አያመል መዕዱዳት ፈጥኖ ሚገባደድ
ለነገ ቤታችን በቂ ስንቅ ሳንሰንቅ ባግባቡም ሳንነግድ
ገባ ሲባል ወጣ እየተቻኮለ እያየን ሲነጉድ
ግን ተሰፋ አልጨለመም በረመዳን መውጣት
ሀጅም ተከትሏል ፆም በሄደ ማግስት
ሰላት ሁሌም አለ በቀንም በሌሊት
ሱና ፆምም አለ ዚክርም ማታ ጠዋት
በዒባዳ ፅና አታቁም ስራህን
ረሱልን ተከተል አታምፅ ወዳጅህን
በሱና ፆም በርታ አታቁም ሰላትክን
ፅናት እንዲሰጥህ ተማፀን ጌታህን