Ministry of Education Ethiopia dan repost
የ2013 የትምህርት ዘመንን ታሳቢ ያደረገ የኮርስ ክለሳ እየተደረገ ነው:- ትምህርት ሚኒስቴር
--------------------------------------------
ትምህርት ሚኒስቴር ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር እያደረገው ባለው ውይይት የቀጣይ አመት ላይ የኮርስ ክለሳ እንደሚያደርግ አስታውቋል።
ትምህርት ሚኒስቴር በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠውን ትምህርት ለማስጀመር የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ፡፡
የ2013 ትምህርት ዘመን ትምህርት የሚሰጥበት ጊዜ አጭር ስለሆነ ተማሪዎች መማር የሚገባቸውን ታሳቢ ያደረገ የኮርስ ክለሳ እየተሰራ ሲሆን በአጭር ጊዜም ወደ ክልሎች ይላካል ተብሏል፡፡
ትምህርት ቤቶች ትምህርት ሲጀምሩ የ2013 ትምህርት ምዕራፍን ከመጀመራቸው በፊት በ2012 የትምህርት ዘመን ያልተሸፈኑ ዋና ዋና ጉዳዮች በመከለስ እንደሚሆን ተገልጿል ፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ትምህርት ቤቶች የኮሮና ቫይረስ በመከላከል ትምህርት መጀመር እንዲችሉ የትምህርት ቤቶችን ዝግጁነት የሚያረጋግጥ አደረጃጀቶችን ፈጥሮ እየሰራ ይገኛል፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተዘግተው የነበሩ ትምህርት ቤቶችን በ3 ዙር ዳግም ለመክፈት የሚያስችል ምክረ ሃሳብ ማቅረቡ ይታወቃል፡፡