በሚኒስቴር መ/ቤቱ፣በዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ እና በኦሎምፒክ ኮሚቴ አባላት ላይ ክስ ተመሠረተ!
በሀገሪቱ ተመዝግበው የሚገኙ ብሄራዊ ፌዴሬሽኖችና የታዋቂ አትሌቶች ህጋዊ ወኪል ጠበቆች በቀን 6/12/16 እና በ15/12/16 ዓ.ም ለኢ.ፊ.ድ.ሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የቅሬታ አቤቱታ ማቅረባቸው ይታወሳል።
የብሄራዊ ፌዴሬሽኖችና የታዋቂ አትሌቶች ህጋዊ ወኪል ጠበቆች ከላይ በተገለፀው መሠረት ከህግና ስርዓት ውጪ በሆነ መንገድ በተፈፀሙ ተግባራት ላይ ተገቢው አስተዳደራዊ እና ህጋዊ እርምጃ በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ሥ/አ ቦርድ አባላትና በፕሬዝዳንቱ ዶ/ር አሸብር ላይ እንዲወሠድ በማለት ከአንድም ሁለት ጊዜ የህግ ሂደቱን በጠበቀ መልኩ የቅሬታ አቤቱታ በማቅረብና የአምስት ቀናት ቀነ-ገደብ ቢያስቀምጡም ጥያቄ የቀረበለት ሚኒስቴር መ/ቤቱ ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት ምላሽ ሳይሠጥ ቆይታል።
እንደ ሀትሪክ ታማኝ የመረጃ ምንጮች ከሆነ በሶስት የህግ ባለሙያተኞች ማለትም የህግ አማካሪና በማናቸውም ፍ/ቤት ጠበቃ አቶ ጳውሎስ ተሠማ ኢላላ፣የህግ አማካሪና ጠበቃ አቶ ኃይሉ ሞላ ደምሴ እና በማናቸውም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ጠበቃና የሕግ አማካሪ አያሌው ቢታኔ መንዛ አማካይነት ለኢ.ፊ.ድ.ሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የቅሬታ አቤቱታ አቅርበው ካስቀመጡት የአምስት ቀናት የጊዜ ቀነ ገደብ በላይ ተጨማሪ ጊዜን ጨምረው በመስጠት ተስፋ ሳይቆርጡ ምላሽ ለማግኘት ቢጠባበቁም ሚኒስቴር መ/ቤቱ ለቀረበለት ህጋዊ ጥያቄ ምላሽ ሳይሠጥ ዝምታን መርጦ መቆየትን መርጧል።
via ሀትሪክ ስፖርት
𝗦𝗵𝗮𝗿𝗲 ➢
@Sky_Sports2𝗦𝗵𝗮𝗿𝗲 ➢
@Sky_Sports2