SOA Molla Maru


Kanal geosi va tili: ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa: ko‘rsatilmagan



Kanal geosi va tili
ko‘rsatilmagan, ko‘rsatilmagan
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


“ከስክሪን ቀንሰን – መጽሐፍት እንግለጥ!”
ከተማ አቀፍ የንባብ ፌስቲቫል ሳምንት
ከነሐሴ 21-25/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ

ንባብ የእውቀት በር፣ የምናብ መስኮትና የትውልድ ግንባታ መሠረት ነው። በዲጂታል ዘመን የስክሪን አጠቃቀም የዕለት ተዕለት ሕይወታችን አካል እየሆነ በመጣበት ወቅት፣ መጽሐፍ ለማንበብ የሚኖረንን ጊዜና ትኩረት እንደገና ማስመለስ የጋራ ኃላፊነት አለብን።
በዚህ መሠረት “ከስክሪን ቀንሰን – መጽሐፍት እንግለጥ!” በሚል መሪ ቃል የሚከበረው የከተማ አቀፍ የንባብ ፌስቲቫል ሳምንት፣ የንባብ ባህልን ለማስፋፋት፣ መጽሐፍ አንባቢዎችን ለማበረታታትና በተለይም በሕፃናትና በወጣቶች ዘንድ የንባብ ፍላጎትን ለማዳበር የተዘጋጀ የንባብ ንቅናቄ ሳምንት ነው።

የፌስቲቫሉ መሪ ቃል “ከስክሪን ቀንሰን – መጽሐፍት እንግለጥ!” ቴክኖሎጂን መቃወም ሳይሆን የስክሪን አጠቃቀማችንን ሚዛናዊ በማድረግ ለንባብ፣ ለማሰብ፣ ለመወያየት እና ለመማር የሚያስፈልገንን ጊዜ እንድናስተካክል የቀረበ ጥሪ ነው።
አንድ ሰዓት ከስክሪን ቀንሰን አንድ ምዕራፍ ከመጽሐፍ ማንበብ፣ ከልጆቻችን ጋር መጽሐፍ ማንበብ፣ መጽሐፍ በስጦታም ሆነ በትውስት መለዋወጥና ባነበብነው ላይ መወያየት ትንሽ ተግባር ቢመስልም ትልቅ የትውልድ ግንባታ መሰረት ነው።

ውድ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፣ ደራሲያን፣ አሳታሚዎች፣ ወጣቶች፣ መምህራን… የንባብ ሳምንቱ ከነሀሴ 21-25/2018 በከተማችን በሚገኙ 72 ቤተመጽሐፍት በሁሉም የሚካሄድ በመሆኑ በየአካባቢያችሁ በሚገኙ ቤተመጽሐፍት በመገኘት በንባብ ባህል ግንባታ የራሳችሁን ሚና እንድትወጡ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ይህ ሳምንት የንባብ ሳምንት ብቻ ሳይሆን፣ የንባብ ልማድን የምንጀምርበት ሳምንት እናድርገው!

“ስክሪንን በሚዛን፣ መጽሐፍን በፍቅር እናብብ!
ትውልዳችንን እናንቃ!”
Via Hirut Kassaw


SOA dan repost


https://www.facebook.com/share/r/1HmLTw2Npm/
ቅዳሜ ጠዋት ልጆቻችሁን አብረሆት ቤተመፃህፍት ውሰዱ


በ2019 የትምህርት ዘመን 9 የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን ተቀብለው ለማስተማር ዝግጅት ማጠናቀቃቸው ተገለጸ፤

ወላጆች ልጆቻቸውን በልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በማስተማር የእድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል።

--------------------------- // --------------------------

(ነሐሴ 2018 ዓ.ም) በ2019 የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ተቀብለው ለማስተማር 9 የፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸው ተገለጸ። የትምህርት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሕይወት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በ2019 የትምህርት ዘመን አዲስ ትምህርት የሚጀምርባቸውን ትምህርት ቤቶች ጨምሮ በ9 የፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ትምህርት እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

በትምህርት ሚኒስቴር የሚተዳደሩት እነዚህ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ብቃት ያላቸው፣ ተወዳዳሪ የሆኑ፣ ሥነ-ምግባርን የተላበሱ እንዲሁም ለሀገር የሚበቁ የወደፊት መሪዎችን ለማፍራት የሚያግዙ ተቋማት መሆናቸውን ፕሮፌሰር ክንደያ አስገንዝበዋል።

ከመደበኛ ትምህርት ቤቶች በተለየ መልኩ በልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶቹ የተግባርና የክህሎት ትምህርት ላይ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥም ተገልጿል። ይህም ተማሪዎች የተለያዩ ክህሎቶችን እንዲያዳብሩ፣ ቴክኖሎጂን በተግባር እንዲጠቀሙና ለወደፊት የሥራና የትምህርት ዓለም ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያግዛል።

በተጨማሪም፣ ከቻይና መንግሥት ጋር በተደረገው የትብብር ስምምነት መሠረት ከሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ጀምሮ የቻይንኛ ቋንቋ በእነዚህ ትምህርት ቤቶች እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት እንደሚሰጥ ፕሮፌሰር ክንደያ ገልጸዋል።

በመሆኑም ወላጆች፣ መምህራንና የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ተማሪዎች ይህንን አንደ ዋና የትምህርት እድል አድርገው እንዲጠቀሙበት የማበረታታትና የማስተባበር ሥራ እንዲያከናውኑ ፕሮፌሰር ክንደያ ጥሪ አቅርበዋል።

የትምህርት ፕሮግራሞች ጥራት ማሻሻል መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ዮሐንስ ወጋሶ በበኩላቸው የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ባለፉት 5 ዓመታት በትምህርት ዘርፉ ከተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎች አንዱ መሆኑን ጠቁመዋል።

ባለፈው ዓመት ሥራ በጀመሩ 5 የልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ 1,250 የተሻለ ችሎታ ያላቸው ተማሪዎች የትምህርት እድሉ ተጠቃሚ መሆናቸውንም ዶ/ር ዮሐንስ ገልጸዋል።

በ2019 የትምህርት ዘመን አዲስ ትምህርት በሚጀምርባቸውና ባለፈው ዓመት ትምህርት በተጀመሩባቸው ትምህርት ቤቶች የ9ኛና 10ኛ ክፍል ተማሪዎች ምዝገባ እየተከናወነ ሲሆን፣ ተማሪዎች ካሉበት ቦታ ሆነው በበይነ መረብ መመዝገብ እንደሚችሉም ዶ/ር ዮሐንስ አብራርተዋል።

የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በመላ ሀገሪቱ በስፋት እንዲዳረሱ ትምህርት ሚኒስቴር በሁሉም ክልሎች 13 ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑም በመግለጫው ተመላክቷል።

ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
ዩቱዩብ- https://www.youtube.com/@ministry-of-education-ethiopia
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et ይከታተሉ
See less










SOA COMMUNITY GEjA 2 CAMPUS dan repost
ዛሬ የክረምት ተማሪዎች -በአራት ኪሎ
ዩኒቨርስቲ ,taxidermy studio





11 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.