" ሂክመት አየችኝ አላየችኝ ብዬ መደንገጤ ልክ ነዉ??"
"ስለሷ ያለቅጥ ማሰቤስ??"
"ቀና ብላ እንኳን ያላየችኝን ልጅ ስለምን ማሰብ እና መከተል ፈለግኩ?"
"እልህ ነዉ ወይስ..."....ላዉንጅ ዉስጥ ቁጭ ብዬ ሳመላልሳቸዉ የነበሩት ሃሳቦች ናቸዉ። የሴቶች ጋጋታ የማያስደነግጠኝ ሰልማን ዛሬ ግን ስለ አንዲት ተከናናቢ ኮተታም እያሰብኩ ነዉ፣ መጥፎ ሁኔታ ዉስጥ አየችኝ ብዬ እየተጨነቅኩ ነዉ። በቆምኩበት ገትራኝ ስለሄደች የያዘኝ እልህ ወይስ እንደ ሌሎች ሴቶች ስላልተለማመጠችኝ ነዉ የማስባት? ወይንስ ከኮተቷ ጀርባ ደምቆ የሚታየዉ ዉበቷ ገዝቶኝ? አወጣለሁ አወርዳለሁ-መልስ ግን የለም። እኔ በሀሳብ በሰመጥኩበት ሰዓት ሳላስተዉለዉ ከፊቴ የተቀመጠዉ ሻይ መቀዝቀዙን ልብ ያልኩት ከሃሳብ ቀዘፋዬ ስልኬ ሲቀሰቅሰኝ ነበር-አቤል ደዉሎ።
*
>
>
> ወደ ቤት ለመሄድ በተሳፈርኩበት ታክሲ ከፊት ለፊቴ ተቀምጠዉ አባት እና ልጅ እየተከራከሩ ነበር። አባትየዉ ልጁን ለማሳደግ እና ለማኖር እድሜ ልኩን ተጎሳቁሎ ኑሮ ለራሱ እንደማያስብ እና ዉበቱ በልጁ ፊት ላይ እንደሆነ ነበር ያስተማሩኝ። ምነዉ የኔ አባት በህይወት ኖሮ ለአለም እንደማላፍርበት በተናገርኩ፣ በተናዘዝኩ-ግን አይሆንም ከንቱ ምኞት!
ቀኑ ሲመሻሽ ዛሬም በጊዜ ወደ ቤት ገባሁ። ሰሞኑን ጓደኛም ሆነ ጨዋታ አስጠልቶኛል-ስበር እየመጣሁ ወደ እናቴ ጉያ መሸጎጥ ሆኗል ስራዬ።
>
>
>
>
>
> የኔ አለም፣ የኔ እናት እኮ እልል ያለች አራዳ ናት...ሳቅ ማምረት ትችልበታለች፣ መቀለድን እሷ ካልቀለደችዉ ቀልድ አይመስለኝም-የኔ ሳቅ!!