ዓለም ዓቀፍ የጉንፋን ሳምንት!
°°°°°°°°°°\\°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
ሰሞኑን ጉንፋን ይዞኛልና አፍንጫዬ ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጭ ሆኗል። ጉንፋኑ አለም አቀፍ ሰርተፊኬት ያለው ነው፤ ማለቴ፦ በቃ International ገነር ነው። እኔ ከአንዳንድ ምሽቶች በቀር(በእንቅልፍ ጊዜዬ ብዙ ጊዜ በህልሜ ራሴን ሌላ አገር ስለማገኝ🤔) ላለፉት ሦስት አሥርት አመታት የኖርኩት እዚሁ ኢትዮጵያ ሲሆን እንደዚህ አይነት ጉንፋን አይቼ አላውቅም(ወደ ፊትም አላይም! ጦሴን!) በቃ ምን አለፋችሁ! እኛ ቤት ሳምንቱ ዓለም ዓቀፍ የጉንፋን ሳምንት ነው የሚመስለው።
ቅሽር ሻይ፣ የካልዲስ Special ሻይ፣ መረቅ፣ ሎሚ ሻይና ሌሎችም በሻይ ስም የሚንቀሳቀሱ ትኩስ ነገሮች ጠጥቼበታለሁ፤ ምግብማ ለዋንጫ ነው 'ምበላው(በዚሁ አጋጣሚ ለሚስቴ ክብር ላስገባ🙏)። ግን "ጉንፋን" የሚሉት አሸባሪ ግለሰብና ግብረ-አበሮቹ (Viruses) ንቅንቅ አላሉም።
ቆይ፦ እኔ ነኝ እንዴ ጉንፋኑን የያዝኩት? ብዬ ማሰብ ጀመርኩኝ። እኔ ደግሞ እንዲህ ሙጭጭ ማለት አላውቅም። ተሳስቼ ብይዘው እንኳን አሳዝኖኝ ቶሎ 'ምለቀው ነው የምመስለኝ፤ በአሳማኝ ምክንያት ይሁን እንጂ "ልቀቀኝ!" ያለኝን ሁሉ ስለቅ የኖርኩ ደግሞም በመልቀቅ የማምን ግለሰብ ነኝና።
ለማንኛውም ግን ንግግሬን በጉንፋን ጀምሬ በጉንፋን ጠቅልዬ "ምነው ዛሬ ደግሞ ጉንፋናም ጽሁፍ ጻፍክ?" እንድትሉኝ በር አልከፍትላችሁም። አስተውሎት የሚሻ መልእክት አለኝ፦ ይኸውም👇 ስለ ስሜት ሕዋሳት እግዚአብሔር ይክበር፤ ይመስገን።
እኔ ያለሁበት ሁኔታ በተለይ ስለ ማሽተት የበለጠ እንዳስብ አድርጎኛል። ለካ አፍንጫ ስላለን ብቻ አናሸትም! ደስ የሚል ሰልካካ አፍንጫ ያለህ መሆኑ የማሽተት ዋስትና አያረጋግጥልህም፤ የምታሸተው ቆንጆ አፍንጫ ሲኖርህ ብቻ ሳይሆን ደህንነቱ የተጠበቀ አፍንጫ ሲኖርህም ነውና።
ዙሩን 'ሳከረው፦ ስለ ህመም ስሜት ራሱ እግዚአብሔር ይመስገን። የህመም ስሜት የሚሰማን ሕያዋን መሆናችን ሲረጋገጥና systeማችን active ሲሆን አይደል? አንድ ሰው በስጋ ደዌ ህመም ሲጠቃ ስሜት-አልባ ስለሚሆን አይኑ እያየ የገዛ ሥጋው ቢቆረጥ ምንም የህመም ስሜት አይሰማውም ይባላል። ታዲያ ስለ ህመም ስሜት ፍጥረት ዑደቱን ጠብቆ ለዓላማው እንዲሠራ የሚያስችል (the sustainer of the creature) እግዚአብሔር ሊመሰገን አይገባም?
በመጨረሻም፦ ዛሬ ላይ በሕይወት ስለ መኖራችን ስሙ ይግነን፤ ጤነኞች ሆነን ሰው የሚያሰኘንንና በምድር የቆየንለትን ተልዕኮ ለመወጣት በሕይወት መኖር ይቀድማልና። ጽሁፌን በሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን አባባል ስቋጭ፦ "አንተ ሲያምህ ከተሰማህ በሕይወት አለህ ማለት ነው፤ ሌሎች ሲታመሙ ከተሰማህ ግን በትክክል ሰው ነህ ማለት ነው።"
ለሃሳብ አስተያየትዎ፦
@ogkings123 Join 👇& Share>
@ogmixed @ogmixed