📢 " አዲሱ ስርዓተ ትምህርት አንድ ተማሪ 3 ቋንቋዎችን እንዲናገር የሚያስችል ነው" - ትምህርት ሚኒስቴር
ከትምህርት ሚኒስቴር ዓበይት የሪፎርም ትኩረቶች አንዱ የስርዓተ ትምህርት ሪፎርም ነው።
አዲሱ ስርዓተ ትምህርት አንድ ተማሪ 3 ቋንቋዎችን እንዲናገር የሚያስችል መሆኑን በሚኒስቴሩ የተፈጥሮ ሳይንስ ስርዓተ ትምህርት ዝግጅት ኃላፊ ዛፏ አብርሃ ለኢቢሲ ገልፀዋል።
ተማሪዎች በቅድመ አንደኛ ደረጃ በአፍ መፍቻ ቋንቋ፣ በአንደኛ ደረጃ ዓለም አቀፍ ቋንቋ ማለትም እንግሊዝኛ ከዚያም ከ3ኛ ክፍል በኋላ ሌላ የአጎራባች ክልል ቋንቋ እንደሚማሩ ኃላፊዋ አስረድተዋል።
የአጎራባች ክልል ቋንቋውም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሳይሆን በክልሎች የሚመረጥ እንደሆነም ነው የገለፁት።
በተጨማሪም ስርዓተ ትምህርቱ በሀገር በቀል ምሁራን ጥናት ላይ ተመስርቶ የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ በማገናዘብ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል።
በዚህም የግብረገብ እና የተግባር ትምህርት እንዲያካትት መደረጉን ነው የተናገሩት።
በሥርዓተ ትምህርቱ ችግሮች ዙሪያ ከመምህራን፣ ከወላጆች እና ከተማሪዎች የሚነሱ ሀሳቦችንም እንመለከታለን ነው ያሉት ኃላፊዋ።
የመጽሐፍ ስርጭትን በተመለከተም ያሉ የበጀት ችግሮችን በመቋቋም በአማካይ ያለውን ተደራሽነት ለመጨመር እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።
በዚህም 18 ሚሊዮን መጻሕፍት ጅቡቲ መድረሳቸውን ጠቁመዋል።
ለመጽሐፍ አቅርቦት እና ተደራሽነት ማነስ በጀት ዋነኛው ተግዳሮት መሆኑን ያነሱት ኃላፊዋ፤ ይህን ለመቅረፍ በተለይ ቴክኖሎጂ ተኮር አሰራርን ለማበጀት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
አክለውም፥ እንደ ሀገር ያጋጠመውን የትምህርት ስብራት ለመጠገን የሁሉም ርብርብ እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል።
በሌላ በኩል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጀመረው "ትምህርት ለትውልድ" ንቅናቄ ዘርፉን እንዳነቃቃው የገለፁት ደግሞ በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ፕሮግራም እና ጥራት ማሻሻል መሪ ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ዮሃንስ ወጋሶ ናቸው።
ከንቅናቄው ባሻገር የትምህርት ቤት ምገባ መርሀ ግብር፣ የመምህራን አቅም ግንባታ እና ሌሎችም የትምህርት ምህዳሩን ለመለወጥ የተሰሩ ስራዎች መኖራቸውን ስራ አስፈፃሚው ገልፀዋል።
ከትምህርት ጥራት አኳያም የተማሪዎች ላሉበት ክፍል ብቁ ያለመሆን ችግር መኖሩን ያነሱት አቶ ዮሃንስ፤ ያንን ለመፍታት ከታችኛው ክፍል ጀምሮ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
ለዚህም በዘርፉ 27 ቢሊዩን ብር በገንዘብ፣ በዓይነት እና በጉልበት ኢንቨስት እንደተደረገ ተናግረዋል።
በመጪው የትምህርት ዘመን በተለይ ዕድሜያቸው ደርሶ ወደ ትምህርት ቤት ያልመጡ ተማሪዎችን ለማካተት፤ በትምህርት ቤት ተገኝተው በአግባቡ ትምህርት ያልተሰጣቸውንም ለማገዝ ይሰራል ብለዋል።
በተጨማሪም ካለፉት ጊዜያት በመማር ደካማ የሆነ የትምህርት ዝግጁነት እና አሰጣጥን ለማሻሻል እንደሚሰራ አመላክተዋል።
ትምህርት ቤቶች የሚያዘጋጁት የትምህርት ንቅናቄ ሰነድም መምህራንን ማዘጋጀት፣ የትምህርት ቁሳቁስን ማሟላት እና ምቹ የትምህርት ከባቢን መፍጠር ላይ እንዲያተኩሩ እንደሚያስችላቸውም ነው የገለፁት።