«ለአንዲት ቅፅበት ብቻ»
(ደበበ ሰይፉ)
-
ለአንዲት ቅጽበት ብቻ
እስቲ የማነው ጉልበት
የሰው የአማልክት
ሊሰጠኝ የሚችል የደቂቃ ዕረፍት ?
ከእውነት - ፍቅር - ውበት እማወጋበት ?
ለአንዲት ውብ ሙዚቃ ሀሳቤን ሰውቼ
ለአንዲት መልካም ቅኔ ባርነት ገብቼ
ህሊናዬን፤ ቀልቤን፤ አካሌን ሰጥቼ፤
ለአንዲት ቅጽበት ብቻ !
የአምሮዬ መርከብ ከማዕበል አምልጣ
ከሕይወት ስንክሣር አምርራ ፈርጥጣ
በዕፁብ - ውበት ቅኝት እጅግ ተመስጣ
ሌላው ሌላው ነገር ባፍንጫዬ ይውጣ!!
.
የጥበብ አፍቃሪያን ብቻ ቤተሰብ ሁኑን
╔═══❖••❖═══╗
@yegtm_hywet
@yegtm_hywet
╚═══❖••❖═══ ╝
❥❥ ⚘ ❥❥
(ደበበ ሰይፉ)
-
ለአንዲት ቅጽበት ብቻ
እስቲ የማነው ጉልበት
የሰው የአማልክት
ሊሰጠኝ የሚችል የደቂቃ ዕረፍት ?
ከእውነት - ፍቅር - ውበት እማወጋበት ?
ለአንዲት ውብ ሙዚቃ ሀሳቤን ሰውቼ
ለአንዲት መልካም ቅኔ ባርነት ገብቼ
ህሊናዬን፤ ቀልቤን፤ አካሌን ሰጥቼ፤
ለአንዲት ቅጽበት ብቻ !
የአምሮዬ መርከብ ከማዕበል አምልጣ
ከሕይወት ስንክሣር አምርራ ፈርጥጣ
በዕፁብ - ውበት ቅኝት እጅግ ተመስጣ
ሌላው ሌላው ነገር ባፍንጫዬ ይውጣ!!
.
የጥበብ አፍቃሪያን ብቻ ቤተሰብ ሁኑን
╔═══❖••❖═══╗
@yegtm_hywet
@yegtm_hywet
╚═══❖••❖═══ ╝
❥❥ ⚘ ❥❥