"የናፈቀ ሰው ሃቅ"
...
ከህሊና አልጋየ
ናፍቆትሽን አባብሎ-ማስተኛት ይከብዳል፣
ምክኒያቱም
እንደ ዓመለኛ ልጅ
በሾሉ ጥፍሮቹ -ነፍስ ይጨመድዳል።
ናፍቆትሽ!
ትዝታሽ!
ገላየን ገረፈው-ልቤን አደቀቀኝ፣
ትላንት ላይ ሁኖ
ከህይወት ጓዳየ-ዛሬየን ሰረቀኝ።
እናም...
ገዘፍሽ፣
ፈረጠምሽ፣
በናፍቆትሽ በኩል-የቀን ግብር በልተሽ፣
ግን ማን ነኝ ?
ግን ማን ነሽ?
ግዛቷ ሰፊ ነው
ከነፍሴ ጫፍ አልፎ-ከየት እስከ የትም፣
እውነት ከተወራ
አሁን የኔን አንች-አንችም አታውቂያትም።
...
ዘነበ-ሞላ
╔═══❖••❖═══╗
@yegtm_hywet
@yegtm_hywet
╚═══❖••❖═══ ╝
❥❥ ⚘ ❥❥
...
ከህሊና አልጋየ
ናፍቆትሽን አባብሎ-ማስተኛት ይከብዳል፣
ምክኒያቱም
እንደ ዓመለኛ ልጅ
በሾሉ ጥፍሮቹ -ነፍስ ይጨመድዳል።
ናፍቆትሽ!
ትዝታሽ!
ገላየን ገረፈው-ልቤን አደቀቀኝ፣
ትላንት ላይ ሁኖ
ከህይወት ጓዳየ-ዛሬየን ሰረቀኝ።
እናም...
ገዘፍሽ፣
ፈረጠምሽ፣
በናፍቆትሽ በኩል-የቀን ግብር በልተሽ፣
ግን ማን ነኝ ?
ግን ማን ነሽ?
ግዛቷ ሰፊ ነው
ከነፍሴ ጫፍ አልፎ-ከየት እስከ የትም፣
እውነት ከተወራ
አሁን የኔን አንች-አንችም አታውቂያትም።
...
ዘነበ-ሞላ
╔═══❖••❖═══╗
@yegtm_hywet
@yegtm_hywet
╚═══❖••❖═══ ╝
❥❥ ⚘ ❥❥