💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
#ፆም
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነትና ትምህርት መሰረት ጾም የማህበርና የግል ተብሎ በሁለት ይከፈላል፡፡
ፆም ምንድ ነው?
#ጾም ማለት ሰው ምግብ ወይም ሰውነት ከሚፈለጋቸው ነገሮች መካከል መወሰን ማለት ነው፡፡ ጾም በጥንተ ፍጥረት አትብላ ተበሎ የህግ መጠበቅም ሆኖ ለሰው ልጅ ከተሰጠው ትዕዛዝ ጾም ከሃይማኖት ጋር የተያያዘ ስርአት ስለሆነ ሃይማኖት በለበት ሁሉ አለ፡፡ ጾም ለተውሰነ ጊዜ ከእህልና ውሀ መከልከል ብቻ ሳይሆን ለሰውነት የሚምረውን ለማየት እና ለመፈጸም የሚያስጎመጀውን ነገር ሁሉ መፈጸም ነው፡፡በተግባራዊ ትርጉም የተረዱና የተጠቀሙበት ሰዎች ጾምን ‹‹ለፀሎት እናቷ፣ ለእንባ መፍለቂያዋ ለበጎ ስራ ሁሉ መሰረት ›› በማለት ተርጉመውታል፡፡
#የፆም_አስፈላጊነት
ሃይማኖት መሰረት ነው ነገር ግን ቤት በመስራት ብቻ የተሟላ እንደማይሆን ሃይማኖትንም ፍጹም የሚያደርጉት በእርሱ መሰረትነት ነው የመሚታነጹ ስነ ምግባራት ናቸው፡፡ ጾም፣ ጸሎት ምጽዋት ስግደትን የመሰሉት ምግባራት ሃይማኖትን እንዲሰራ ያደርጉታል፡፡
ጾም የስጋን ምኞትን እናፈቃድን ለማስታገስ ይረዳል፡፡ መዝ 34፡13፣ ሮሜ 8፡12-14፣ 1ኛ ቆሮ 6፡12 ‹‹ ለሚጠፋ ምግብ አትስሩ ይልቅስ የሰው ልጅ ለሚሰጣቹህ የዘለዓለም ህይወት ለሚሆን ምግብ ስሩ›› ዮሐ 6፡7 . ጾም በአምሮት በምኞትና በስስት ጸባዮች ላይ የበላይነት ያስገኛል፡፡
#በፆም_የተጠቀሙ_ሰዎች
ሀ. #በብሉይ_ኪዳን
የሰማርያው ንጉስ አክአብ 1ኛ ነገ 20፡27
የእስራኤል ሰዎች 2ኛ ዜና 20፡1-23
በጉዞ ላይ የነበሩ ሰዎች እዝ 8፡21
የነነዌ ሰዎች ዮናስ 3፡3
ነብዩ ነሕምያ ነህ 1፡2
ሀማ በተነሳ ጊዜ አስቴር 3፡9 የመሳሰሉት፡
ለ. #በሐዲስ_ኪዳን
በሐዲስ ኪዳን ጾም የጀመረው ክርስቶስ ነው፡፡ ክርስቶስ ከጾም በኋላ 3 ነገሮችን ድል ነስቷል፡፡ 1. ስስት 2. ትእቢት 3. ፍቅረ ነዋይ
መላእክትም ቀርበው አገልግለውታል፡፡ መዝ 90፡11 ፣ ማቴ 4፡1 ፣ ሮሜ 14፡1-6
#የአዋጅና_የግል_ጾም
፩.#የአዋጅ_ጾም
በአባቶቻችን የተደነገጉ ሰባት አጽዋማት አሉ፡፡
፩ ዐብይ ጾም
፪.ጾመ ነብያት
፫.ሐዋርያት
፬.ፍልሰት
፭.ገሃድ
፮.ነነዌ
፯.ፆመ ድህነት
#ዐብይ_ጾም
ሙሴ በሲና ተራራ ህጉን ከማቅረቡ በፊት 40 ቀን 40 ሌሊት ጾሟል፡፡ ጌታም ወንጌል ከመስበኩ በፊት በገዳመ ቆሮንጦስ 40 ቀን 40 ሌሊት ጾሟል፡፡
. ይህ ጾም አብይ ወይም ሁዳዴ በመባል ይታወቃል፡፡ አብይ የሚሰኘው ዐብይ ነብያት የጾሙት በሐዲስ ኪዳንም ጌታም የኦሪተንና የነቢያትን ህግ ለመጠበቅና ለመፈጸም ሲል የጾመው በጾሙ ፍጻሜ ከሰይጣን የመጣውን ፈተና ድል የነሳበት በመሆኑ ነው፡፡
. በአብይ ጾም ሰባት ቅዳሜ ስምንት እሁድ ይገኛሉ፡፡ ይህም የጾሙን ጊዜ ስምንት ሳመንታት ያደርገዋል፡፡ የመጀመርያው ሳምንት ህርቃል ተብሎ ይታወቃል ወደ ጾሙ መግቢያ መለማመጃ ማለት ነው፡፡ የመጨረሻው ሳምንት ሕማማት ነው ክርስቶስ መከራ የተቀበለበት ቀን በመሆኑ ነው፡፡
#ጾመ_ሐዋርያት
ጾመ ሐዋርያት ሀብተ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ወንጌልን ለሕዝብ ከማስተማራቸው አስቀድመው ጾመዋል፡፡ የሰኔ ጾም ይባላል፡፡ ይህ ጾም ከፍና ዝቅ ስለሚል የተወሰነ ቀን የለውም አንዳንድ ጊዜ ከአርባ ይበልጣል ሌላ ጊዜ ደግሞ ከሰላሳ ያንሳል፡፡
#ጾመ_ነብያት
ለአዳም የተሰጠው ተስፋ ይጠብቁ የነበሩ ነብያት የጾሙት ነው፡፡ ነብያት ስለመሲህ መምጣት በናፍቆት ይጸልዩ ነበር፡፡
#ጾመ_ፍልሰታ
ጾመ ማርያም ይባላል፡፡ የእመቤታችን የዕረፍት፣ ትንሳኤና ዕርገት ምስጢር ለሐዋርይት የተገለጠበት ታሪክ መታሰቢያ ጾም ነው፡፡
ሐዋርያት ከሐምሌ 1-14 ድረስ ጾመው ድንግል ማርያም ተገልጣላቸዋለች በ 16ኛው ቀን አርጋለች፡፡
#ጾመ_ገሃድ
ገሃድ ማለት ግልጥ ይፋ፣ በገሃድ የሚታይ ማለት ነው፡፡ መለኮት የተገለጠበት ጌታ ልዩ የሆነ የአንድነትና የሶስትነት ምስጢር የተገለጠበት ስለሆነ ይህን ስያሜ አግኝቷል፡፡ ማቴ 3፡16 ዮሐ 1፡29
#ጾመ_ሰብአ_ነነዌ
ይህ የነነዌ ሰዎች የጾሙት ነው፡፡ የዚያች አገር ሰዎች የፈጸሙት በደል በእግዚአብሄር ፊት ታላቅ ሆኖ በመገኘቱ ቅጣት ታዝዞባቸው ነበር፡፡ የነነዌ ጾም ሰኞ፣ ማክሰኞ እና ዕረቡ ሶስት ቀን ነው፡፡
#ጾመ_ድህነት (የዕረቡና የአርብ)
ከትንሳኤ በኋላ ከሚኖሩት 50 ቀኖች በቀር ዕረቡና አርብ ዓመቱን በሙሉ የጾም ቀኖች ናቸው፡፡ እንደጾሙአቸው የተደረገው አርብ እና ዕሮብ፤ ዕሮብ የተፈረደበት አርብ የተሰቀለበት ቀን መሆኑን አስመልክቶ ነው፡፡
፪. #የግል_ጾም
በሕግ የታወቁ አጽዋማት በግልጥ በማህበር ይጾማሉ፡፡ የግል ጾም ግን ከዚህ የተለየ ነው፡፡ በሰዎች የግል ፍላጎትና የሕሊና ውሳኔ ሚጾም የፈቃድና የንስሐ ጾም ነው፡፡ ማቴ 5፡6 ማቴ 6፡18
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
ከእናንተ የመጣ ጥያቄ
አርብ እና ዕሮብ ለምን እንፆማለን?
መልስ ✅
ዕሮብን የምንፆምበት ምክንያት ሊቃነ ካህናት ጌታችንን ለመያዝ የተነጋገሩበት ዕለት / ምክረ አይሁድ /ስለሆነ ነው
አርብን የምንፆመው ደግሞ ጌታችንና አምላካችን እየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ተሰቅሎ ዓለምን እኛን ያዳነበት ቀን ስለሆነ እንፆማለን ማለት ነው።
ዲ/ን ፍቅረአብ ወ/ሀና
ጥያቄ ለመጠየቅ ከፈለጉ👇
👉 @fikreabe ይላኩልን
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
https://t.me/yetewahedofera
💙💙💙💙💙💙💙💙
አገልግሎቱን መደገፍ መርዳት ለምትፈልጉ ሃሳብ አስተያየት ጥያቄ ካላችሁ በዚህ በኩል ያናግሩን!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉👉 @Fikreabe 👈👈👈👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆