ትምህርት ሚኒስቴር!በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ወደ 11ኛ ክፍል መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ!
በ2011ዓ.ም የአጠቃላይ ትምህርት (10ኛ ክፍል) ማጠቃለያ ሀገር አቀፍ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ወደ 11ኛ ክፍል መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ ዛሬ ይፋ መሆኑን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡
በዚህም መሰረት፡- የመደበኛ፣የማታና የግል ተፈታኝ ተማሪዎች ለወንድ 2.00 እና በላይ ለሴት 1.86 እና በላይ ሆኖ የማታና የግል ተፈታኝ ተማሪዎች በማታው ፕሮግራም ይቀጥላሉ።
ለአካል ጉዳተኞች መስማት የተሳናቸው ለወንድ 1.86 እና በላይ ለሴት 1.71 እና በላይ እንዲሁም ለዓይነ ስውራን ለወንድ 1.71 ለሴት 1.61 እንዲሆን ተወስኗል።
ልዩ ድጋፍ የሚሹ ክልሎች፣አርብቶ አደር አካባቢዎች እና የፀጥታ ችግር የታየባቸው አካባቢዎች ደግሞ ለወንድ 1.86 ለሴት 1.71 እንዲሆን መወሰኑን ኤጀንሲው አስታውቋል።
ከዚህ በተጨማሪ፦ ሁሉም ወደ 11ኛ ክፍል የሚገቡ ተማሪዎች የሚመርጡት የትምህርት መስክ በትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ-ካርታው በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት በምርጫ ተፈጥሮ ሳይንስና ማህበራዊ ሳይንስ ብቻ ይሆናል፡፡
ከዚህ በፊት የአጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት 10ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና 2.00 ነጥብ እና ከዚያ በላይ ያመጡ በማታው ፕሮግራም የ11ኛ ክፍል ትምህርታቸውን መቀጠል የሚችሉ መሆኑን ኤጀንሲው አስታውቋል፡፡
ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia