Addis Standard Amharic


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


አዲስ ስታንዳርድ በጃኬን አሳታሚ ኃ.የተ.የግ.ማ. ባለቤትነት ስር የሚታተም በኢትዮጵያ የሚገኝ ነፃ እና ገለልተኛ ሚዲያ ነው። አዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የአዲስ ስታንዳርድ እንግሊዝኛ ሕትመት አካል ነው።
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


#ሶማሊያው ፕሬዝዳንት ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ኤርትራ ገቡ

የሶማሊያ ዝሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃመድ ለስራ ጉብኝት ዛሬ ታህሳስ 16/ 2017 ከሰዓት በኋላ #አስመራ መግባታቸውን የ #ኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አስታወቀዋል።

ፕሬዝዳንቱና ልዑካን ቡድናቸው አስመራ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል ሲሉ የማስታወቂያ ሚንስትሩ የማነ ገ/መስቀል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል።

ሁለቱ መሪዎች የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን እንዲሁም የጋራ ጠቀሜታ ያላቸውን ቀጠናዊ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች የበለጠ ማጠናከርን በተመለከተ ይወያያሉ ተብሏል።

በመስከረም ወር መገባደጃ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሃሰን ሼክ ሞሃመድ፣ የግብጹ ፕሬዝዳንት አብደል ፈታ አልሲሲ እና የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈውርቂ ጋር በኤርትራ ባደረጉት የሶስትዮች ጉባኤ ሶማሊያ የየብስ እና የባህር ድንበሮቿን ለመጠበቅ የሚስያችል አቅሟን ለማጠናከር ስምምነት አድርገዋል።


================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm


ዜና: አራት የስኳር ፋብሪካዎች ከክረምት ጥገና በኋላ መደበኛ ስኳር የማምረት ስራቸውን መጀመራቸው ተጠቆመ

ከ2016 ዓ.ም የክረምት ወራት መግባት ጋር ተያይዞ አጠቃላይ የጥገና ሥራ ሲያከናውኑ የቆዩት አራት ስኳር ፋብሪካዎች መደበኛ የማምረት ሥራቸውን መጀመራቸውን #የኢትዮጵያ የስኳር ኢንደስትሪ ግሩፕ አስታወቀ።

ስኳር ማምረት የጀመሩት ፋብሪካዎች ወንጂ ሸዋ፣ መተሐራ፣ ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3/1 እና ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 መሆናቸውም ተገልጿል፤ የፊንጫ ስኳር ፋብሪካም የክረምት ወራት አጠቃላይ የጥገና ሥራውን አጠናቆ ወደ ኦፕሬሽን እየገባ መሆኑ ተጠቁሟል።

ፋብሪዎቹ ስራ አቁመው የተለያዩ የእርሻና የመስኖ ማሽነሪዎቻቸውን እንዲሁም የመስኖ አውታር አጠቃላይ የጥገና ሥራዎችን በክረምቱ ወራት ሲያከናውኑ እንደነበር ተገልጿል።

በእስከአሁኑ ሂደት ፋብሪካዎቹ ከ300ሺ ኩንታል የሚበልጥ ምርት ማምረት መቻላቸውንም ከኢትዮጵያ የስኳር ኢንደስትሪ ግሩፕ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በአሁኑ ወቅት ፋብሪካዎቹን እያጋጠማቸው ያለው ዋነኛ ችግር የጉልበት ሰራተኞች አቅርቦት ችግር ነው ሲል መረጃው አመላክቷል፤ የሰው ሐይል ከሚገኝባቸው ክልልች ጋር ተቀርርቦ በመስራት ችግሩን ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ ይገኛል ብሏል፡፡

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አመቻቺነት መንግስት በበጀት ዓመቱ ለስኳር ፋብሪካዎች የውጭ አገር መለዋወጫ ግዢ የሚውል 27 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር መድቦ ከዚህ ውስጥ እስካሁን 10 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚደርስ የመለዋወጫ ግዢ ተከናውኗል ሲል ገልጿል።

በአጠቃላይ በሀገሪቱ ከሚገኙ 8 የስኳር ፋብሪካዎች ውስጥ 4ቱ ስራ መጀመራቸው ተመላክቷል።


ዜና፡ ግዙፉ የ #ቻይና ኤሌክትሪክ መኪና አምራች ቢዋይዲ በ #ኢትዮጵያ በአምስት የኤሌክትሪክ ሞዴሎችን ለሽያጭ አቀረበ

የቻይናው የመኪና አምራች ቢዋይዲ (BYD) አምስት የኤሌክትሪክ ሞዴሎችን በማቅረብ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ በይፋ መግባቱን አከፋፋዩ ሞኤንኮ አስታውቋል።

በኤሌክትሪክ ተስከርካሪ አምራችነት ዘርፍ ታዋቂ የሆነው ኩባንያው፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ትላልቅ የመኪና አከፋፋዮች አንዱ ከሆነው ሞኤንኮ ጋር በመተባበር ወደ ገበያ መግባቱን በ #አዲስ_አበባ በተካሄደው የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ አስታውቋል።

በተጨማሪም ቢዋይዲ ለደንበኞቹ የመኪና ሽያጭ እና የጥገና አገልግሎቶችን ለማቅረብ በአዲስ አበባ #ቃሊቲ ማሳያ ክፍልና የድህረ ሽያጭ አገልግሎት ማዕከል ከፍቷል። #መገናኛ አካባቢም አዲስ የተሽከርካሪ ማሳያ ክፍል በይፋ መክፈቱን አስታውቋል።

ተጨማሪ ያንብቡ፦ https://addisstandard.com/Amharic/?p=6276


ዜና: "በሰሜን #ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ በአልሚ ምግብና በመድሀኒት አቅርቦት ችግር ምክንያት ዜጎች ለጉዳት ተዳርገዋል" - ኮሚሽኑ

#በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ ነዋሪዎች ላይ ጉዳት የደረሰው በአልሚ ምግብና በመድሀኒት አቅርቦት ችግር ምክንያት ነው ሲል የክልሉ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበሪያ ኮሚሽን አስታወቀ።

በሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ሳቢያ 110 ሺህ ወገኖች አስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው መሆኑን ኮሚሽኑ ገልጿል።

“በኛ በኩል የምግብ እህል በተገቢው ጊዜና ሁኔታ የቀረበ ቢሆንም በአሜሪካ የልማት ተራድኦ ድርጅት USAID በኩል የሚተላለፉ የደጋፊ ምግቦችን /Supplments/ በወቅቱ ባለማድረስ በመጣ ክፍተት ችግሩ ተከስቷል” ሲሉ ም/ኮሚሽነሯ ሠርካዲስ አታሌ ማስታወቃቸውን ከክልሉ ኮሚሽን ማስተባበሪያ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

https://addisstandard.com/Amharic/?p=6272


#ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ 5 ወራት ውስጥ ከቡና ወጪ ንግድ 797 ሚሊዮን ዶላር አገኘች

ኢትዮጵያ በበጀት አመቱ የመጀመሪያ አምስት ወራት ውስጥ 178,000 ቶን ቡና ለውጭ ገበያ በማቅረብ 797 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታውቋል።

ይህም ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በመጠን የ72 በመቶ እንዲሁም ከገቢ አንጻር የ55 በመቶ ብልጫ አለው ተብሏል።

የባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የግብይት ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሻፊ ዑመር ለኢዜአ እንደተናገሩት ባለፉት አምስት ወራት 117 ሺህ ቶን ቡና ወደ ውጭ ለመላክ ታቅዶ ከ178 ሺህ ቶን በላይ ማሳካት እንደተቻለ ገልፀዋል።

አክለውም በበጀት ዓመቱ አጋማሽ ከ200 ሺህ ቶን በላይ ቡና በመላክ 1 ቢሊዮን ዶላር ማግኘት እንደሚቻል ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ በባለፈው በጀት ዓመት 298 ሺህ ቶን ቡና ወደውጭ በመላክ 1 ነጥብ 43 ቢሊዮን ዶላር ያገኘች ሲሆን ዘንድሮ መጠኑን ወደ 400 ሺህ ቶን በማሳደግ ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ለማግኘት ማቀዷ ተመላክቷል።

================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek


“የገቢዎች ቢሮ ያሳለፈው ውሳኔ የኢንዱስትሪ ሰላምን እንዳያውክ እሰጋለሁ”_የኢትዮጵያ ሆቴልና ቱሪዝም ፌደሬሽን

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የደሞዝ ግብር ማጭበርበርን ለመቅረፍ እንደ ሆቴሎች እና ካፌቴሪያዎች ባሉ የተመረጡ የንግድ ተቋማት ላይ “ዝቅተኛ የደመወዝ ተመን እና የሰራተኛ ብዛትን” በተመለከተ ያሳለፈው ውሳኔ የኢንዱስትሪ ሰላምን እንዳያውክ እሰጋለኹ ሲል የኢትዮጵያ ሆቴልና ቱሪዝም ፌደሬሽን አስታወቀ።

የፌደሬሽኑ ፕሬዝደንት ዶ/ር ፍትህ ወልደሰንበት የቢሮው ውሳኔ የአሠሪና ሠራተኛ አዋጁን መሠረት ያላደረገና ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልም እንደሃገር ገና በሂደት ላይ ባለበት ወቅት የተወሰነ መሆኑን መግለጻቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።

"ውሳኔውን በተመለከተ ከንግድ ማህበረሰቡ ጋር በቂ ውይይት አልተደረገም" ያሉት ፕሬዝዳንቱ ዝቅተኛ የሠራተኛ ብዛትን በተመለከተ ንግድን በነጻነት ከትንሽ ተነስቶ ለማሳደግ አዳጋች እንደሚያደርገው ጠቁመዋል።

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሰውነት አየለ በበኩላቸው ከዚህ በፊት እንደ ምግብ እና መጠጥ ቤቶች ያሉት የንግድ ተቋማት ለሠራተኞቻቸው ስለሚከፍሉት ደመወዝ በአግባቡ እንደማይገልጹ ጠቅሰው የግብር ማጭበርበርን ለማስቀረት አዲስ አሰራር መዘርጋቱን አመልክተዋል።

በዚህም ቢሮው ለሆቴሎች፣ ለካፊቴሪያዎች፣ ለምግብ እና መጠጥ ቤቶች እንዲሁም ለሥጋ ቤቶች ዝቅተኛ የሰራተኛ ብዛት ተመን እና ዝቅተኛ የሰራተኞች ደመወዝ ወለል ማስቀመጡን ተናግረዋል።

አክለውም ይህ አዲስ አሰራር አነስተኛ የንግድ ተቋማትን እንደማይመለከት ገልጸው የንግድ ሥርዓቱን የሚያውክ ነገር የለም ብለዋል።


ዜና፡ #ሶማሊያ#ኢትዮጵያ ወታደሮች ጥቃት ፈጸመዋል ስትል ባቀረበችው ክስ ኢትዮጵያ ማዘኗንና "ሀሰት" መሆኑን ገለጸች

ሶማሊያ በዶሎው የኢትዮጵያ ወታደሮች ጥቃት ፈፅመዋል ስትል ባቀረበችው ክስ ኢትዮጵያ ማዘኗን በመግለጽ ክሱን "ሀሰተኛ" ስትል ጠራች። ኢትዮጵያ ክሱ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል ግንኙነትን ለማደስ የተጀመረውን ጥረት ለማስተጓጎል የታሰበ ነው ብላለች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ ድርጊቱ "የአፍሪካን ቀንድ ለማተራመስ የሚሹ" እና "በቀጠናው ሰላም እንዳይኖር የሚሰሩ" አካላት ተግባር መሆኑን ገልጿል።

ኢትዮጵያ ይህን ምላሽ የሰጠችው ሶማሊያ ዶሎው በተባለው የድንበር ከተማ በኢትዮጵያ ኃይሎች "በግልጽ ጸብ አጫሪነት ድርጊት" ፈጸመዋል ስትል መክሰሷን ተከትሎ ነው። ሶማሊያ የኢትዮጵያ ወታደሮች በሶማሊያ ብሔራዊ ጦር፣ በብሔራዊ መረጃና ደህንነት ኤጀንሲ እና በሶማሊያ የፖሊስ ኃይል ቤዝ ላይ "ያልተጠበቀ ጥቃት" መፈጸማቸውን በመግለጽ የሞቱና የቆሰሉ ሰዎች መኖራቸውን ተናግራለች።

ያንብቡ፦ https://addisstandard.com/Amharic/?p=6262


ዜና: #ኢትዮጵያ ከአጎዋ ተጠቃሚ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ በድጋሚ አለመካተቷ ተገለጸ

ኢትዮጵያ #ከአሜሪካ ነጻ የንግድ ስምምነት አጎዋ በድጋሚ ተጠቃሚ ለመሆን ያደረገችው ጥረት አለመሳካቱ ተገለጸ።

የዩናይትድ ስቴት የንግድ ተወካዮች ምክር ቤት ከአጎዋ ተጠቃሚ የሚሆኑ 32 ሀገራትን ስም ዝርዝር ታህሳስ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ይፋ ያደረገ ሲሆን ኢትዮጵያ ከተዘረዘሩት ሀገራት ውስጥ አልተካተተችም።

ባሳለፍነው አመት ሐምሌ ወር ላይ የአሜሪካ የንግድ ተወካይ ቢሮ ባለስልጣናት ኢትዮጵያ ለአጎዋ ብቁ መሆን አለመሆኗን ለመለየት ውይይት ያደረጉ ቢሆንም ተጠቃሚነቷ እንዲነሳ የሚያደርገው ውሳኔ አሁንም እንዲቀጥል ተደርጓል።

ከሶስት አመታት በፊት በትግራይ የተካሄደውን ጦርነት ተከትሎ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ኢትዮጵያን ከአፍሪካ ግሮውዝ ኦፖርቹኒቲ አክት (አጎዋ) የቀረጥና ታሪፍ ነፃ መብት መሰረዛቸውን ጥር 2014 ዓ.ም ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።

በያዝነው አመት መስከረም ወር መጀመሪያ ላይ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት አምባሳደር ታየ አቅጸስላሴ ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሀመር ጋር በነበራቸው ውይይት አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የጣለቸውን የአጎዋ እገዳ እንድታነሳ መጠየቃቸው ይታወሳል።

ኢትዮጵያ ከአጎዋ ተጠቃሚነቷ መታገዷ በርካታ በሀገሪቱ በተለያዩ ዘርፎች ተሰማርተው የነበሩ ፋብሪካዎች ዘግተው እንዲወጡ ማድረጉን በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል።

================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg


ዜና: መንግስት ሰብዓዊ ዕርዳታ ተደራሽ ማድረግ የሚያስችል በቂ ክምችት አለኝ፣ የተሟላ ዝግጅት አድርጊያለሁ ሲል ገለጸ

#በኢትዮጵያ ሰብዓዊ እርዳታ የሚሹ ወገኖችን ተደራሽ ማድረግ የሚያስችል አሁናዊ በቂ የሰብዓዊ ድጋፍ ክምችትና ዝግጅት መኖሩን የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም(ዶ/ር) ገለጹ።

መንግስት በራስ አቅም ሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ ለማድረግ የሚያከናውናቸውን ተግባራት በማስተጓጎል ጥቅም ይገኛል በሚል የሚንቀሳቀሱ አካላት ከድርጊታቸው ሊታረሙ ይገባል ሲሉም አስጠንቅቀዋል።

በሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ ከአንድ ወር በፊት በቤተሰብ ደረጃ እንዲሁም አጠቃላይ ተጋላጭነትን የተመለከቱ ሁለት ጥናቶች ኮሚሽኑ ማካሄዱን አምባሳደር ሽፈራው ጠቁመዋል።

በወቅቱ የጎላ ችግር አልነበረም ያሉት ሃላፊው ነገር ግን በአንዳንድ ኪስ ቦታዎች የምግብ ዋስትና ጋር የተያያዙ ክፍተቶች መለየታቸውን ተናግረዋል።

በአካባቢው የነበረው የጸጥታ ችግር ሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ ለማድረግ እንቅፋት መፍጠሩንም ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።

ነገር ግን ጉዳዩን ከፖለቲካ ጥቅም ጋር በማያያዝ ላልተገባ ዓላማ የሚያውሉ ወገኖች አጀንዳቸው ከሰብዓዊ ድጋፍ ጋር ትስስር የሌለው ነው ሲሉ ተችተዋል።

መንግስት ችግሩን ለመቅረፍ በትኩረት እየሰራ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ ከሃይማኖት አባቶችና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በመናበብ ሰብዓዊ ድጋፎች ለሚፈለገው አካል ብቻ እንዲደርሱ መግባባት ላይ ተደርሷል ብለዋል።

መንግስት በራስ አቅም ሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ ለማድረግ የሚያከናውናቸውን ተግባራት በማስተጓጎል ጥቅም ይገኛል በሚል የሚንቀሳቀሱ አካላት ከድርጊታቸው ሊታረሙ ይገባል ሲሉ ማሳሰባቸውን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

"በጸጥታ ችግር" ለሁለት ወራት እርዳታ ባልደረሰበት ቡግና ወረዳ በሀገር ሽማግሌዎች ስምምነት መደረጉን ተከትሎ የእህል እርዳታ መጓጓዝ መጀመሩ የተመለከተ ዘገባ ባሳለፍነው ሳምንት መገባደጃ ማቅረባችን ይታወሳል፤ https://addisstandard.com/Amharic/?p=6234


#ኢትዮጵያ የአንካራውን ስምምነት ‘ሙሉ በሙሉ’ ለመተግበር ቁርጠኛ መሆኗን ገለጸች

ከአንካራው ስምምነት በኋላ የመጀመሪያ ጉብኝታቸው በ#አዲስ_አበባ እያደረጉ ከሚገኙት የ #ሶማሊያ የልዑካን ቡድን ጋር ውይይት መደረጉን ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ኢትዮጵያ የአንካራውን ስምምነት ‘ሙሉ በሙሉ’ ለመተግበር ቁርጠኛ መሆኗን ገለጹ።

የሶማሊያ የውጭና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ አሊ ኦማር እና አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በዛሬው ዕለት ባደረጉት ውይይት በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል በተርክ አሸማጋይነት ታኅሣሥ 2/2017 ዓ.ም የተፈረመውን ስምምነት ተግባራ ለማድረግ ተስማምተዋል።

በተጨማሪም ሚኒስትር ደዔታዎቹ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምን ለማስፈን እና ብልፅግናን ለማረጋገጥ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ለማጠናከር መስማማታቸውን መንግስታዊ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

የሶማሊያ ሰላም የኢትዮጵያ ሰላም መሆኑን የገለጹት አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ሽብርተኝነትን በመከላከል በቀጣናው ሰላም ለማስፈን ትብብራችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። አክለውም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማጠናከር ቀጣይነት ያለው ውይይት እናደርጋለን ብለዋል።

የሶማሊያ የውጭና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ አሊ ኦማር ከወንድሜ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ማለታቸው ተገለጿል።

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት እልባት ለመስጠት በተርክዬ አሸማጋይነት ታኅሣሥ 2/2017 ዓ.ም ስምምነት ላይ መደረሱ ይታወቃል።

በዚህም መሰረት የአንካራውን ስምምነት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼኽ ሞሐመድ በአንካራ መፈረማቸው ይታወሳል።


ዜና: #ኢትዮጵያና #ጅቡቲ በድንበር አከባቢ ሰላማችንን የሚያውኩ ያሏቸውን ሀይሎችን እንቅስቃሴ ለመግታት ተስማምተናል አሉ

የኢትዮጵያና የጅቡቲ የደኅንነት ተቋማት በድንበር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ የሁለቱን ሀገራት ሰላም የሚያውኩ ሀይሎችን በጋራ ለመግታት የሚያስችል የጋራ ግብረ-ኃይል አቋቁመው ለመሥራት ተስማምተናል ሲሉ ገለጹ።

ተቋማቱ ከሚያደርጉት የመረጃ ልውውጥ ባሻገር የጋራ ግብረ-ኃይል አቋቁመው ስምሪት ለማከናወን እና ወንጀለኞችንም አሳልፎ ለመስጠት መስማማታቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የላከላቸውን መረጃ ዋቢ በማድረግ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን በዘገባዎቻቸው አስታውቀዋል።

በጅቡቲ ሪፐብሊክ የሴኪዩሪቲ ዶክመንቴሽን ሰርቪስ ዳይሬክተር ጀነራል ሐሰን ሰይድ ካይራ የተመራ የልዑክ ቡድን ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ኢትዮጵያ መግባቱን፣ ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በጸጥታ፣ በደኅንነትና በተያያዥ ጉዳዮች መወያየታቸውን ዘገባዎቹ ጠቁመዋል።

ሁለቱም ተቋማት ትብብራቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ የሚረዳ ምክክር ማድረጋቸውን የአገልግሎቱን መረጃ ዋቢ በማድረግ ዘገባዎቹ አስታውቀዋል።

የሁለቱን ሀገራት የጋራ ስጋቶች መመከት የሚያስችሉ እንዲሁም ቀጣናዊ መረጋጋትን ለማምጣት የሚረዱ ጉዳዮች ዋነኛ የምክክሩ አጀንዳዎች እንደነበሩ በመረጃው መጠቆሙን አመላክተዋል።

ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በተለይም ሕገ-ወጥ የሰዎችና የጦር መሣሪያ ዝውውርን ለመግታት፤ ሕገ-ወጥ ስደተኞችንም ለመከላከል የሚደረገውን ትብብር ለማጠናከር መስማማታቸውን አስታውቀዋል ብለዋል።

ኢትዮጵያ በጅቡቲ ወደብ በኩል የምታከናውነው የወጪ ገቢ ንግድ ላይ የሚስተዋሉ የደኅንነት ችግሮችን መፍታት የሚያስችል ውይይት መካሄዱንም የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት መረጃ ዋቢ በማድረግ አስታውቀዋል።


#ግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከ #ቀይ_ባህር ጋር የማይዋሰኑ ሀገራት ባህሩን መጠቀማቸው “ተቀባይነት የለውም” ሲሉ ገለጹ

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ "ከቀይ ባህር ጋር ከሚዋሰኑ ሀገሮች ውጭ ያሉ ማኛቸውም ሀገሮች በህሩን መጠቀማቸውተቀባይነት የለውም" ሲሉ ሰኞ ዕለት በ #ካይሮ ከሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ ሞአሊም ፊኪ ጋር ባደረጉት የሁለትዮሽ ውይይት ተናግረዋል።

ሚኒስትሮቹ በውይይታቸው በቅርቡ በ #ሶማሊያ እና የኢትዮጵያ መካከል #በአንካራ አሸማጋይነት የተደረገውን ድርድርን ጨምሮ ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። ፊኪ እነዚህ የዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች "በክልሉ ውስጥ ተጨማሪ ብጥብጥን በመመለስ የተሳሱ" እንደሆኑ ጠቅሰው ይህም "የሁሉንም ፍላጎት ሊያቃጥል የሚችል አደገኛ ፍንዳታ" እንዳያጋጥም ተከላክሏል ብለዋል።

ውይይቱ ያተኮረው በ #ኢትዮጵያና በ #ሶማሊላንድ መካከል ባሳለፍነው አመት የተደረገውን ስምምነት ተከትሎ ባሉ በክልሉ የባህር ላይ ደህንነት ላይ ነው። ፊኪ "የሶማሊያ ሉዓላዊነት፣ ነፃነት እና የግዛት አንድነት" መጠበቅ አስፈላጊ መሆኑን አፅንዖት ሰጥቷል።

ሁለቱ ሚኒስትሮች በካይሮ ያደረጉትን ስብሰባ ያጠናቀቁት "የሀገሮቹን ትስስር ወደ ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ደረጃ" ከፍ ለማድረግ በጋራ መግለጫቸው ላይ ፊርማ በማኖር ነው።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm


ዜና: ሰሞኑን ከተከሰቱት ከፍተኛውና በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 9 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ትላንት ምሽት መከሰቱ ተገለጸ

ትላንት ታህሳስ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ሁለት #የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱ ተገለጸ። የመጀመሪያው የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተው ቀን 9 ሰዓት አከባቢ ሲሆን ሁለተኛው የተከሰተው ከምሽቱ 4 ሰዓት ከ41 ደቂቃ ላይ መሆኑ ተጠቁሟል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፈንታሌ ተራራ በመተሃራ አቅራቢያ ትናንት ምሽት የተከሰተው መሬት መንቀጥቀት ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ መሰማቱን አስታውቋል።

በዩኒቨርሲቲው የጂኦ ፊዚክስ ሕዋ ሣይንስና አስትሮኖሚ ተቋም የሴስሞሎጂ ትምህርት ክፍል ሃላፊ አታላይ አየለ (ፕ/ር) እንዳሉት፥ በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳና በመተሃራ አካባቢ ከታሕሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የተለያየ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ ነው፡፡

ይህም ሰሞኑን ከተከሰቱት ከፍተኛው መሆኑን ጠቅሰው ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ መሰማቱን አስረድተዋል።

በአካባቢው የሚከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ከቀን ቀን እየጨመረ መምጣቱን ጠቁመው ነዋሪዎች ላይ ችግር እንዳያስከትል የቅርብ ክትትል እንዲደረግ አሳስበዋል፡፡

በአፋር ክልል የዞን 3 ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዶ አሊ አቡበከር በበኩላቸው ከምሽቱ 4፡41 የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ከበፊቱ በተለየ ሁኔታ ንዝረቱ መቆየቱን አንስተዋል።

እስከ ሌሊቱ 7 ሰዓት ድረስም በአካባቢው የተለያየ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን መናገራቸውን ከፋና ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ሌላኛው ትናንት ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ በፈንታሌ ተራራ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 6 የሆነ ነው ተብሏል።


#አንካራ ስምምነትን ተከትሎ የ #ሶማሊያ ልዑካን ቡድን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ #አዲስ_አበባ ይገባል

በሶማሊያ የውጭ ጉዳይና አለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አሊ ኦማር የተመራ የሶማሊያ ፌዴራል መንግስት የልዑካን ቡድን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ እንደሚገባ ተገለፀ።

ጉብኝቱ በአንካራው ስምምነት መሰረት ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል ሲል የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የልዑካን ቡድኑ በጋራ ጥቅም እና ትብብር ላይ የተመሰረተ አጋርነት ለመፍጠር የለውጥ ዕድሎችን በማሰስ ላይ እንደሚያተኩር ተጠቁሟል።

በተጨማሪም የሶማሊያ መንግስት ከጎረቤት ሀገራት ጋር በሉዓላዊነት እና በግዛት አንድነት መርሆዎች ላይ የጸና ግንኙነት ለመፍጠር ባለው ራዕይ ቁርጠኛ መሆኑ ተመላክቷል።

ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በባሕር በር ሳቢያ በመካከላቸው የተፈጠረውን ውዝግብ ለማርገብ ታህሳስ 2/ 2017ዓ/ም በቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን አሸማጋይነት በአንካራ ስምምነት መፈጸማቸው ይታወሳል።


ዜና: አቶ #ክርስቲያን እና አቶ #ዮሐንስ "ህመማቸው እንደባሰባቸው" ቤተሰቦቻቸው ተናገሩ፣ ከቀዶ ሕክምናው በኋላ ወደ ሆስፒታል አለመወሰዳቸውን ገልጸዋል

በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እስር ላይ የሚገኙት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ እና የአማራ ክልል ምክር ቤት አባሉ አቶ ዮሐንስ ቧያለው "ለከፍተኛ ሕመም" መዳረጋቸውን የቅርብ ቤተሰቦቻቸው አስታወቁ።

አቶ ክርስቲያን እና አቶ ዮሐንስ ቀዶ ሕክምና ከተደረገላቸው በኋላ "የማያቋርጥ የደም መፍሰስ እንዳጋጠማቸው" ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ ቤተሰባቸው ነግረውኛል ሲል ቢቢሲ በዘገባው ጠቁሟል።

አንድ የአቶ ክርስቲያን የቅርብ ቤተሰብ "ቁስሉም አልደረቀም እና ደግሞ ደም እየፈሰሳቸው ነው፤ ሐኪሞቹም ተናግረዋል፤ ደም መፍሰስ ሊያጋጥም እንደሚችል እና ይህ ሲያጋጥምም እንድታመጧቸው ብለው ነበር" ብለዋል ያለው ዘገባው ነገር ግን ከቀዶ ሕክምናው በኋላ ወደ ሆስፒታል አለመወሰዳቸውን ነግረውኛል ብሏል።

ሕክምናውን ተከትሎ ለሚከሰተው የደም መፍሰስ ማስታገሻ እንደተሰጣቸው ያስታወሱት የቤተሰብ አባላቱ "የተሰጣቸው የማስታገሻ መድኃኒትም አልቆባቸዋል። ሕመሙን ለማስታገስ ቶሎ ቶሎ እየወሰዱት ስለነበር" ሲሉ ተናግረዋል ብሏለ።

የአቶ ዮሐንስ ቤተሰብ አባል፤ "ትላንት ማስታገሻ ይዘን ስንሄድ መግባት አትችሉም ተባልን፤ ለምንድን ነው ስንል? ሊቀየሩ ነው አሉን። እስከ ትናንት ግን እነሱ አይሄዱም ብለውን ነበር። ትናንት በድንገት ተነስተው ሊወጡ ስለሆነ ምንም ምግብ ማስገባት አትችሉም መድኃኒትም አይገባም ብለው ከለከሉን" ማለታቸውንም ዘገባው አካቷል።

የአቶ ክርስቲያንም የቤተሰብ አባል በተመሳሳይ "ትላንትና ምግብም ማስታገሻም ይዘን ስንሄድ የሚያስገባን ስለሌለ ተመለስን" ሲሉ መናገራቸውን አስታውቋል።


ዜና፡ በ #ኮሬ ዞን ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ሁለት አርሶ አደሮች ተገደሉ

በ #ደቡብ_ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ ቆሬ ቀበሌ ትናንት ታህሳስ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት በእረኝነት ላይ የነበሩ ሁለት የአከባቢው አርሶ አደሮች "በአሰቃቂ ሁኔታ" መገደላቸውን ነዋሪዎችና ኃላፊዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።

ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ነዋሪ ጥቃቱ ትናንት እሁድ ታህሳስ 13 አመሻሽ 11:30 ላይ “ከ #ኦሮሚያ ክልል #ምዕራብ_ጉጂ ዞን ተሻግረው የመጡ የሸኔ ታጣቂዎች” ባሏቸው አካላት መፈጸሙን ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል።

በጎርካ ወረዳ የቆሬ ቀበሌ ምክትል ሊቀ መንበር የሆኑት ደስታዬ ዮሐንስ በዚህ ሳምንት ብቻ 3 ሰላማዊ ሰዎች “ከአዋሳኝ ዞኑ በመጡ የሸኔ ታጣቂዎች” መገደላቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ አስታውቀዋል።

ያንብቡ፦
https://addisstandard.com/Amharic/?p=6244


ዜና: #የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተረክርስቲያን በሀገሪቱ በሚካሄዱ ግጭቶች ሳቢያ መንፈሳዊ ተግባራት ለማከናወን መቸገሯን አስታወቀች

በግጭቶቹ ሳቢያ አጥቢያዎቼም ተዘግተዋል ብላለች

በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚካሄድ ላይ ባሉ ግጭቶች ሳቢያ ሀይማኖታዊ ተግባራት ለማከናወን መቸገሯን የኢትዮጵያ ካቶሊካዊ ቤተረክርስቲያን አስታወቀች፤ በግጭቶቹ ሳቢያ አጥቢያዎቼም ተዘግተዋል ብላለች።

ቤተክርስቲያኗ ይህንን ያስታወቀችው ከሳምንት በፊት ለአራት ቀናት ሊቃነ ጳጳሳቷ በሞጆ ባካሄዱት 57ኛ ሀገራዊ ጉባኤ መጠናቀቁን ተከትሎ ትላንት ታህሳስ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ባስተላለፉት መልዕክት ነው።

“ክሊኒኮቻችን፣ ትምህርት ቤቶቻችን እና የአርብቶ አደር ማዕከሎቻችን ውድመት ደርሶባቸዋል” ስትል በመግለጫዋ የጠቆመችው ቤተክርስቲያኗ “አገልጋዮቼ እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ላይ ስርአተ አምልኮ ለማከናወን ተገደዋል፣ አንዳንዶቹ ደግሞ ለህልውናቸው አስጊ የሆነ የጸጥታ ችግር በመፈጠሩ አጥቢያዎቻቸውን ዘግተው ለመሰደድ ተገደዋል” ብላለች።

“በጦርነት፣ በዕርስ በርስ ግጭቶች፣ በዋጋ ንረት ሳቢያ በህዝባችን ላይ እየተፈጠረ ያለውን የዕለት ተዕለት ጉዳት እና ቁስል እንገነዘባለን” ስትል ገልጻለች።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=6241


ዜና: የአለም ባንክ #የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጨምሮ ሶስት ባንኮችን አሰራር ለማሻሻል የሚውል 700 ሚሊየን ዶላር ብድር መስጠቱ ተጠቆመ

የአለም ባንክ ኢትዮጵያ ለምታካሂደው የፋይናንስ ስርአት ማሻሻያ የሚውል 700 ሚሊየን ዶላር ብድር መስጠቱ ተገለጸ፤ ብድሩ የሚውለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን መልሶ ለማደራጀት፣ ብሔራዊ ባንክንና የልማት ባንክን አሰራር ለማሻሻል መሆኑም ተጠቁሟል።

ብድሩን ያጸደቀው አለም አቀፉ የልማት ማህበር (IDA) መሆኑን ባንኩ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ማህበሩ ብድሩን ያጸደቀው የሀገሪቱ የገንዘብ ስርአት ቀጣይነት ያለው እና የተረጋጋ እንዲሆን ለሚተገበሩ ፕሮጀክቶች በሚል መሆኑን ባንኩ ጠቁሟል።

የኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ በርካታ አሳሳቢ ፈተናዎች የተጋረጠ ነው ሲል የገለጸው የአለም ባንክ መግለጫ በተለይም በቂ ያልሆነ የቁጥጥር ማዕቀፎች ያሉት እና የህዝብ የፋይናንስ ተቋማቱ እጅግ ደካማ መሆናቸው ነው ሲል አመላክቷል።

የማሻሻያ ፕሮጀክቱ በዋናነት እነዚህን ችግሮች የሚፈቱ አሰራሮችን ለመዘርጋት ይውላል ሲል ገልጿል፤ ከፕሮጀክቶቹ መካከልም የብሔራዊ ባንክ የክትትልና የቁጥጥር ማዕቀፍን ማዘመን አንዱ መሆኑን ጠቁሟል።

የአለም ባንክ ከፈቀደው ብድር ውስጥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የአስተዳደር ስርአት ማሻሻል፣ የባንኩን የሒሳብ መዛግብት መልሶ ማዋቀር እና ባንኩን መልሶ ማደራጀት የሚያስችል ፕሮጀክት መተግበሪያም የሚሆን እንደሚገኝበት አመላክቷል።

ሌላኛው ብድሩ የሚውለው ልማት ባንክ ወደ ዘላቂ ልማት ፋይናንስ ተቋምነት ለማሸጋገር ለሚተገበሩ ፕሮጀክቶች መሆኑንም አስታውቋል።

https://web.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid024g7VmtvJ7SiGviM3xYgt5azinV8bgQe2WwpbE7HVymVMRWP6djPrCJ6GERuRzoC8l


ከኮሪደር ልማት የፍርስራሽ ግምት ለግል ጥቅማቸው ሊያውሉ የሞከሩ 3 አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ

በአዲስ አበባ መንግስትና ህዝብ የጣለባቸውን ሃላፊነት ወደ ጎን በመተው ከኮሪደር ልማት የፍርስራሽ ግምት ለግል ጥቅማቸው ሊያውሉ የሞከሩ 3 አመራሮች በከተማው የፀጥታ አካላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ።

በቁጥጥር ስር የዋሉት አመራሮቹ፤ የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ራሄል ኃ/ኢየሱስ ጨምሮ የወረዳው ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደበበ ጉልማ፣ የወረዳው የፋይናስ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታደለ ግዛቸው መሆናቸውን የከተማ አስተዳደርሩ ትናንት ባወጣው መግለጫ ገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 በካዛንችስ የኮሪደር ልማት ላይ ባልተገባ አካሄድ የፍርስራሽ ግምት ለግል ጥቅም ለማዋል በመሞከር ላይ እያሉ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ከከተማ እስከ ክ/ከተማ የፀጥታ መዋቅሩን በመጠቀምና ክትትል በማድረግ መሆኑን ተገልጿል።

በዚህም መሠረት የወንጀል ማጣራት ሂደቱ በሚመለከተው አካል እየተካሄደ ይገኛል ያለው መግለጫው አስተዳደሩ ሌብነትና ብልሹ አሰራር የልማታችን ዕንቅፋት እንዳይሆን ተገቢውን እርምጃ ወስዷል ብሏል፡፡

አስተዳደሩ “አስተዳደሩ የከተማዋን ፈተናዎች ባሏት ፀጋዎቿ በማሻገር ሁለንተናዊ ብልፅግናዋን ለማረጋገጥ በሚጥርበት በዚህ ወቅት የኮሪደር ልማትን መነሻ በማድረግ የግል ፍላጎታቸውንና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ የሚሯሯጡ አልጠፉም” ሲሉም ገልጿል።

በቀጣይም የተጀመሩ ልማቶቻችንን በማሳለጥ ሌብነት ላይ የሚደረገው ትግል ተጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል።


ዜና: "በጸጥታ ችግር"ለሁለት ወራት እርዳታ ባልደረሰበት ቡግና ወረዳ በሀገር ሽማግሌዎች ስምምነት መደረጉን ተከትሎ የእህል እርዳታ መጓጓዝ መጀመሩ ተገለጸ

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ በህጻናት መቀንጨርና በምግብ እጥረት ለተጎዱ ከ110 ሺህ በላይ ሰዎች ከሁለት ወራት በኋላ የርዳታ እህል መጓጓዝ መጀመሩን የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ገለጸ።

በተጨማሪም በላሊበላ ከተማ 34ሺህ ለሚሆኑ ሰዎች 5100 ኩንታል እርዳታ ለፌደራል መንግሥት መጠየቁን ጠቅሰው እስከዚህ ሰዓት ድረስ 1200 ኩንታል መግባቱን አመላክተዋል፡፡

እርዳታው መጓጓዝ የጀመረው በጸጥታ ችግር ምክንያት ላለፉት ሁለት ወራት እርዳታ መድረስ ባለመቻሉ በሀገር ሽማግሌዎች ስምምነት መደረጉን ተከትሎ መሆኑን የሰሜን ወሎ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለሙ ይመር ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል።

ይህ በእንዲህ እያለ አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በወረዳው የተከሰተውን የምግብ እጥረት ቀውስ የሚገልጹ ሪፖርቶችን እየተከታተለ መሆኑን ትናንት ታኅሣሥ 11 ቀን 2017 ዓ.ም አመልክቷል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=6234

20 last posts shown.