ቅድስት ሆይ ለምኝልን🙏


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


ሰአሊ ለነ ማርያም 🙏

Related channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


እንኳን ለብርሀነ ልደቱ በሰላም አደረሰን
ታኅሣሥ 29/2017 ዓ.ም


ዘመኑ የሠላምና የፍቅር፣ የመተሳሰብና የምስጋና ዓመት ይሁንልን። አሜን₃ 🤲🙏
           💚💛❤️    💚💛❤️    💚💛❤️


🕊 ዛሬ ቀኑ 27 ቸሩ መድኃኔዓለም🙏🏻❤️

«መድኃኔዓለም ማለት ዓለምን ያዳነ የዓለም መድኃኒት  ማለት ነው። ሰው በመበደሉ ምክንያት ከክብር ተዋርዶ ይኖር ነበር። ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የተዋረደውን ሰው እርሱ በመስቀል ተሰቅሎ ወደ ቀደመ ክብሩ መለሰው። ምን ዓይነት ፍቅር ነው???🥹

ወንድሜ/እህቴ አስባችሁታል ግን ስለ እኛ ብሎ እኛን ለማዳን ብሎኮ ነው የተሰቀለው። ራቁትን መሰቀል ምን ያህል አሳፋሪ ነገር እንደሆነ እናውቀዋለን። ጌታ ግን እኛን ለማዳን ብሎ ራቁትን መሰቀልን ናቀው። በፈጠራቸው ፍጥረታት ተተፋበት። እኛን ትእግስት ሊያስተምረን እነርሱን ማጥፋት እየቻለ እርሱ ግን በፍቅር እያየ የሚያደርጉትን አያውቁምና አባት ሆይ ይቅር በላቸው ይል ነበርክርስቶስ እኛን ለማዳን ሲሰድቡት አልተሳደበም ሲንቁት አልናቃቸውም ሲታበዩበት ሁሉ እርሱ ግን በትሕትና ያያቸው ነበር። ታድያ እኛ ደግሞ ራሳችንን ለማዳን ሰዎች ሲንቁን ሲሰድቡን ሲታበዩብን በፍቅር በዝምታ ማለፍ ይጠበቅብናል። ይህን ካደረግን የክርስቶስ ደቀመዝሙር እንባላለን።

"ሳይኖረን በክብር የሚያኖረን የድንግል ማርያም ልጅ ቸሩ መድኃኔዓለም ነው። ቸሩ መድኃኔዓለም ጥበቃው ማዳኑ በረከቱ አይለየን በእውነት ♥

🌹በቀኙ ያኑረን የዓለሙ ቤዛ🙏❤    
      


🤍 ጥያቄ 1. አንቀፀ ብርሃን የተሰኘውን የእመቤታችን የምስጋና ፀሎት የደረሰው ማን ነው? @Maryam_Maryam2127
Poll
  •   ሀ// ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
  •   ለ// ቅዱስ ደቅስዮስ
  •   ሐ// ኢትዮጲያዊው ቅዱስ ያሬድ
  •   መ// ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
  •   ሠ// መልስ የለም
6 votes


✞ #ታህሳስ_ወር_የንግስ_በዓላት ✞

ማክሰኞ ታህሳስ 1 - የነብዩ ኤልያስ ልደቱ - በእንጦጦ እና በጎፋ ገብርኤል

ሐሙስ ታህሳስ 3 - ባዕታ ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ቀን
                      -ቅዱስ ፋኑኤል - በዓለም ባንክ              
_በአያት መሪ ቅዱስ ፋኑኤል
      
                      -ዜና ማርቆስ - በጣፎ

እሁድ ታህሳስ 6 - ቅድስት አርሴማ ቅዳሴ ቤቷ - የቅድስት አርሴማ ታቦት ባለበት

ማክሰኞ ታህሳስ 8 - አባ ኪሮስ ልደታቸው - አለምባንክ ጀሞ ተራራ መድኃኔዓለም ቤ/ክ - በጣፎ

ረቡዕ 9 - እስትንፋሰ ክርስቶስ ልደታቸው - በቦሌ ቡልቡላ ዋሻ ተክለሃይማኖት

አርብ 11 - ቅዱስ ያሬድ - ጎተራ አጎና ሲኒማ ፊት ለፊት

ቅዳሜ ታህሳስ 12 - አባ ሳሙኤል እረፍታቸው - በአቃቂ አባ ሳሙኤል ቤተ ደናግል ገዳም ፣ በቦሌ ቡልቡላ አባ ሳሙኤል እና በሲኤሚሲ ሚካኤል

እሁድ ታህሳስ 13 - ቅዱስ ሩፋኤል ቅዳሴ ቤቱ - በሸጎሌ

ረቡዕ ታህሳስ 16 - ፍቅርተ ክርስቶስ ቃልኪዳን የተቀበለችበት እለት - በአንቆርጫ መድኃኔዓለም ከፈርንሳይ ጉራራ ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ጋር ባጃጅ እና ታክሲ አለ የአንቆርጫ

ቅዳሜ ታህሳስ 19 - ቅዱስ ገብርኤል - ሶስቱን ህፃናት ያዳነበት

ማክሰኞ ታህሳስ 22 - ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና እደምትወልድ ያበሰረበት - በብስራተ ገብርኤል

ሐሙስ ታህሳስ 24 - አቡነ ተክለሃይማኖት - ልደታቸው

ሰኞ ታህሳስ 28 - ቅዱስ አማኑኤል - የልደቱ መታሰቢያ - በመሳለሚያ

ማክሰኞ ታህሳስ 29 - ባለወልድ - የኢየሱስ ክርስቶስ የልደቱ መታሰቢያ በዓል - በ4 ኪሎ ባለወልድ ቤተክርስቲያን - በለቡ መብራት አብርሃም ገዳም

✞ መምጣት የማትችሉ በማድረግ የበረከቱ ተካፋይ ይሁኑ ✞

      


❷❼ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ❣️
--------------------------------------




አሻግረህኛል ያንን ዘመን
አሻግረህኛል ያን ክፉ ቀን
ጉልበቴ አንተ ነህ ለዘላለም
ተመስገንልኝ መድኃኔ ዓለም ❣️






❤️🌹❤️...........❷❼🕯


“ወዳጄ ሆይ! የትዕቢት መርዝ ተጠራቅሞ አብጦብሃልን? እንኪያስ ወደ ቅዱስ ሥጋዉና ክቡር ደሙ ቅረብ፤ ስለ ወዳጆቹ ሲል አርአያ ገብርን የነሣ ትሑቱ ጌታም ትሕትናን ያስተምርሃል፡፡ የስግብግብነት ትኩሳት አስቸግሮሃልን? ወደ ቅዱስ ሥጋዉና ክቡር ደሙ ቅረብ፤ ደግነትንም ትማራለህ፡፡ የምቀኝነት ብርድ አስቸግሮሃልን? እንኪያስ ወደ ሰማያዊው መዓድ ቅረብ፤ ምህረት ማድረግንም ገንዘብ ታደርጋለህ፡፡ ትዕግሥትን የማጣት እከክ ይዞሃልን? እንኪያስ ወደ ቅዱስ ሥጋዉና ክቡር ደሙ ቅረብ፤ ራስን መግዛትንም ገንዘብ ታደርጋለህ፡፡ በመንፈሳዊ ሕይወትህ ልል ዘሊል ብትሆን ይህን መንፈሳዊ መዓድ ተመገብና ብርቱ ትሆናለህ፡፡ ቆሽሸሃልን? እንኪያስ ወደዚሁ መብልና መጠጥ ቅረብ ብዬ እመክርሃለሁ፤ ንጽሕናንም ገንዘብ ታደርጋለህ፡፡”

ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ


🫵 ኪስህን ብቻ ካየህ ተሰፋ ትቆርጣለህ!!

ያጣኸዉን ነገር ብቻ ከቆጠርክ አዎ ፀሎት ታቋርጣለህ።
የጎደለብህን ነገር ብቻ የምትደምር ከሆነ ለቤተክርስቲያን ለቅዱስ እግዚአብሔር ጀርባህን ትሰጣለህ።

ጥለዉህ የሄዱትን ሰዎች ብቻ የምታይ ከሆነ ልዑል እግዚአብሔርን ትሳደባለህ ታማለህ።

እይታዉ ነዉ የሚወሰነዉ
ከጎደለህ ይልቅ የበዛብህን ማየት ስትችል ግን፡- ከጠፋዉ ነገር በላይ የጠፋዉን እጥፍ አድርጎ ሊሰጥህ የሚችለዉን አምላክ ማየት ብትችል ግን ያን ጊዜ ማመስገን ትጀምራለህ።🙏🏻🤎

✍ ምንጭ፦
ከመምህር ኢዮብ ይመኑ ትምህርት የተወሰደ


💙#ስለማዕተብ ትንሽ እንማማር

#ማዕተብ
👉ማዕተብ ማለት ምልክት ማለት ነው ለተጠመቁ ክርስቲያኖች ሁሉ የክርስትና ሃይማኖት መታወቂያ ፣ ምልክት፣አርማ ነው።

#በኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ዘንድ ማዕተብ የተጀመረው በሃይማኖተ አበው በድርሳነ ያዕቆብ መረጃ መሠረት ከልደተ ክርስቶስ በኋላ #በአምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን #በእስክንድርያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስተያን ሊቀጳጳስ በነበረው #ያዕቆብ ዘእልበረዲ ነው፡፡

መስቀል በክር በአንገት ላይ ማሰር የክርስቲያኖች
#መለያ ሆኖ አንገትን ለሰይፍ ፣ ለመከራ እሰጣለሁ ማለት ነው።

#ዘዳ 68            #ምሳ 6፥20
#ማቴ 10፥38      #ማር 10፥2
#ሉቃ 14፥27

ግሩፑን ለመቀላቀል

@Orthodox_temhrt_Group

ቻናሉን ለመቀላቀል
@Orthodox_temhrt
@KEDEST1HOY1LEMGNILN


🔔አዲስ_ዝማሬ

🎙|ስማኝ አምላኬ |🥹

🎤ዘማሪ ዲያቆን ፍሬዘር ደሳለኝ

💒✞ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ትምህርቶች✞💒

@Orthodox_temhrt
@Orthodox_temhrt
@Orthodox_temhrt
         👆 ይቀላቀሉን  👆

New Ethiopian Orthodox Mezmur 2024

💚💛❤️


ሰላም እንደምን ቆያችሁ
❤️❤️ማስታወቂያ ❤️❤️❤️

ማገልገል ማገዝ የምትፈልጉ ካላቹ ባላችሁ አቅም መርዳት ለምትፈልጉ  post በማረግም ሆነ ፅሁፎች ግጥሞች መዝሙሮችን በመዘመር በመልቀቅ የምትተባበሩን ካላችሁ መልክ እናግዛቹ የምትሉ ከታች ባለው ሊንክ ያናግሩን
  አናግሩን 👇👇👇
@Elshio_owner


የገና /ልደት በዓል መዝሙሮች ስብስብ የምትፈልጉ እንሆ የ 1 ሰዓት ከ 5 ደቂቃ መዝሙር ስብስብ❤️


ሼር ያድርጉ🤗
https://t.me/Dnglmaryamn21


የአእላፋት ዝማሬ ነው በደንብ አጥኑት 😊👆


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ይኸው (እሰይ) ተወለደ

#Share


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ቸርነትህ ብዙ
ምሕረትህ ብዙ !

#Share


ታላላቅ ሥራን አድርጎልኛልና✝ 
                                                  

       
     በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ



❤️


Forward from: ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ
ፆመ ፍልሰታ

እንኳን በሰላም አደረሳችሁ


የሰውነት ሕዋሳት

ግእዝ                       አማረኛ

ገጽ            ግንባር  ፊት
ቅርንብ        ቅንድብ
አይን           አይን
እዝን            ጆሮ
አንፍ           አፍንጫ
ከንፈር        ከንፈር
አፍ            አፍ
ልሳን          ምላስ
ጉርኤ         ጉሮሮ
መትከፍ       ትከሻ
ክሳድ          አንገት
እድ              እጅ
መዝራእት      መዳፍ
አጽባእት       ጣት
ጥብእ          ጡት
ገቦ              ጎን
ልብ              ልብ
ሕሊና           ሐሳብ
እግር           እግር
ብርክ          ጉልበት
አጽም          አጥንት
ሰኮና           ተረከዝ
ሥን            ደም ግባት
ሐፍ             ወዝ
ስእርት         ጸጉር
ጽፍር           ጥፍር
ከርስ           ሆድ
እንግድአ      ደረት


#ይህንን_ያውቃሉ

የሦስቱ ዲያቆናት ምሳሌነት ምንድን ነው ?

ቅዳሴ ላይ እንደሚታወቀው ልዑካኑ  ከሁለት እስከ ሃያ አራት ድርስ ሊደርሱ ይችላሉ

አምስቱ ልዑካን  ማለት ሁለት ካህን ሦስት ዲያቆናት በአጠቃላይ የአምስቱ አማዕደ ምሥጢራት ምሳሌ ናቸው

ሦስቱ ዲያቆናት የየራሳቸው ምሳሌነት አላቸው

1. የዋና ዲያቆን (ሠራዒ )

ይህ ዲያቆን የቅዱስ እስጢፋኖስ ምሳሌ ነው

መጾር ወይም መስቀል ይዟ መቀደሱ ቅዱስ እስጢፋኖስ የተቀበለውን ሰማዕትነት ለማሰብ ነው

2. ተጨማሪ (ንፍቅ )

ዲያቆን ይህ ዲያቆን ደግሞ መጥመቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ ምሳሌ ነው

ከፊት ከፊት እየቀደመ  ካህናቱን መምራቱ ሊቀ ካህናት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከፊት ቀድሞ መጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ጥርጊያውን መንገድን የማዘጋጀቱ

ይህ ዲያቆን መብራት ወይም ጠፋፍ የሚያዙ ከመስዋዕት ከማቅርብ አልፎ በዚህ ይመሰላል

3. ፍሬ ሰሞን (መጽሐፍ ገላጽ )

  ይህ ዲያቆን የሐዋርያት አባቶቻችን ምሳሌ ነው እንዴት ቢሉ መጽሐፍ ይዞ በአራቱም አቅጣጫ ይዞራል ይህም
ሐዋርያት በአራቱ አቅጣጫ ወንጌልን የመስበካቸው ምሳሌ ነው።
https://t.me/tmhrtegeeze


"ወደ ቤተክርስቲያን ወጥተህ እግዚአብሔርን እንደ አምላክነቱ እንደሚገባ አምልከህ ከዚያ በኋላ ወደ ስራህ ብትሔድ የምትሠራው ሥራ የተባረከና የሠመረ እንደሚሆንልህ አታውቅምን?"
  
       
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ


የንጉስ ጭካኔ ፥ ክንዱ ቢበረታ፤
ለጣዖት ሳንሰግድ፥ እኛ ሳንረታ፡፡
የምናምነው አምላክ፥ ሊያድነን ወደደ፤
ገብርኤል መጣና፥  እሳቱ በረደ፡፡

ፍላፃና ሠይፉን፥ አጠፈው መላኩ፤
ሰላም ይዞ መጣ፥ ባለም ለታወኩ፡፡
አትጠራጠሩ፥ ምልጃው ያስምረናል፤
የሚነደው እሳት፥ ሳይነካን ወተናል፡፡

የሰልስቱ ደቂቅ፥ የእጠሉጣ ብርታት፤
የድንግል አብሳሪ፥ የቂርቆስ ረዳት፡፡
በሚመጣው አለም፥ እንዳይበላኝ እሳት፤
አማልደኝ ከጌታ፥ ነፍሴን እንዲምራት፡፡

የነገርኩህ ሁሉ፥ በቀኑ ደረሰ ፤
በዘብር ገብርኤል፥ እንባዬ ታበሰ፡፡
ና ልጄ ስትለኝ፥ አልልህም እንቢ፤
ስለቴን ተቀበል፥ አባቴ ቁልቢ፡፡

የልቤን ነግሬህ፥ የቁልቢው ገብርኤል፤
ሳትረሳ ፈፀምከው፥ ስለቴን  ተቀበል፡፡
ለንግስ እንመጣለን፥ አንተ አትረሳምና፤
ደሞ የዛሬ አመት፥ አድርሰን በደህና፡፡
+++++++

እንኳን ለሃያሉ ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሳችሁ
https://t.me/KEDEST1HOY1LEMGNILN

20 last posts shown.