የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ National Election Board of Ethiopia


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


NEBE

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሴቶችን ያማከለ የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ እና የባለድርሻ አካላት ሚናን አስመልክቶ የምክክር መድረክ አካሄደ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መጋቢት 6 ቀን 2013 ዓ.ም. ሴቶችን ያማከለ የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ እና የባድርሻ አካላት ሚናን አስመልክቶ ከፖለቲካ ፓርቲዎችና ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ። መድረኩን የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ውብሸት አየለ በንግግር የከፈቱት ሲሆን፤ ሰብሳቢው በንግግራቸው ያለፉት 30 ዓመታት የሴቶችን የፖለቲካ ተሣትፎ ምን እንደሚመስል ገልጸው ያለውን መሻሻል ጥናቶችን ጠቅሰው አብራርተዋል። መሻሻል ቢኖርም እንኳን ከሚፈለገውና ሊሆን ከሚገባው አንጻር እጅግ ብዙ እንደሚቀር አክለው ገልጸዋል።
የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢን ንግግር ተከትሎ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንን ጥናት ያጠኑት አቶ ኤልያስ ዓሊ በፖለቲካና በምርጫ ሂደቶች የሚሣተፉ ሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ዙሪያ ጥናታዊ ጽሑፍ ሲያቀርቡ፤ ከሥርዓተ-ፆታ ኦዲት ሪፖርት በኋላ ስለተገኙ መረጃዎች እንዲሁም የሴት ፓርቲ አባላት እና ዕጩዎችን አስመልክቶ የተሰጡ ምክረ ሃሳቦች የተመለከተ ጽሑፍ ደግሞ የቦርዱ የሥርዓተ-ፆታ እና አካታችነት ኃላፊ የሆኑት መድኃኒት ለገሠ አማካኝነት ቀርቧል። https://www.facebook.com/414693405979601/posts/905011086947828/


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለመራጮች ት/ት ፍቃድ ከተሰጣቸው ሲቪክ ማኅበራት ጋር ሁለተኛ ዙር ውይይት አደረገ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለመራጮች ትምህርት ፍቃድ ከተሰጣቸው የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ጋር ሁለተኛ ዙር የውይይት መድረክ አካሄደ። በቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ውብሸት አየለ የተከፈተው መድክ በተከታታይ ለሁለት ቀናት የተካሄደ ሲሆን መጋቢት 3 ቀን 2013 ዓ.ም. ተጠናቋል። በመጀመሪያ ቀን የተደረገው የውይይት መድርክ የመራጮች ት/ት ፍቃድ አሰጣጥ እና የሥነ-ምግባር መመሪያ ቁጥር 4/2012 ላይ የሠፈሩትን መሠረታዊ ደንቦች ከሲቪክ ማኅበራት ኃላፊነት አንጻር በቦርዱ አመራር አባል አበራ ደገፋ (ዶ/ር) ሲቀርብ፤ በመራጮች ት/ት ወቅት መካተት ያለባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች፣ ለሲቪክ ማኅብራት የተዘጋጀ ማስታወሻ፣ ሪፖርት ማድረጊያ ቅጽ እንዲሁም የሥነ-ምግባር ደንቡን የተመለከቱ ጉዳዮች በቦርዱ የሲቪክና የመራጮች ትምህርት ክፍል ባልደረቦች አማካኝነት ተብራርቷል። የመራጮች ት/ት አሰጣጥ ላይ የኮቪድ 19 መመሪያ እና የሥነ-ምግባር ድንብን ማስተዋወቅ ሌላው የመጀመሪያው ቀን ውይይት አጀንዳ ሲሆን በቦርዱ የኮቪድ 19 አስተባባሪ አማካኝነት ማብራሪያ ተሰጥቶበታል። ማብራሪያዎቹን ተከትሎ ከተሣታፊዎች ለቀረቡት አስተያየቶች በቦርድ አመራሩ አበራ ደገፉ (ዶ/ር) እንዲሁም በቦርዱ የሥራ ክፍሎች መልስ ተሰጥቶባቸዋል።
አካታች የሆነ የመራጮች ት/ት አስፈላጊነት፤ ከሥልጠናው የሚጠበቁ ውጤቶች እና ምርጫውን አካታች ለማድረግ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች በሁለተኛው ቀን የውይይት መድረክ ላይ ትኩረት ከተደረገባቸው አጀንዳዎች ውስጥ ሲሆኑ፤ https://www.facebook.com/414693405979601/posts/904395063676097/


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለደ/ብ/ብ/ህ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን የጻፈው ደብዳቤ


የእጩዎች ምዝገባን መጠናቀቅ አስመልክቶ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ
መጋቢት 02 ቀን 2013 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ በሰሌዳው ላይ የተጠቀሱ ተግባራትን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመመካከር ሲተገብር ቆይቷል። ከዚህም ውስጥ ዋናው እና ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር የተገናኘው የምርጫ ምልክት መረጣ እና እጩዎች ምዝገባ ነው።
ሁሉም ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ፓርቲዎች በራሳቸው ወይም በፈጠሩት ትብብር/ህብረት አማካኝነት 53 ፓርቲዎች 49 (አርባ ዘጠኝ) የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶችን ወስደዋል።
1. የእጩዎች ምዝገባ ቀናት
የመጀመሪያ ዙር የካቲት 08-21 ለአራት ቀን የተራዘመ (አ.አ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ቤኒሻንጉል ፣ጋምቤላ፣ ኦሮሚያ (ከምእራብ ወለጋ፣ ከምስራቅ ወለጋ፣ ከቄለም ወለጋ እና ሆሮጉድሩ ውጪ)
ሁለተኛ ዙር የካቲት15- 26 ለተጨማሪ አራት ቀናት የተራዘመ (በአማራ፣ በሶማሌ፣ በአፋር፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች እና በሲዳማ ክልሎች) የተከናወኑ ሲሆን የእጩዎች ምዝገባ በአጠቃላይ ለ22 ቀናት በ673 የምርጫ ክልልሎች ላይ ሲፈጸም ቆይቷል። በዚህም ወቅት የተለያዩ ሂደቱን ያጓተቱ ዋና ዋና ችግሮች ያጋጠሙ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ
• የምርጫ ቁሳቁስ ለማጓጓዝ የትራንስፓርት ትብብር ማነስ
• የምርጫ ክልል ጽ/ቤት ስራው ከተጀመረ በሁዋላም ቢሆን ቢሮዎች እና ቁሳቁስ ማዘጋጃ ቦታዎች ሳይዘጋጅ በመቅረቱ መዘግየት እና የአስፈጻሚዎች መንገላታት
• አስቀድሞም ግጭቶች የነበሩባቸው ቦታዎች ልዩ የሆነ የቁሳቁስ እንቅስቃሴም ሆነ ዝግጅት ማስፈለጉ እና ጊዜ መውሰዱ (ቤኒሻንጉል መተከል ዞን፣ ኦሮሚያ ... https://www.facebook.com/414693405979601/posts/902441553871448/


በምርጫ ሂደት ላይ እየተሳተፋችሁ ላላችሁ የፓለቲካ ፓርቲዎች የተደረገ ጥሪ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛ አጠቃላይ ምርጫን የተሻለ ግልጽነት እና ተአማኒነት አንዲኖረው ለማድረግ የተለያዩ ጥረቶች ሲያደርግ እንደቆየ ይታወሳል። ከዚህም መካከል ለፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ አስፈጻሚዎችን ዝርዝር በመስጠት የገለልተኝነት ማጣራት እንዲያከናውኑ እና ለቦርዱ እንዲያሳወቁ ማድረግ አንዱ ነው።

በዚህ መሰረት ከዚህ በፊት በተለያዩ ዙሮች የምርጫ አስፈጻሚዎችን ዝርዝር ለፖለቲካ ፓርቲዎች እንዳቀረበ ይታወሳል፣ በመሆኑም በአሁኑ ወቅት ቦርዱ በተለያየ መልኩ የመለመላቸው እና ለመራጮች ምዝገባ ተግባር ላይ ሊሳተፉ የሚችሉ አስፈጻሚዎች ዝርዝርን አዘጋጅቷል። በመሆኑም ፓርቲዎች ከቦርዱ የተሰጣችሁን ፍላሽ ይዛችሁ በመምጣት ከፖለቲካ ፓርቲዎች የስራ ክፍል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የመራጮች ምዝገባ ከሚጀመርበት ቀን አስቀድሞ (እስከ መጋቢት 15) አስተያየታችሁን ለቦርዱ እንድታቀርቡ እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
መጋቢት 2 ቀን 2013 ዓ.ም


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ የጊዜ ሠሌዳ ከወጣበት ጊዜ አንሥቶ በልዩ ሁኔታ የተለያዩ መድረኮችን በማዘጋጀት የኦፕሬሽን ሥራዎችን ቅደም ተከተል በጠበቀ መልኩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በተለይም ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየመከረ መሆኑ ይታወቃል።

በጊዜ ሠሌዳው በተመለከተው ቅደም ተከተል መሠረት በመከናወን ላይ የነበረው የዕጩዎች ምዝገባ በትላንትናው ዕለት የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም. መጠናቀቁን ተከትሎ ቦርዱ በነገው ዕለት መጋቢት 02 ቀን 2013 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል። በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ብዙሃን መገናኛዎች ከቀኑ 8 ሰአት በደሳለኝ ሆቴል ተገኝታችሁ መዘገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
•በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የተመዘገበ ብዙኃን መገናኛ ተቋም መሆን
•የሚሰሩበትን ሚዲያ መታወቂያ ይዞ ለመዘገብ መምጣት
•ከአንድ ሚዲያ ሁለት ባለሞያዎች ብቻ መሳተፍ ይችላሉ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
መጋቢት 01 ቀን 2013 ዓ.ም


ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የእጩዎች ምዝገባን ከየካቲት 08 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በሁለት ዙሮች ሲያከናውን እንደነበር እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች ተጨማሪ ቀናት በመጨመር እና የፓርቲዎችን አቤቱታዎች በመፍታት ሲያከናውን ቆይቷል።
በዚህም መሰረት የእጩዎች ምዝገባ ትላንትና የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም በይፋ ተጠናቋል። በመሆኑም በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቢሮዎች ችግር የተነሳ በልዩ ሁኔታ የሚታይ ካልሆነ በስተቀር ለ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ የእጩዎች ምዝገባ መዘጋቱን እየገለጸ አጠቃላይ የጸደቁ የእጩዎች ዝርዝርን በቅርቡ ይፋ የሚያደርግ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
መጋቢት 01 ቀን 2013 ዓ.ም


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ኛውን አጠቃላይ ምርጫ ለመታዘብ ማመልከቻ ላስገቡ እና በመጀመሪያ ዙር ላለፉ ሀገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ሥልጠና ሰጠ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሁለት ቀናት ማለትም የካቲት 26 ቀን 2013 ዓ.ም. እና የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ.ም. 6ኛውን አጠቃላይ ምርጫ ለመታዘብ ማመልከቻ ላስገቡ እና በመጀመሪያ ዙር ላለፉ ሀገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ሥልጠና ሰጠ። በቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ውብሸት አየለ የተከፈተው መድረክ የተለያዩ ክፍሎች ያሉት ሲሆን፤ በቦርዱ የፕሮግራም ባለሙያ-የውጭ ግንኙነት ክፍል፣ በቦርዱ የሥርዓተ -ፆታ እና አካታችነት ክፍል እንዲሁም ዓለም ዐቀፍ ተሞክሮ ባላቸው ባለሙያ ቀርቧል። ሥልጠናውን ለምን መስጠት እንዳስፈለገ የተናገሩት የቦርድ አመራሯ ብዙወርቅ ከተተ፤ የተወሠኑት ሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ያስገቡት ሠነድ ላይ የዕቅድ አወጣጥና ዘዴ ክፍተት በመታየቱ እንደሆነ ገልጸዋል።

ለምን ምርጫ መታዘብ ያስፈልጋል፣ የምርጫ መታዘብ ዕሴቶችና ጥቅሞች፣ በምርጫ መታዘብ ወቅት የሚጠበቁ የሥነ-ምግባር ደንቦችና ኃላፊነቶች፣ አካታችነትን ያማከለ የምርጫ መታዘብ ሂደት፣ የምርጫ መታዘብ አቀራረብ ዘዴ ዓለም ዐቀፍ ተሞክሮዎች፤ ማለትም የምርጫ መታዘብ ስልት፣ ሪፖርቶችን ማደራጀት፣ የአካታችነት መርሆችን ተግባራዊ ማድረግ ከሥልጠናው ዋና ዋና አጀንዳዎች ውስጥ ሲሆኑ፤ የቀረበውን ሥልጠና የተመለከተ ውይይት ከተሣታፊዎች ጋር ተደርጎ የፕሮግራሙ ማብቂያ ሆኗል።


የሴቶች በምርጫ የመሳተፍ ህጋዊ መሰረቶች እና በፈቀዱት ሁኔታና መጠን በምርጫው ሂደት መሳተፍ እንዲሁም ድምፅ መስጠት እንዳይችሉ የሚከለክሏቸዉ ተግዳሮቶች ከብዙ በጥቂቱ


መልካም የዓለም ዐቀፍ ሴቶች ቀን!


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ስጋት ከግምት ውስጥ ያስገባ ምርጫ ለማከናወን እየሰራ ነው

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በነሐሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ሊካሄድ የነበረው 6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት ሊከናወን አለመቻሉ ይታወሳል። ቦርዱ በአሁኑ ወቅት በምርጫ ወቅት የኮቪድ-19 ስርጭትን በመከላከል ረገድ አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶችን ለማከናወን ይረዳ ዘንድ የኮቪድ-19 አስተባባሪ ቀጥሮ የተለያዩ ተግባራትን እየፈጸመ ነው።
ከእነዚህም ውስጥ በምርጫ ወቅት የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር አዘጋጅቶ ያጸደቀው መመሪያ አንዱ ሲሆን በዚህ መመሪያ ዙሪያ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር ተደጋጋሚ የጋራ ምክክር መድረክ አከናወኗል። ከዚህም በተጨማሪ የሰራቸው ስራዎች የሚከተሉት ናቸው።

1. ቦርዱ ባወጣው መመሪያ መሰረት ለመራጮች ትምህርት የሚያገለግል የኮቪድ- 19 መተላለፊያ እና መከላከያ መንገዶች፣ በሁሉም የምርጫ እንቅስቃሴዎች የሚተገበሩ የኮቪድ-19 ቅድመ ጥንቃቄ እርምጃዎች እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተግባር እና ኃላፊነቶችን የሚገልጽ ማኑዋል በማዘጋጀት የመራጮች ትምህርት መርሀ ግብር ውስጥ አካትቷል።

2. በዕጩዎች እና መራጮች ምዝገባ እና በድምጽ አሰጣጥ ሂደት ላይ የሚተገበሩ የኮቪድ-19 ቅድመ ጥንቃቄ እርምጃዎችን በዝርዝር በማስቀመጥ የምርጫ አስፈጻሚዎች የስልጠና ማኑዋሎች ላይ እንዲካተት ተደርጓል።

3. ለምርጫ ወቅት የሚያገለግሉ የኮቪድ-19 የግል መከላከያ ቁሳቁሶች ማለትም የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎች እና የእጅ ሳኒታይዘሮች ምርጫ ቦርድ ለሚያሰማራቸው አሰልጣኞች እና የምርጫ ክልል ጽ/ቤት እና የምርጫ ጣቢያ ምርጫ አስፈጻሚዎች ተደራሽ ለማድረግ ግዥዎችንም ፈጽሟል።

4. ለእጩዎች ምዝገባ ለተከፈቱት የምርጫ ክልል ጽ/ቤቶች፣ ለስልጠና ቦታዎች አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎች እና የእጅ ሳኒታይዘሮች አሰራጭቷል።

5. የኮቪድ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር መወሰድ ያለበትን ጥንቃቄ እና ስነምግባር ደንብ አዘጋጅቶ ተወዳዳሪ እጩዎች እንዲፈርሙት አድርጓል።

6. ከቦርዱ ጋር አብረው የሚሰሩ የመራጮች ትምህርት የሚያስተምሩ ሲቪል ማህበራት፣ ምርጫ ለመታዘብ የሚንቀሳቀሱ ታዛቢዎች፣ ጋዜጠኞች ሊያደርጉት የሚገባውን ጥንቃቄ እና ስነምግባር ደንብ በማዘጋጀት እየሰራ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምርጫ ወቅት የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን ሰፊ በሆነው የምርጫ ተግባር የሚንቀሳቀሱ አካላትም በፈረሙት የስነ ምግባር ደንብ እና ቦርዱ ባጸደቀው መመሪያ መሰረት መሆን እንዳለበት ያስገነዝባል።
https://bit.ly/30e9u0j

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ


ከአትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ክልል ጽኅህፈት ቤቶችን ጥበቃ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ 673 የምርጫ ክልሎችን በመክፈት የእጩዎች ምዝገባን እያከናወነ እንደሆነ ይታወሳል። ቦርዱ የእጩዎች ምዝገባን ለመጀመር የምርጫ ክልል ቢሮዎችን ዝግጅት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የተለያዩ ትብብሮችን ከክልል መንግስታት እና ከከተማ መስተዳድሮች ሲጠይቅ እንደነበር በአንዳንድ ክልሎች በትብብሮቹ መዘግየትም የተነሳ የእጩዎች ምዝገባ በሁለት ዙር እንዲያደርግ መገደዱ ይታወሳል። ከዚያም በተጨማሪ የትራንስፓርት ትብብሮች አስቸጋሪ ከመሆናቸው የተነሳ የተለያዩ የምርጫ ክልል ቢሮዎች መከፈትም ዘግይቶ የእጪዎች ምዝገባ ሊራዘም ችሏል።

የምርጫ ክልሎች ከተከፈቱም በኋላ ደህንነታቸውን የማስጠበቅ ሃላፊነት የክልል እና የከተማ መስተዳድሮች ነው። ቦርዱ በተለያየ ጊዜ የምርጫውን ደህንነት ለማስጠበቅ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይቶች እና ንግግሮቸን እያደረገ የቆየ ሲሆን በዚህም መሰረት አብዛኛው የምርጫ ክልሎች ጥበቃ ሊሟላላቸው ችሏል። ለዚህም ቦርዱ ከፍተኛ ምስጋናውን ያቀርባል።
ነገር ግን አሁንም ቢሆን
• በኦሮሚያ ክልል- 21 የምርጫ ክልሎች
• በሶማሌ ክልል- 31 የምርጫ ክልሎች
• አማራ ክልል- 40 የምርጫ ክልሎች
• በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል- 6 የምርጫ ክልሎች ጥበቃ አልተመደበላቸውም። በመሆኑም አስፈላጊውን የደህንነት ከለላ ከክልል መንግስታቱ እያገኙ አይደለም።
ስለዚህ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ክልሎች በአስቸኳይ ለቀሪ የምርጫ ክልል ቢሮዎች የጥበቃ ምደባ እንዲያከናውኑ ነገር ግን ይህ ሳይሆን ቀርቶ በጥበቃ ችግር ሊፈጠሩ የሚችሉ የምርጫ አፈጻጸም ችግሮች ክልል መስተዳድሮች እና የጸጥታ አካላት ሃላፊነቱን እንደሚወስዱ ያስገነዝባል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
የካቲት 25 ቀን 2013 ዓ.ም


ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የእጩዎች ምዝገባን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የእጩዎች ምዝገባን ሂደትን አስመልክቶ በተለያየ ወቅት የተለያዩ መረጃዎችን ሲያደርስ እንደነበር ይታወቃል። በተጨማሪም የእጩዎች ምዝገባን አስመልክቶ ሶስት የተለያዩ ምክክሮችን ከፓርቲዎች ጋር አከናውኗል::
በመሆኑም በመጀመሪያ ዙር እጩዎች ምዝገባ የተጀመረባቸው ክልልሎች/የከተማ መስተዳድሮች ማለትም
- በአዲስ አበባ
- በድሬዳዋ
- በኦሮሚያ
- በሃረሪ
- በጋምቤላ
- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ
የእጩዎች ምዝገባ በትላንትናው እለት ተጠናቋል።
የእጩዎች ምዝገባን ዘግይተው በጀመሩ ክልልሎች እና ቦታዎች ማለትም
- በአማራ
- በሶማሌ
- በአፋር
- በምእራብ እና ምስራቅ ወለጋ ዞን ኦሮሚያ፣
- በደ/ብ/ብ/ህ
- በሲዳማ
በመርሃ ግብሩ መሰረት ዛሬ የካቲት 26 ቀን 2013 ዓ.ም ሊጠናቀቅ እንደሚገባው ይታወቃል።
ነገር ግን በቢሮዎች መከፈት መዘግየት የተነሳ፣ እንዲሁም የትራንስፓርት እና ሌሎች እክሎችን እና የፓርቲዎች አቤቱታዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት በሁለተኛ ዙር የእጩዎች ምዝገባ እስከ የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ መራዘሙን እያሳወቅን ፓርቲዎች በተሰጡት ተጨማሪ ቀናት ውስጥ ምዝገባቸውን አንዲያጠናቅቁ እናሳስባለን

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
የካቲት 26 ቀን 2013 ዓ.ም


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ የዕጩዎች ምዝገባ ሂደትና የቴክኒክ ሥራዎችን የተመለከተ ውይይት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር አደረገ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ትላንትና የካቲት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. የ6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ የዕጩዎች ምዝገባ ሂደትና የቴክኒክ ሥራዎችን የተመለከተ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር መገናኛ ብዙኃን በተገኙበት ውይይት አድርጓል። የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ በተገኙበት የተደረገው ውይይት በዕጩዎች ምዝገባ ሂደት ላይ ያጋጠሙ የተለያዩ ግኝቶች የቀረቡበት ሲሆን፤ እስካሁን ባለው ሂደት የቀረቡ አቤቱታዎችና የተሰጡ መፍትሔዎች በዝርዝር በቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ቀርበዋል።
ከተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲዎች በመንግሥት ላይ አቤቱታዎች እንደቀረቡ በመጥቀስ ለገዥው ፓርቲ መመሪያ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ እንዳገኙት የገለጹት ሰብሳቢዋ፤ ገዥው ፓርቲ ከቀድሞ ልማዶች መላቀቅ እንደሚገባው ገልጸዋል። ፖለቲካ ፓርቲዎችም ማንኛውም ዕክል ሲገጥማቸው በሰዓቱ ለቦርዱ ቢያሳውቁ በጊዜ መልስ እየሰጡ ለመሄድ እንደሚያስችል በማሳሰብ፤ ፓርቲዎቹ ቦርዱ ካዘጋጀው የጥሪ ማዕከል በተጨማሪ ይቀለናል በሚሉት መንገድ አቤቱታቸውን ቢያቀርቡ ቦርዱ አፋጣኝ መልስ ለመስጠት ዝግጁ እንደሆነ ገልጸዋል። የቦርድ ሰብሳቢዋን ሀሳብ የተጋሩት ተሣታፊ ፖለቲካ ፓርቲዎቹ መፍትሔ አገኝተንባቸዋል ያሏቸውን አካባቢዎች በመግለጽ ያመሰገኑ ሲሆን፤ አሁንም ከፍተኛ ሥጋት አሉባቸው ያሏቸውን ቦታዎች በመግለጽ በእጩዎች ምዝገባ ወቅት ያጋጠማቸውን እና መፍትሄ የሚፈልጉ ጉዳዮችን፣ የምረጡኝ ዘመቻ ለማድረግ የሚያስቸግሩ ያሏቸውን ሁነቶች ... https://bit.ly/2PuMasR


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው አጠቃላይ ምርጫን ለማስፈጸም 140 ሺህ በላይ አስፈጻሚ ለመሆን የሚችሉ ሰዎቸን ምልመላ የሚያከናውንበት ሂደት በማጠናቀቅ የአስፈጻሚዎችን ፍቃደኝነትን፣ ገለልተኝነትን እና ብቃትን በማረጋገጥ ስራ ላይ አንደሆነ ይታወቃል።

ምርጫ አስፈጻሚዎች የምርጫ ሂደቱ ዋና አካል መሆናቸውን በመረዳት እና ስራውም ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቅ በመሆኑ እንዲሁም የምርጫ ሂደቱ ከተጀመረ በኋላ የሰው ሃይል እጥረት እነዳይፈጠር በማሰብ ተጨማሪ የሰው ሃይል ምልመላ ማከናወን እንዳለበት አምኗል።
በዚህም መሰረት
- ለምርጫ አስፈጻሚነት በገለልተኝነት አገራችሁን ለማገልገል የምትፈልጉ
- ምንም አይነት ፓርቲ አባልነት፣ የዝቅተኛ የአስተዳደር እርከኖች ላይ ሰርታችሁ የማታውቁ
- ከሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ውጪ በሌሎች የቀድሞ ምርጫ የማስፈጻም ተግባራት ላይ ተሳትፋችሁ የማታውቁ
- የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም ተመጣጣኝ ረጅም አመት የስራ ልምድ ያላችሁ
የሚከተለውን ፎርም በመጠቀም በሚቀጥሉት አራት ቀናት እስከ የካቲት 27 ድረስ ብቻ ማመልከት ትችላላችሁ።
የስራው ቆይታ ለ4 ወራት ሲሆን፣ የቀን አበል፣ አስፈላጊ የሆኑ ቦታዎች/ ሁኔታዎች ላይ ጥበቃ፣ እንዲሁም ስራውን ለማከናወን የሚያስፈልጉ ማንኛውንም ነገሮች ቦርዱ ያሟላል።
የስራ ልምድ ሰርተፍኬት፣ የድጋፍ ደብዳቤ በቦርዱ የሚሰጥ ይሆናል።
https://nebe.org.et/pworkers/

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
የካቲት 24 ቀን 2013 ዓ.ም


ጥሪ ለፖለቲካ ፓርቲዎች በሙሉ

የፖለቲካ ፓርቲዎች ለ6ተኛው አገራዊ ምርጫ እጩዎቻቸሁን እያስመዘገባችሁ እንደሆነ ይታወቃል። የእጩ ተወዳዳሪዎች ምዝገባ፣ የድጋፍ ፊርማ አሰባሰብ እና መለያ ምልክት አመራረጥ መመሪያ ቁጥር 07/2013 አንቀጽ 19 መሰረት እጩዎች ምዝገባ በምርጫ ክልል የሚከናወን ሲሆን የእጩዎች አጠቃላይ ዝርዝር ደሞ ለቦርዱ ይቀርባል።
በዚህም መሰረት የእጩዎች ዝርዝር መረጃን በእጩዎች ዝርዝር ማቅረቢያ ቅጽ በመጠቀም የምዝገባ የጊዜ ሰሌዳ ከመጠናቀቁ በፊት እንድታቀርቡ ቦርዱ ያሳሰባል።
ቅጹ ከቦርዱ ድረገጽ (ከስር በሚገኘው ሊንክ) እንዲሁም የፓለቲካ ፓርቲ የስራ ክፍል ማግኘት የሚቻል ሲሆን የሚከተሉትን ዝርዝሮች መያዝ አለበት።
• ተ.ቁ
• የእጩ ስም ከነአያት
• የእጩ ስራ
• የሚወዳደርበት/የምትወዳደርበት ክልል/የከተማ መስተዳድር
• የሚወዳደርበት/የምትወዳደርበት የምርጫ ክልል
• የሚወዳደርበት/የምትወዳደርበት የምርጫ አይነት
የእጩዎች ዝርዝር ሰነዱ የፓርቲውን ስም፣ የፓርቲውን ሃላፊ ስምና ፊርማ እንዲሁም የፓርቲውን ማህተም መያዝ ይኖርበታል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
የካቲት 22 ቀን 2013 ዓ.ም
https://bit.ly/2OaKfJk


የመራጮች ምዝገባን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳን አውጥቶ ተግባራትን እያከናወነ እንደሆነ ይታወቃል። ከዚህም መካከል በአሁኑ ወቅት እየተከናወነ ያለው የእጩዎች ምዝገባ አንዱ ሲሆን በጊዜ ሰሌዳው መሰረት ተከታዩ ዋና ተግባር የመራጮች ምዝገባን ማከናወን ነው።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ተግባራትን ማከናወን ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ካጋጠሙት ተግዳሮቶች መካከል  የምርጫ ክልል ቢሮዎች ዝግጅት መዘግየት እና አስፈጻሚዎች ሰልጥነው ከተሰማሩም በኃላ ቢሆን ቢሮዎች ዝግጁ ሆነው ባለመገኘታቸው የቢሮ መከፈት መዘግየቱ፣ በተወሰኑ ክልልሎች አስፈላጊው ቢሮዎች ተዘጋጅተው ባለማለቃቸው የእጩዎች ምዝገባ በጊዜ ሰሌዳው መሰረት መጀመር አለመቻሉ እና ለሁለት ዙር መከፈሉ፣ ለምርጫ ቁሳቁሶች ስርጭት የትራንስፖርት እጥረት እና የገለልተኛ አስፈጻሚዎች ምልመላ ሂደት ከፍተኛ ጥንቃቄ እና ጊዜ የሚወስድ ተግባር መሆኑ ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

በዚህም መሰረት ቦርዱ የእጩዎች ምዝገባ ሂደትን በመገምገም ተጨማሪ ቀናት እንደሚያስፈልገው በመረዳት በመጀመሪያ ዙር የእጩዎች ምዝገባ በተጀመረባቸው ክልሎች ለ4 ቀናት ያራዘመ ሲሆን፣ በሁለተኛ ዙር የእጩዎች ምዝገባ የተጀመረባቸው ክልሎችም ላይ የቢሮዎች ዝግጅት የመጀመሪያዎቹ ቀናት ላይ ችግር ሆኖ እንደነበር ተረድቷል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የገለልተኛ ምርጫ አስፈጻሚዎች ምልመላ ተግባርንም እያከናወነ እንደሆነ ይታወሳል፤ 140 ሺህ በላይ እጩ የምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚነት የሚሰሩ ግለሰቦችን አዘጋጅቶ ገለልተኝነት ማጣራትን እያከናወነ ሲሆን፣ ይህም ከተጠበቀው ጊዜ በላይ ሊወስድ ችሏል። በመሆኑም ከክልሎች የሚገኘው የቢሮዎች ትብብር በመዘግየቱ፣ የእጩዎች ምዝገባ ቀናት ከተጀመሩም በኋላ ዝግጁ ያልሆኑ የተወሰኑ ቢሮዎች የነበሩ በመሆኑ ፣ ፓለቲካ ፓርቲዎችም ተጨማሪ ቀናት በመጠየቃቸው እና የእጩዎች ምዝገባ በመራዘሙ፣ እንዲሁም በእጩዎች ምዝገባ ወቅት ያጋጠመው የቁሳቁስ ማጓጓዝ ተግዳሮቶች በመገምገም እና የእጩ አስፈጻሚዎችን ገለልተኝነት የማጣራት ስራን በተሻለ ጥራት ለማከናወን የመራጮች ምዝገባን ከተያዘለት ቀን የካቲት 22 ቀን 2013 ዓ.ም ወደ መጋቢት 16 ቀን 2013 እንዲዘዋወር ወስኗል።  

በመሆኑም የ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ከመጋቢት 16- ሚያዝያ 15 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ የሚከናወን ሲሆን ቦርዱ ለወደፊትም ከመራጮች ምዝገባ ጋር በተያያዘ ተጨማሪ መረጃዎችን የሚያቀርብ ይሆናል።  

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
የካቲት 22 ቀን 2013 ዓ.ም


የምርጫ ክርክር ለማዘጋጀት ፍላጎት ላላቸው የሲቪል ማህበራት እና ሚዲያዎች የተደረገ ጥሪ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ተግባራትን እያከናወነ እንደሆነ ይታወቃል፣ በዚህም መሰረት የተወሰኑ ተቋማት በተወዳዳሪዎች መካከል የምርጫ ክርክር ለማከናወን ከቦርዱ ፍቃድና አቅጣጫ ለማግኘት ጥያቄዎችን አቅርበዋል።

ይህንን እንዲሁም ሌሎች ልምዶችን መሰረት በማድረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የእጩዎች ምዝገባ ተጠናቆ ተወዳዳሪ ፓርቲዎች ከታወቁ በኋላ አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክርን ለማስተባበር ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በፊት ጥያቄ/ ማብራሪያ ያስገባችሁም ሆነ በዚሁ ጉዳይ ላይ ፍላጎት ያላችሁ መንግስታዊ ያልሆናችሁ ተቋማት እና ሚዲያዎች በተናጠል ወይም በጋራ የምርጫ ክርክር ዝርዝር የፍላጎት መግለጫ ወረቀት (Expression of interest) ለቦርዱ እንድታቀርቡ ጥሪ ያቀርባል።

የምክረሃሳቡ ማካተት የሚገባቸው ዋና ዋና ሃሳቦች
ማንኛውም የምርጫ ክርክር ለማከናወን የሚያስብ ተቋም የሚመለከቱትን ዋና ዋና ነገሮችን ያሟላ ምክረሃሳብ ሊያቀርብ ይገባል።
- ሊያከናውኑት ያቀዱት ክርክር ግልጽ አላማ
- ሊያከናውኑት ያቀዱት ክርክሩ የሚከናወንበት መንገድ (mode of engagement)
- ሊያከናውኑት ያቀዱት የክርክሩ ስነምግባር ደንብ (code of conduct)
- የክርክሩ ቁጥር ብዛት፣ የተሳታፊዎች ሁኔታ፣ ለህዝብ የሚቀርብበት ሁኔታ
- የአከራካሪ አመራረጥ ሂደት፣ መስፈርት እና መመዘኛ
- ክርክሩ ለህዝብ የሚቀርብበት መንገድ
- በጀት እና የገንዘብ ምንጭ
- ክርክሩን የሚከናወንባቸው ቋንቋዎች እና የመሳሰሉት
ከላይ ከተጠቀሱት ዋና ዋና ጉዳዮች በተጨማሪ ምክረሃሳብ የሚያስገቡ ተቋማት አስፈላጊ ነው የሚሉትን ዝርዝር እቅድ በምክረሃሳባቸው ውስጥ አካተው ማቅረብ ይችላሉ። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ክርክሩን በማመቻቸት ብሔራዊ ክርክር መከናወንን ከማመቻቸት በተጨማሪ ለክርክር ዝግጅት የሚሆን የፋይናንስ ድጋፍ አያደርግም።
የፍላጎት መግለጫ ወረቀት እስከ የካቲት 26 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ (በአምስት የስራ ቀናት ውስጥ) በቦርዱ ዋና መስሪያ ቤት በግንባር ወይም በ media@nebe.org.et ኢሜይል አድራሻ ሊቀርብ ይችላል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
የካቲት 21 ቀን 2013 ዓ.ም


ለፖለቲካ ፓርቲዎች በሙሉ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ አጭር መረጃ

1. የፓለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ክልል ቢሮዎችን አድራሻ ከነልዩ የቦታ መጠሪያ ስማቸው በዝርዝር ለማወቅ በጠየቃችሁት መሰረት ሁሉንም የምርጫ ክልሎች አድራሻ ከነልዩ መጠሪያ ቦታቸውን በዝርዝር በምርጫ ቦርድ ድህረ ገጽ ምርጫ ክልሎችና ጣቢያዎች ክፍል ሰር ይገኛሉ፡፡ ተጨማሪም ከቦርዱ ዋና መስሪያ ቤት የፖለቲካ ፓርቲዎቸ የስራ ክፍል በሶፍት ኮፒ ማግኘት የሚቻል መሆኑን እየገለጽን በድረ-ገጹ ላይ ለማየት የሚከተለውን ሊንክ ይከተሉ። https://nebe.org.et/am/polling-stations

2. የፖለቲካ ፓርቲዎች በእጩዎች ምዝገባ ወቅት እና የምረጡኝ ዘመቻ ወቅት ለሚያጋጥማችሁ ማንኛውም ተግዳሮቶች እና ለሚኖራችሁ አቤቱታ አፋጣኝ ምላሽ ለማግኘት በኢሜል አድራሻ political-parties@nebe.org.et ወይም ከቦርዱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስራ ክፍል በተሰጣችሁን የዋትሳፕ ወይም ቴሌግራም አድራሻ በኩል ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
የካቲት 18 ቀን 2013 ዓ.ም


ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ6ተኛው ጠቅላላ ምርጫ የእጩዎች ምዝገባን እያከናወነ እንደሆነ ይታወቃል። የእጬዎች ምዝገባ ሂደቱን በመገምገም እንዲሁም ከፓለቲካ ፓርቲዎች የሚቀርቡ አቤቱታዎችን በማገናዘብ ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታትም እየሰራ ነው። በመሆኑም በአዋጅ 1162/2011 እንዲሁም በእጩ ተወዳዳሪዎች ምዝገባ ድጋፍ ፊርማ አሰባሰብና የመለያ ምልክት አመራረጥ መመሪያ ቁጥር 7/2013 አንቀጽ 16(1) መሰረት የመንግስት ሰራተኛ እጩዎች ስራቸውን መልቀቅ ሳያስፈልጋቸው በእጩነት ለመወዳደር እንደሚችሉ ይደነግጋል። እንዲሁም እጩ ከሆኑ በኃላ በምርጫ ወቅት ያለደምወዝ ፈቃድ የማግኘት መብታቸውም በህግ የተሰጠ ነው።

ቦርዱ የእጩዎች ምዝገባን በሚያከናውንበት ወቅት በእጩ ተወዳዳሪዎች ምዝገባ ድጋፍ ፊርማ አሰባሰብና የመለያ ምልክት አመራረጥ መመሪያ ቁጥር 7/2013 አንቀጽ 16(2) ትርጉም ተዛብቶ በመወሰዱ የተለያዩ የምርጫ ክልሎች የመንግስት ሰራተኛ እጩዎችን ያለደምወዝ ፈቃድ የተወሰደበትን ሰነድ እንዲያቀርቡ መጠየቃቸውን ተረድቷል። በመሆኑም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የተፈጠረውን መምታታት ለመፍታት እጩ ተወዳዳሪዎች ምዝገባ ድጋፍ ፊርማ አሰባሰብና የመለያ ምልክት አመራረጥ መመሪያ ቁጥር 7/2013 አንቀጽ 16 (2) እንዲሰረዝ የወሰነ ሲሆን ይህንን ተከትሎ ማንኛውም እጩ ለመመዝገብ ያለደምወዝ ፍቃድ የማያስፈልገው መሆኑን አጽንኦት በመስጠት የዚህን የአሰራር ክፍተት ለመድፈን ለምርጫ ክልል ጽ/ቤት አስፈጻሚዎች ይኸው መልእክት እንዲተላለፍ የሚደረግ መሆኑን ቦርዱ ያሳውቃል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
የካቲት 18 ቀን 2013 ዓ.ም

20 last posts shown.

4 301

subscribers
Channel statistics