Ministry of Revenues -Medium Taxpayers Branch No2


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


This is official Telegram Channel of Ministry of Revenues Medium Taxpayers Branch No 2.
Join the channel.

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


*****************************

1/ ታክስ ከፋዩ በለውጥ ማሳወቂያ ቅጽ በማንዋል ወይም በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ በመሙላት ታክስ ለሚከፍልበት ቅ/ጽ/ቤት ለውጡ በተደረገ በ 30 ቀናት ውስጥ ማቅረብ አለበት፡፡

2/ የሚቀርብ የለወጥ ማስታወቂያ የ3ኛ ወገን ማረጋገጫ የሚያስፈልገው ከሆነ ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ማረጋገጫ ከተሞላው ቅጽ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡-https://tinyurl.com/3yx44e4t


ከተከፋይ ሂሳቦች ላይ ታክስ ቀንሶ የማስቀረት አስተዳደር (withholding tax) ስልጠና ተሰጠ
*************************
(ታህሳስ 14/2017ዓ.ም፡ መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁጥር 2 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)


ቀጥተኛ በሆኑ የታክስ ዓይነቶች ላይ ለ16ኛ ዙር ሰልጣኞች ሲሰጥ የነበረዉ የክፍል አንድ ስልጠና የተጠናቀቀ ሲሆን የዛሬው ስልጠና ከተከፋይ ሂሳቦች ላይ ታክስ ቀንሶ የማስቀረት አስተዳደር (withholding tax) የተመለከተ ነበር፡፡

ስልጣኞች በክፍል አንድ ስልጠናቸው ከመቀጠር የሚገኝ ግብር፣ የወጪ መጋራት አከፋፈል ሥርዓትን፣ ከንግድ ስራ የሚገኝ ገቢ ግብር፣ እንዲሁም የዛሬውን ስልጠና ከተከፋይ ሂሳቦች ላይ ታክስ ቀንሶ የማስቀረት አስተዳደር ስርዓት (withholding tax) በተመለከተ በሰፊው ስልጠና የተሰጠባቸው ርዕሰ ጉዳዮች ናቸው፡፡

የዛሬው ስልጠናው በወ/ሮ ካሰች አስራት የታክስ ከፋዮች ትምህርት መሪ ባለሙያ የተሰጠ ሲሆን ስለ ቅድመ ግብር ምንነትን እና ዓይነቶችን ፣ ግብር ቀንሰው ገቢ እንዲያደርጉ ግዴታ የተጣለባቸው ሰዎች/ ድርጅቶች መቼ፣ ከማን እና እንዴት ግብር ቀንሰው ገቢ ማድረግ እንደሚገባቸው ፣ግብር ቀንሶ የመያዝ ግዴታ የማይመለከታቸውን ሰዎች እና ግብይቶች ፣ ከተከፋይ ሂሳቦች ላይ ግብር ቀንሶ አለማስቀረት /ግዴታን/ አለመወጣት የሚያስከትለውን ውጤት በስልጠናው የተብራሩ ርዕሰ ጉዳዮች ናቸው፡፡


ግብር÷ ለሀገር ክብር!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ቴሌግራም፦ https://t.me/mormto2
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/info.mto2/
ኢሜል፡- mormto2taxeducation2023@gmail.com
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@ministryofRevenues-MTO2
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡




Video is unavailable for watching
Show in Telegram
***********************
1/ ማንኛውም ታክስ ከፋይ ከዚህ በታች የተመለከተው ለውጥ ሲያደርግ ለውጡ በተደረገ በ30 ቀናት ውስጥ ለሚኒስቴሩ በጽሁፍ ማሳወቅ አለበት፡፡

ሀ) በንግድ ድርጅቱ ስያሜ ላይ የተደረገ ለውጥ፣

ለ) በድርጅቱ ስም የተመዘገበ፣

(1) ቋሚ የንግድ ሥራ፣ የቢሮ እና የመኖሪያ አድራሻ ለውጥ፣

(2) በማምረቻ ቦታ ወይም ታክስ ከፋዩ በሚጠቀምበት መጋዘን ላይ የተደረገ የአድራሻ ለውጥ፣

(3) በፖስታ ወይም በመደበኛ እና በተንቀሳቃሽ ስልክ፣ ፋክስ ወይም ኢ-ሜይል አድራሻ ላይ የተደረገ ለውጥ፣

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡-https://tinyurl.com/28abheb4




ቀጥተኛ ያልሆኑ ታክሶች ላይ ገለፃ ተካሄደ
*************************************


(ታህሳስ 11/2017ዓ.ም፡ መካከለኛ ግብር ካፋዮች ቁጥር 2 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)

ቀጥተኛ ያልሆኑ ታክሶች ላይ ያተኮረውን የክፍል ሁለት ስልጠና ለርቀት ሰልጣኞች ለድርጅት ባለቤቶች፣ ስራ አስኪያጆች፣ ም./ስራ አስኪያጆች እና የሒሳብ ክፍል ኃላፊዎች በታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የስራ ሂደት በወ/ሮ ሀና ንጉሴ ገለፃ  ተሰጠ፡፡

የታክሶቹ ምንነት፣ አከፋፈል እና ምጣኔ፣ ታክሶቹ የሚከፈልባቸው አቅርቦቶች የሚከናወኑበት ቦታ፤ ጊዜ እና ዕሴት ላይ በቂ እውቀት ኖሯአቸው ሕግ እና ሥርዓቱን መሠረት በማድረግ ወቅቱን ጠብቀው ግብራቸውን አሳውቀው እንዲከፍሉ ማድረግ የገለፃው ዋና ዓላማ ነው፡፡

ሰልጣኞች ስልጠናቸውን በርቀት የሚከታተሉ እና የክፍል አንድ ስልጠና በአግባቡ ተከታትለው ያጠናቀቁ ሲሆን በቀጣይም የታክስ አስተዳደር ላይ የሚያተኩረውን የክፍል ሶስት ስልጠና ይወስዳሉ፡፡






ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ከዕቅድ በላይ ገቢ ሰበሰበ
*************************************
(ታህሳስ 10/2017ዓ.ም፡ መካከለኛ ግብር ካፋዮች ቁጥር 2 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በህዳር ወር አፈፃፀሙ እንደተመላከተው በወሩ ሊሰበስብ ካቀደው የገቢ ዕቅድ 107% መሰብሰብ መቻሉ ተገለፀ፡፡ ይህ የተገለፀው የህዳር ወር እና የአምስት ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማውን ከማኔጅመንት አባላቱ ጋር ባደረገበት ወቅት ነው፡፡

የውይይቱን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት አቶ ቶሉ ፊጤ እንደገለፁት በየጊዜው የሚሰበሰበው የገቢ ዕቅድ ከፍ እያለ መምጣቱን አና ይህ ማለት ደግሞ መንግስት በሚኒስቴር መስሪያቤቱ ላያ ያለው እምነት ከፍተኛ መሆኑን እና ሀገራዊ ወጪ በሀገራዊ ገቢ ለመሸፈን የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት ትልቁ ድርሻ የኛ ነው የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በአፈፃፀሙ እንደተመላከተው በህዳር ወር ቀጥተኛ ከሆኑ ታክሶች፣ ቀጥተኛ ካልሆኑ ታክሶች እና ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች ለመሰብሰብ እቅድ 1,731,682,915.42 ብር፣ ክንዉን 1,858,297,181.38ብር፣ አፈፃፀሙም 107.31% ሲሆን ከእቅድ በላይ 126,614,265.96 ብር መሰብሰብ የቻለ መሆኑን እና አጠቃላይ የአምስት ወራት አፈፃፀሙም 12,113,830,710.12ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 11,650,891,671.40 ብር መሰብሰብ የቻለ እና ይህም በመቶኛ ሲገለጽ 96.18% ይሆናል፡፡ የዕቅድ አፈፃፀሙ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የዕቅድና በጀት አፈፃፀም ቡድን አስተባባሪ ኮማንደር ሞላ ተሾመ ቀርቧል፡፡

በአፈፃፀሙ ዙሪያ የስራ ሂደቶች እና ቡድኖች አስተያየት እና ምላሾችን ሰፋ ባለ መንግድ የሰጡ ሲሆን የዘርፍ ም/ክ ስራአስኪያጆችም የየዘርፎቻቸውን የስራ አፈፃፀም ላይ ማብራሪያ በመስጠት በቀጣይ በጋራ ስራዎችን መስራት እና ገቢውን ከፍ ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

አቶ ቶሉ በማጠቃለያቸው በርካታ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ እና የቀጣይ የስራ አቅጣጫ ያስቀምጠው ሲሆን ወሩ የበጀት ዓመቱ ግማሽ ዓመት በመሆኑ ስራዎች ከበፊቱ ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው እና ግብር ከፋዩን በማክበር፣ ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት በመስጠት የታህሳስ ወር የስራ አፈፃፀምን የተሻለ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ግብር÷ ለሀገር ክብር!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ቴሌግራም፦ https://t.me/mormto2
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/info.mto2/
ኢሜል፡- mormto2taxeducation2023@gmail.com
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@ministryofRevenues-MTO2




የክፍል ሶስት ስልጠና ተጠናቀቀ
*************************
(ታህሳስ 10/2017ዓ.ም፡ መካከለኛ ግብር ካፋዮች ቁጥር 2 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)


ለ14ኛ እና 15ኛ ዙር ሰልጣኞች ሲሰጥ የነበረው የክፍል ሶስት ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡ ሰልጣኞች በክፍል ሶስት ስልጠና የታክስ አስተዳደር ላይ ያሉ የተለያዩ አዋጆች፣ መመሪያዎችና ደንቦችን በተመለከተ ስልጠና ወስደዋል፡፡

ታክስ ማሳወቅና የታክስ ቅጾች፣ የታክስ አስተዳደር እና የወንጀል ቅጣቶችና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በወ/ሮ ካሰች አስራት የታክስ ከፋዮች ትምህርት መሪ ባለሙያ ስልጠናው ተሰጥቷል፡፡

ሰልጣኞች በክፍል ሶስት ስልጠናቸው የታክስ ከፋይ ምዝገባ፣ ስረዛ እና ክሊራንስ አሰጣጥ፣ ስለ ደረሰኝ እና የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ፣ የታክስ ማስታወቂያዎችና ቅጾች፣ የታክስ ስሌቶችና ሌሎች ክፍያዎችን ስለመክፈል፣ የታክስ አስተዳደራዊ እና የወንጀል ቅጣቶች እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በዝርዝር ስልጠና የወሰዱ ሲሆን በታክስ አስተዳደር አዋጅ፣ ደንብ እና አዋጁን ለማስፈጸም በወጡ መመሪያዎች ዙሪያ ሰልጣኞች በቂ ግንዛቤ እንዲያገኙ ማድረግ የክፍል ሶስት ስልጠና ዋና ዓላማ ነበር፡፡

ግብር÷ ለሀገር ክብር!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ቴሌግራም፦ https://t.me/mormto2
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/info.mto2/
ኢሜል፡- mormto2taxeducation2023@gmail.com
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@ministryofRevenues-MTO2




ዳታዌርሀውስ እና አድቫንስድ ኤክሴል ላይ ስልጠና ተሰጠ
**************************
(ታህሳስ 8/2017 ዓ.ም፡ መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁጥር2 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)


ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ከተለያዩ የስራ ክፍሎች ለተውጣጡ ሰራተኞች ዳታዌርሀውስ (Data warehouse) እና አድቫንስድ ኤክሴል (Advanced Excel) ላይ ከ7/4/2017ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት የቆየ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡

ስልጠናው በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የሰው ሀይል አመራርና ልማት የሥራ ሂደት አዘጋጅነት በአቶ ዮሴፍ መለስ የታክስ ከፋዮች ስጋት ስራ አመራር ቡድን እና በወ/ሪት ፈትለ እሸቱ የስጋትና የህግ ተገዢነት ስትራቴጂ የሥራሂደት እየተሰጠ ይገኛል፡፡

አቶ አሰፋ ጐንፋ የሰው ሀብት ሥራ አመራርና ልማትሥራ ሂደት አስተባባሪ ባስተላለፉት የመክፈቻ ንግግር እንደገለፁት ስልጠናው የፍላጎት ዳሰሳን መሰረት በማድረግ በሰራተኛው ፍላት የተዘጋጀ መሆኑን አስታውቀው ሰልጣኞች ስልጠናውን በዲሲፒሊን በመከታተል ለስራቸው ተጨማሪ ግብዕት እንደሚሆናቸው ገልፀዋል፡፡

ወ/ሪት ሄለን አስፋው የስልጠና ምልመላ ከፍተኛ ባለሙያ ገለፃ ሰልጣኞች ከዚህ በፊት ስልጠናውን ያልወሰዱ ነገር ግን ከስራቸው ጋር ተያያዥነት ያለው ስልጠና በመሆኑ የሰራተኛውን አቅም መገንባት የስልጠናው ዋና ዓላማ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ አክለውም የሰራተኛውን የክህሎት ክፍተት በመሙላት ለገቢ አሰባሰቡ የተሻለ መደላደል እንደሚፈጥር አስገንዝበው ሰልጠናው በሁለት ዙሮች የሚሰጥ እና ይሄኛው የመጀመሪያው ዙር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡


ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ቴሌግራም፦ https://t.me/mormto2
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/info.mto2/
ኢሜል፡- mormto2taxeducation2023@gmail.com
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@ministryofRevenues-MTO2
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡



14 last posts shown.