ABRET PRO


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


የአብሬት
እንዲሁም የቃዲሪይ ሲልሲላ መንዙማዎችን
ከአካቢሮች የሰማናቸውን ቀሰሶች
እንዲሁም ከመሻኢኾቻችን ኪታቦች አንዳንድ ጠቃሚ ነገሮችን የምንማማርበት አጠቃላይ የሀድራ ስራዎችን ምንዘክርበት ቻናል ነው
@Abretpro

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


ትልቅ ሰውን የሚያውቀው ትልቅ ሰው ነው:: ፊቱን ወደ አህሉሏህ ያዞረለት አሏህ ኸይር የሻለት ሰው ነው::

ሲሆን ልጃቸው ሁን አለዛ ጦሌያቸው
ቀርበህ እንድታሸት ተቡልቅያቸው
ቀርበህ እንድትሰማ ተሹኩሹካቸው
ቀርበህ እንድበላ ከበሉት እሳቸው

ዛሬ የነብያችንﷺ ቤተሰብ የሆኑት የሞሮኮው ሸይኽ ሸይኽ ሙሐመድ ቢን አብዱልራሕማን አልማሊኪይ አልዓለዊይ አልመግሪብይ በሠይዲ ቤት ያደረጉት ዚያራ እጅግ ልዩና ውብ ነበር:: ለዚህ ያማረ ዚያራ መሳካት ሸይኽ ሸሪፍ የጨካ ሸይኽ ኸሊፋ ፣ ዑስታዝ አስለም ፣ ዑስታዝ ዐዲል ፣ ዑስታዝ ሙዘሚል ፣ ዑስታዝ ሸምሰዲን ፣ ዑስታዝ ሐቢብ ሌሎቹም ዑስታዞች ትልቅ ድርሻ እንደነበራቸው ሰምቻለው::

ሸይኹ ከሠይዲ ቤት ሲደርሱ በታላቅ ተዋዱዕ በዐደብ "ሠይዲ" "መውላዬ" እያሉ ነበር የገቡት አሉ:: ገብተውም ዝቅ ብለው ውስጥ እግራቸውን ስመው ነው የዘየሯቸው:: ሠይዲም በተዋዱዕ በታላቅ ክብር ተቀበሉዋቸው:: ውሎው እጅግ ያማረ ፣ ብዙ ጥቅም የነበረው ፣ በአደብ በሙሓባ የተሞላ ብዙ ጉድ የነበረው መጅሊስ ነበር::

የአብሬትይ አልሳኒ ሁለት መንዙማዎች "ሸራበል ሙሓባ" እና ስለ አሕለል በይት ብዙ የሚለው "ሠይዱል ኢስጢፋ" በሙነሺድ ፉአድ መልካ እና አብዱ ተቀሩ ፣ እንዲሁም ከመናቂብ ፣ ከሚስባህ ፣ ከመጅሙዕ በዑስታዞቹ ተቀራ ፣ ከሠይዲ መድሆችም "ሰላቱሏህ" የሚለው መድህ ተቀራ:: እሳቸውም ልክ መንዙማዎቹን ከዚህ በፊት እንደሚያውቁት ሆነው አሸቁ::

ሸይኹ ስለመደሁት መድህ ኢንሻአሏ እመለስበታለው::


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ከሞሮኮ የመጡ ትልቅ ሸይኽ(ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ዓብዱልራሕማን አልማሊኪይ አልዓለዊይ አልመግሪቢይ) ሸይኻችን ሸይኽ ሠይድ ሚቅባሰል ኑር ሐፊዘሁሏህን ለመዘየር ቤታቸው እየሄዱ መንገድ ላይ ለሠይዲ የገጠሙትን ግጥም(መድህ) በአጠገባቸው ሲያነቡላቸው♥️♥️♥️


የነብዩንﷺ ውልደት አሏህ ከፍ አድርጎ አክብሮታል:: አሏህ ለውልደታቸው የጀሃነም በሮች እንዲዘጉ የጀሃነሙን መላኢካ ማሊክን አዘዘው ፣ ለውልደታቸው ጀነት እንዲዘይን የጀነቱ መላይካ ሪድዋንን አዘዘው ፣ ለሺ አመታት ሲቀጣጠል የነበረው እሳት ለክብራቸው አጥፋው ፣ እብሊስ ተወገረ.... በነብዩﷺ ውልደት እጅግ ብዙ ብዙ ጉዳ ጉዶች ሆኑ

ነቢ ﷺ ቢወለዱ

አብሮ የመጣው ኑር አለሙን አበራ
በየኮረምታው ላይ ሀቲፉ ተጣራ
ተወለዱ እያለ የከውኑ ሙሽራ
መላይካውም ቆሞ እየተሰለፈ
በየኮረምታው ላይ ሀቲፉን አጠፈ
ተወለዱ ማለት ባገር ተረፈፈ
የምስራች ማለት እጀነት አለፈ
ማሊክ ታዘዘና አዛብ ተቆለፈ
ጅብሪል ታቀፈና በጀነቱ ሀር
ያዘውና ሄደ በሀዋ ሲበር
አግብቶ አስጠወፈው በጀነት ሀገር
ስንት አጃኢብ ታየ ለቁጥር የጠፋ
ሺ አመት የበራው እሳትም ጠፋ
እብሊስ ይሄድ ነበር ሰማይ እየወጣ
ወሬ እየሰረቀ ለሰዉ ሊያመጣ
ያንን እያወራ ተመንገድ ሊያወጣ
ነቢﷺ ቢገኙ ይሄን ሹመት አጣ


አሕመዴ

ወፉቲሓል ጂናኑ ወልዒጥሩ የተባሃሩ
#ሊመውሊዲ_ጧሃል ዓረቢዪል ሙጅተበል አምጀዴ

#ወለይለቲ _መውሊዲሂ ሪድዋኑ ሚን ረቢሃ
ወዓይኑ ጉፍራኒሂ ወሚስኪል ኺታሚል ሙተጀዲዴ

አሏሁመ ሰሌ አላ ሙሀመዴ አሕመዴ
አሏሁመ ሰሌ አላ ሙሀመዴ አልስአዴ


የዑለማእ ዚያራ ሳምንት
••••••••••••••••••••••

የሀበሻ ምድር ሀገረ ኢትዮጵያ ከምትታወቅበት ፀጋዎቿ አንዱ አንቱ የተባሉ የነቁ የበቁ ድንቅ የአላህ ባርያዎች መሻይኾች ሀገር መሆኗ ነው። ዑለማኦችን ማክበር፣ እውቃታቸውን መውረስ፣ ከነሱ ጋር አብሮ በመቀማመጥ በረካቸውን ማግኘት ታላቅ ሥጦታ ነው።

★ ስለ ዑለማእ ታላቅነት ቁርአን ሲመሰክር እንዲህ ይላል

√ «አላህን ከባሮቹ ውስጥ የሚፈሩት ዐዋቂዎቹ ብቻ ናቸው» [ፋጢር:28]
(إِنَّمَا يَخْشَى اللَّهَ مِنْ عِبَادِهِ الْعُلَمَاءُ)

√ «እነዚያ የሚያውቁና እነዚያ የማያውቁ ይስተካከላሉን?» በላቸው፡፡ የሚገነዘቡት ባለ አእምሮዎቹ ብቻ ናቸው፡፡ [ዙመር:9]

(قُلْ هَلْ يَسْتَوِي الَّذِينَ يَعْلَمُونَ وَالَّذِينَ لَا يَعْلَمُونَ ۗ إِنَّمَا يَتَذَكَّرُ أُولُو الْأَلْبَابِ)

√ «አላህ ከናንተ እነዚያን ያመኑትንና እነዚያንም ዕውቀትን የተሰጡትን በደረጃዎች ከፍ ያደርጋል» [አልሙጃደላ:11]

( يَرْفَعِ اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا مِنكُمْ وَالَّذِينَ أُوتُوا الْعِلْمَ دَرَجَاتٍ ۚ )

√ «እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ መልክተኛውንና ከእናንተም የስልጣን ባለቤቶችን (ዑለማኦችን) ታዘዙ» [ኒሳእ:59]

(يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَطِيعُوا اللَّهَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ وَأُولِي الْأَمْرِ مِنكُمْ ۖ )

★ አሽረፈል ኸልቅ የፍጥረቱ ዓይነታ ረሱል ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ስለ ዑለማእ ክብር እንዲህ ይነግሩናል

√ "እውቀት ፍለጋ ከቤቱ ለወጣ ሰው የጀነትን መንገድ አላህ ያገራለታል። ለእውቀት ፈላጊ መላእክት ክንፋቸውን ያነጥፋለታል። በሰባት ሰማይ በሰባት ምድር ያለው ፍጥረት ሁሉ በባህር ውስጥ ያለ ዓሳ ሳይቀር ለአንድ ዓሊም ምህረትን ይለምናሉ። አንድ ዓሊም ከተርታው ህዝብ ያለው ብልጫ ጨረቃ ከዋክብትን የምትበልጠውን ያህል ነው። ዑለማእ የነብያት ወራሽ ናቸው፣ ነብያት እውቀትን እንጂ ዲናርና ዲርሃምን አላወረሱም፣ ይህን እውቀት የሸመተ ትልቅ እጣ አገኘ።" ( አቢዳውድ ቲርሚዚይ)

فعن أبي الدرداء - رضي الله عنه -قال: سمعتُ رسول الله - صلى الله عليه وسلم - يقول: ((من سلك طريقًا يلتمس فيه علمًا، سَهَّل الله له طريقًا إلى الجنة، وإن الملائكة لَتضعُ أجنحتَها لطالب العلم؛ رضًا بما يصنع، وإن العالم لَيستغفرُ له مَن في السموات ومن في الأرض، حتى الحيتانُ في الماء، وفضلُ العالم على العابد كفضلِ القمر على سائر الكواكب، وإن العلماء ورثةُ الأنبياء، وإن الأنبياء لم يورِّثوا دينارًا ولا درهمًا؛ وإنما ورَّثوا العلم، فمن أخذه، أخذ بحظٍّ وافر))؛ رواه أبو داود والترمذي،

√ "በረካ ልቅና ያለው ከትላልቆቻቹህ ጋር ነው" (ጦበራኒ፣ ሐኪም)

وعن ابن عباس أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال: البركة مع أكابركم. رواه الطبراني والحاكم، وقال صحيح على شرط مسلم

የነገው እሁድ ዑለማኦቻችንን ምንዘይርበት ሳምንት ነው። የአሽረፈል ኸልቅን መውሊድን ስናስብ ወራሾቻቸው ዑለማኦች ቀዳሚውን ሥፍራ ይይዛሉ። በመውሊድ ረሱልን ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ማስታወስ ማላቅ ከፍ ማድረግና ማፍቀር፣ የኢስላምን መልእክት ለዘነጉት ማድረስ፣ ማህበረሰብን በጥበብ ማስተማር፣ መንፈሳዊ እሴትን መፍጠር የቻሉት መሻይኾች ናቸው። ከእነሱ ጋር መቀማመጥ የዲንም የዱንያም የአኼራም ሃሳብ መለዋወጥ በቸገራቸው ነገር አብሽሩ ከጎናችሁ አለን ብሎ ደጀን መሆን ታላቅ እመርታ በመሆኑ የነገውን እሁድ በአካባቢያችን የሚገኙ ዑለማኦችን እና ታላላቅ ሽማግሌዎችን በመዘየር እንድናሳልፈውና የመውሊድን ማህበራዊ እሴት ከፍ እንድናደርገው ጥሪያችንን እናቀርባለን።

የአዲስ አበባ ሙስሊም ወጣቶች ማሕበር


ከአብሬትይ አልሳኒ የመውሊድ ኪታብ አልዱረሩል መዓኒ የተቀነጨበ
(درر المعاني في مولد النبي ﷺ)
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
🌞
ወኩሉል ሙዐዘሚ ወልሲሩል ሙፈኸሚ
ወዛከ ሙሓመዱን ሙስጠፈል በሪየቲ
🌞
ወካነ ሐቢበሁ ቢታጂል ኑቡወቲ
ሚን ቀብሊ አው አዲመ በይነል ማእ ወልጢነቲ
🌞
የዕሱቡል አዘሊዪ ወፈውዙል አበዲዪ
ጀነቱል ዛኢሪነ መቃመል ቁድሲየቲ
🌞
ወያረቢ ሰሊምና ሚን ኩሊል በሊየቲ ³
ወነዲር ውጁሃና ቢልሪዷ ወልቁርበቲ
🌞
ሰላቱን ወተስሊሙ ቢአንማ በረከቲ ³
ዓላ መን ሢሪል ረውዲ ወኩሉል መኽሉቀቲ
🌞
ፈከይፈ ዓላኡሁ ወከይፈ ሠማኡሁ
ወሽታቀል መላኢካ ሊዱሪል ፈርዲየቲ
🌞
ወተዕሉ ፈውቀል ጀውዛ ወልሡራዲቂል አስና
ወቲልከ ኑሩል ሐቂ ዓጀበን ሊነዝረቲ
🌞
ፈከይፈ ቢሚثْሊሂ ወበሕረ ሲፋቲሂ
ወሃዛ ሙሐመዱን ብትቁርቢን ወዙልፈቲ


ከሚለው የዳኒይ መድህ አለፍ አለፍ ተብሎ የተቀነጨቡ ስንኞች
❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀

አንተል ባቡ ሊዓጣኢ-ላህ
ኹዝ ቢየዲ ያ ረሡለ-ሏህ
♥️
አንተ ዓይኑ ሚን ዑዩኒ-ላህ
ኹዝ ቢየዲ ያ ረሡለ-ሏህ
♥️
አንተል ሢሩ ሊኢብዳኢል ከውን
ኹዝ ቢየዲ ያ ረሡለ-ሏህ
♥️
አንተ ከህፉ መውጁዳቲ-ላህ
ኹዝ ቢየዲ ያ ረሡለ-ሏህ
♥️
አንተ አንተ ያ ረሡለ-ሏህ
ኹዝ ቢየዲ ያ ረሡለ-ሏህ
♥️
አንተል መቅሱድ ያ ሐቢበ-ሏህ
ኹዝ ቢየዲ ያ ረሡለ-ሏህ
♥️
አንተል ራቂ ቂመተል ከማል
ኹዝ ቢየዲ ያ ረሡለ-ሏህ
♥️
አንተል ዋቂ ሚን ዓዛቢ-ላህ
ኹዝ ቢየዲ ያ ረሡለ-ሏህ
♥️
አንተል ሣቂ ሚን ሸራቢ-ላህ
ኹዝ ቢየዲ ያ ረሡለ-ሏህ
♥️
አንተል ّሣሪ ቢኢዝኒል ባሪ
ኹዝ ቢየዲ ያ ረሡለ-ሏህ
♥️
አንተል ሣቂ ሊእሕባቢ-ላህ
ኹዝ ቢየዲ ያ ረሡለ-ሏህ


አላሁመ ሶሊ ዓላ ሙሀመዲ፣
መለይካ አንቢያን የበለጠው፣
ሲሩ ያልተገለጠው፣²
❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀

ሥሙን የከተበው፣ غገይብ ላይ በአዘል
ጀነት በየ‘ግንቡ፣ በየ‘ዛፉ ቀንዘል
በሱ-ነው አፍርቶ፣ ያገኘው መንዘልዘል
ጀነት ላይ ቢልጁዲ ወል-ከረሚል
አጅዘል፣
በጀሊል ልግስና ለሱ ለሚሰጠው።
.
ሥሙን የከተበው፣ ለአርዋህ መዳረሻ
በሃዉዱ መርጊያ‘ላይ በተስኒም መፍሰሻ
ባህረል መስጁር ዳር ዳር፣ አለ‘መጨረሻ
ከሲበል ዘዉር‘ላይ ላህሉ‘ሏህ መንገሻ፣
በአላህ መሀባ እሳት ለተለመጠጠዉ።

ሥሙን የከተበው፣ ጌታችን ጀባሩ
በጅብሪል ክንፍ‘ላይ ባይኑ በግንባሩ
በቀልቡ በራቀዉ ማእናና አኽባሩ
ማበሉን የዋኘዉ፣ የኛ ወቅት አህባሩ፣ በነኪር በሙንከር፣ ምላስ የኸጠጠዉ።

ሥሙን የከተበዉ፣ ወሲላ ደረጅ ላይ
ቡጡን የከተበው፣ አላንድ እንኳን ሰላይ
ኣማ‘ላይ ከተበው፣ ተከዉኑ ሆኖ አግላይ
ላሁት ላይ ከተበው፣ ላየው ሆኖ አዋላይ፣
ተመለይካ ተሰው ለተመረጠው

ሥሙን የከተበው፡ በየ-ጀነቱ ዕቃ
ሥሙን የከተበው በየ-በሩ ሳንቃ
ሥሙ ያጠፋው እጅግ የሳት ላንቃ
በሥሙ ያደነው የስንቱን ሰው ጫንቃ፣ የጀሀነም እሳት እንዳይለመጥጠው

ሥሙን የከተበው ሰማይ በየ-በሩ
ጀነት በየ‘ጉልቱ፣ ባለው በሚበሩ
በሹሃዳው እቃ በራቀው ኸበሩ
በጦር በጋሻቸው ገርሞ ማጥበርበሩ፣ በኑር መከዳቸው አላህ በመረጠው

በሱለይማን ኻተም፡ ስሙን የረቀመው
የየሱፍም ቀሚስ በሱ ቀመቀመው
ሂዝቡን ከያለበት ሥሙን የለቀመው
ስሙ በመጡረድ ጥፊ ጠረቀመው፣ ኢብሊስን ከሀድራው ጀሂም አፈረጠው።

ሥሙን የከተበው፡ በአህሉላህ ደረት
ጀነት በያቁቱ፣ በሉለዎ፣ በዱረት
ሥሙን የከተበው በሙንተሃ ሲድረት
ሥሙን ለሰዓዳ ያረገው መሰረት፣
ሥሙን በስንቱ ሆድ ሲሩን አስደፈጠው

የሥሙ መክተብያ ተቆጥሮ የማያልቀው
መለይካ-ሰው ቆጥሮት ምላሰ እማይዘልቀው
ለካ ረቡል‘ጀሊል ለጉድ‘ነው ሲኸልቀው
ሙናጢን ሊሰደው መደዱን ሊያፈልቀው፣
ስንቱ እሱን በማየት ተስንቱን ሊያበልጠው።
.
.
አላሁመ ሶሊ ዓላ ሙሀመዲ፣ መለይካ አንቢያን የበለጠው፣ ሲሩ ያልተገለጠው፣²
‹መጅሙዐቱል መዳኢኽ አል-አጀምያ»
(ሼህ ሰይድ ኢብራሂም-ጫሌ 1872-1947)›

@muhammednessim


ፋጢመቱ-ዘህራእ ቢንት ሙሐመድﷺ

ፋጢመቱ ዘህራእ ቢንት ሙሐመድ የነብዩ ሙሐመድ ﷺ እና የእመት ኸዲጃ (ረ.ዐ) አራተኛ ሴት ልጅ ናት። ፋጢማ (ረ.ዐ) የተወለደችው ሙሐመድﷺ ነብይና መልእክተኛ ከመሆናቸው አምስት ዓመት በፊት ወይም ከሂጅራ አስራ ስምንት ዓመታት በፊት ነበር።" "መሪየም ፣ እመት ኸዲጃ ፣ አሲያ እና ፋጢማ(ረ.ዐ) በምድር ላይ ካሉ ሴቶች ሁሉ ንጹህና በላጭ ናቸው " በማለት ነብዩﷺ መስክረውላቸዋል።

ፋጢማ(ረ.ዐ) የአምስት ዓመት ታዳጊ እያለች አባቷﷺ ለሰው ዘር በሙሉ ነብይ ተደርገው ተላኩ። በዚህም የተነሳ ፋጢማ (ረ.ዐ) ገና በለጋ እድሜዋ ቁረይሾች በአባቷ ላይ በየጊዜው በሚያደርሱት ግፍ ክፉኛ መሳ^ቀቅና ሃዘን ደርሶባታል። በይበልጥም ደግሞ ከሁሉም የከፋ መከራ የደረሰባት ከመላ ቤተሰቧና የበኒ ሃሽምና የዐብድመናፍ አባላት ጋር የአቡ ጧሊብ ሸለቆ የሚባለው ስፍራ ገና በለጋ እድሜዋ ሶስት የመከራ ዓመታትን በገፉበት ጊዜ ነበር። በዚያ ሳለች ብዙ የርሀብና የጥም ዕለታትን አስተናግዳለች። ያንን የመከራ ጊዜ ተገላግላ ብዙም ሳትቆይ ነበር ተወዳጇን እናቷን ኸድጃን(ረ.ዐ) በሞት ያጣችው። ይሁን እንጂ ሌላ ምርጫ ስላjልነበራት የእናቷን ፍቅር ደርባ ለክቡሩ አባቷ በመስጠት በሁሉም ጉዳያቸው ከጎናቸው መቆሟን በተግባር ለማሳየት ትጥር ነበር።

ነብዩﷺ ሙስሊሞች ሁሉ ከመካውያን ግፍ ለማምለጥ ይችሉ ዘንድ ወደ መዲና እንዲሰደዱ ባዘዙበት ጊዜ እሷና እህቷ እሙ ኩልሡም ወደ መዲና የሚወስዳቸው ሰው እስኪላክላቸው ድረስ መካ ውስጥ ቆይተው ነበር። ፋጢማ(ረ.ዐ) አስራ ስምንት አመት እንደሆናት አቡበክርና ዑመርን(ረ.ዐ) የመሳሰሉ በርካታ ታላላቅ ሶሀባዎች ለትዳር ፈልገዋት ነበር። ሆኖም ግን ነብዩﷺ በታላቅ ትህትና ይቅርታ እንዲያደርጉላቸው እየጠየቁ ጋብቻውን ውድቅ አድርገውታል። ከዚያም ነብዩﷺ ለአሊ(ረ.ዐ) ዳሯት። በጊዜው ዐሊ(ረ.ዐ) ለመህር የሚሆን ገንዘብ ስላልነበራቸው ነብዩﷺ ያበረከቱላቸውን ጋሻ ለዑስማን(ረ.ዐ) በአራት መቶ ሰባ ዲርሀም ሸጡላቸው። ከዚያም ገንዘቡን ወስደው ለነብዩﷺ ሲሰጧቸው እርሳቸው ደግሞ ቢላል ጥቂት ሽቶ እንድገዛ ካደረጉ ቡኋላ የቀረውን ለሙሽራዋ የሚያስፈልጋትን ነገሮች ትገዛላት ዘንድ ለኡሙ ሰለማ(ረ.ዐ) ሰጧት። ከዚያ ነብዩﷺ ተከታዮቻቸውን ጋብዘው የጋብቻቸውን ሥነ-ሥርዓት አደረጉ። የዒሻእ ሰላት ተሰግዶ እንዳበቃም ወደ ሙሽሮቹ ሄደው ውሃ እንዲሰጧቸው ጠየቁ። ከዚያም ውዱእ ካደረጉ ቡኋላ ውሃውን በእነርሱ ላይ እየረጩ እንድህ አሉ፦ "አላህ ሆይ! ባርካቸው እንዲሁም ከእነርሱ የሚወጡትን ልጆችም ባርክ።" ይህ ከሆነ ከዓመት ቡኋላ ፋጢማ(ረ.ዐ) የመጀመሪያ ልጇን ለነብዩምﷺ የመጀመሪያ የልጅ ልጅ የሆነውን አል-ሐሰንን በሂጅራ የዘመን አቆጣጠር ሦስተኛው አመት ላይ ወለደች። ነብዩﷺ በሁኔታው በጣም የተደሰቱ በመሆናቸው በህፃኑ ልጅ ጆሮ ላይ አዛን አደረጉበት። ከዚያ ቴምር በአፋቸው ካላመጡ ቡኋላ በአፉ ላይ አደረጉበት። ስሙንም አል-ሐሰን ብለው ከሰየሙት ቡኃላ ጸጉሩን ላጭተው በጸጉሩ ሚዛን ልክ ብር ሶደቃ አከፋፈሉ። ቡኃላ ደግሞ ፋጢማ አል-ሑሰይን የሚባል ወንድ ልጅ ተገላገለች። ነብዩﷺ አል-ሐሰንና አል-ሑሰይንን በጣም የሚወዷቸው ከመሆኑ የተነሣ ሁልጊዜም ከአጠገባቸው አይለዩዋቸውም ነበር። ሀያሉ አላህ፦

"የነብዩ ቤተሰቦች ሆይ! አላህ የሚሻው፤ ከናንተ ላይ እርክሰትን ሲያስወግድና፤ ማጥራትንም ሲያጠራችሁ ብቻ ነው።" (አል-አሕዛብ፡33)

የሚለውን የቁርኣን አንቀጽ ባወረደ ጊዜ ነብዩﷺ በኡሙ ሰለማ ቤት ዓሊን ፣ ፋጢማን ፣ አል-ሐሰንና አል-ሑሰይንን ሰብስበው በመጎናጸፊያቸው ከሸፈኗቸው ቡኃላ እንደሚከተለው በማለት አላህን ለመኑ፦ "አላህ ሆይ! እነዚህ ቤተሰቦቼ ናቸው። ከእነርሱ ላይ ርክስነትን አስወግድ። ንጹህና ነውር የሌለባቸውም አድርጋቸው" ይህንን ለሦስት ጊዜያት ያክል ከደጋግሙ ቡኃላ እንዲህ አሉ፦ "አላህ ሆይ! ሶላትና በረከትን በኢብራሂም ቤተሰቦች ላይ አድርግ በእርግጥ ምስጋና የሚገባህና ታላቅ የሆንክ ጌታ ነህና።» በአምስተኛው የሂጅራ ዓመት ፋጢማና አሊ(ረ.ዐ) አያቷ ነብዩ ሙሐመድﷺ ዘይነብ በማለት ስም ያወጡላትን ልጅ ወለዱ። ቆመው ይቀበሏትና ይስሟታል። እርሷም እንደዚያው ታደርጋለች።" አንድ ጊዜ ሚንበር ላይ ሆነው ንግግር እያደረጉ ለፋጢማ ያላቸውን ፍቅር ሲገልጹ እንዲህ ብለዋል፦

"ፋጢማ የእኔ አካል ነች እሷን ያስቆጣ እኔንም አስቆጥቷል።» በሌላ የሀድስ ዘገባ ነብዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንደሚከተለው ማለታቸው ተጠቅሷል፦ "ፋጢማ የእኔ አካል ነች እሷን ያስቆጣ እኔን አስቆጥቷል። እሷን የጎዳ እኔን ጎድቷል። (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

ይሁን እንጂ ነብዩﷺ ተወዳጇን ልጃቸውን ፋጢማን(ረ.ዐ) ሌሎችንም የሚቀርቧቸውን መልካም ስራዎችን የመስራትን አስፈላጊነት በመግለጽ ትኩረት እንዲሰጡት ይገፋፉ ነበር። አንድ እለት እንዲህ አሉ፦

"የቁረይሽ ሕዝቦች ሆይ! ነፍሶቻችሁን አድኑ። የአላህን ሀቅ በተመለከተ ምንም የማደርግላችሁ ነገር የለኝም። የሙሐመድ ልጅ ፋጡማ ሆይ! እኔ ዘንድ ካለው ነገር የፈለግሽውን ነገር ጠይቂኝ። የአላህን ሀቅ በተመለከተ ግን ምንም ላደርግልሽ አልችልም። በሌላ ዘገባ እንደሚከተለው ብለዋል፦ "ፋጢማ ቢንት ሙሐመድ ሆይ! እራስሽን ከጀሀነም እሳት ጠብቂ። ከአላህ ፍቃድ ውጭ ልጎዳሽም ሆነ ልጠቅምሽ አልችልምና።" ( ቡኻሪ ዘግበውታል)


ሠልማንን ፋሪስን የማረከው ሑቡ
የናፍቆቱን ሸራብ የጠጣው ሙሒቡ
ቡራዒን ተየመን ያስተኛው በቅርቡ
አሚሩል የመንም ሞተ ባጠገቡ
እነ አሕመደል ሃዲ መዲና ኸተሙ ሙስጠፋ ነቢ የሁሉ ኢሚሙ
♥️
ሰላቱ ረቢ ዓለይኩም ሠላሙ
ሰላቱ ረቢ ዓለይኩም ሠላሙ
ሙስጠፋ ነቢ የሁሉ ኢሚሙ
♥️
ቢላልን ያመጣው ከአርዱል ሐበሻ
እርግብ ያጫወተው ሲገባ በዋሻ
ሸረሪቱ ድሩን ያርገለት ጋሻ
ያምቢዮቹ አለቃ የደሓ መሸሻ
በስሙ ተማሩ አቡና አደሙ ሙስጠፋ ነቢ የሁሉ ኢሚሙ
♥️
ሰላቱ ረቢ ዓለይኩም ሠላሙ
ሰላቱ ረቢ ዓለይኩም ሠላሙ
ሙስጠፋ ነቢ የሁሉ ኢሚሙ
....
የመሓባን መዕና ልንገርህ በወግቴ
እስቲቃማ ጋራ ሌላ አለው ጭማርቴ
ሐሉ ይመራሀል ልንገርህ በእውንቴ
ቀጥ ማለት ብቻ ነው አትበል ወረቴ
ዱረል ኹሱሲያ አለው በግድሙ ሙስጠፋ ነቢ የሁሉ ኢሚሙ
♥️
ሰላቱ ረቢ ዓለይኩም ሠላሙ
ሰላቱ ረቢ ዓለይኩም ሠላሙ
ሙስጠፋ ነቢ የሁሉ ኢሚሙ
♥️
መሓባ አስል ነው ለሙላው አሕዋል
መሓባ የለለው የለውም ከማል
ለመሓባ ሲል ነው መቃመል ሪጃል
ማእሪፋ ማገኘት ማወቅ ዙልጀላል
መሓባ የሌለው ውድቅ ነው መቃሙ ሙስጠፋ ነቢ የሁሉ ኢሚሙ
♥️
ሰላቱ ረቢ ዓለይኩም ሠላሙ
ሰላቱ ረቢ ዓለይኩም ሠላሙ
ሙስጠፋ ነቢ የሁሉ ኢሚሙ


🖤❤️ከአብሬትይ አልሳኒ ወአዝ❤️🖤❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀

አላህ ያበ ኒዕማ የኸረ በኸረ ያነኸማ ኤኽሪ። ዮረ ግዝየ ይኽሪ ባንኸሬ ታነማ ኤኽሪ። በላ የቸነ ግዝየ ባንኸሬ ባንቸነ ኤኽሪ። እማት እማት በፎር ያነቦ ኒእማ ቂማ ኤነኖ ቃርኖ:: በቂማ ይገሙችዮ ቃር ተኸረ ቂማ ባነከውኖ::

መጀመሪያ ኢማን:- ኢማን ይስሬ ቃር ተኸረ ታፈር ቅርሽቶ ታነ ሰሜ ስን ወርቅ ቢሰፉሪ ቂማታ ባንሰኔ።
የአፍያም ኒእማ የኸረ በኸረ እንክሙ። እማት አይን ይስሬ ቃር ተኸረ ቂማታ ምር ይስራን ባነ? እንዝር :- ስሞት ይስሬ ቃር ተኸረ ቂማታ ምራህር ባነ? አቅል ይስሬ ቃር ተኸረ ቂማታ ምራህር ቃር ባነ? ዘንጎት ይስሬ ቃር ተኸረ ዘንጎት ኹታ በምራህር ቃር ይንኸዊ ባነ?

📌#በአማሪኛ
~~~~~~~~~~~~

አሏህ የሰጠን ኒእማ የሆነ እንደሆነ መኖሩ አይታወቅም:: የሄደ ግዜ ይታወቃል እንጂ እያለማ አይታወቅም:: በላ የመጣ ግዜ ይታወቃል እንጂ በላ ካልመጣ አይታወቅም:: እያንዳንዱ በላያችን ያሉ ኒእማዎች ሊተካ የሚችል ዋጋ የሌላቸው
ነገሮች ናቸው:: በዋጋ የሚገመቱ ቢሆኑ ኖሮ ትክክለኛ ዋጋ አይገኝላቸውም ነበር::

መጀመሪያ ኢማን:- ኢማን የሚገዛ ነገር ቢሆን ኖሮ ከመሬት አንስቶ እስከ ሰማይ ወርቅ ቢሰፈር ዋጋውን አይደርስም:: የአፍያ ኒእማ የሆነ እንደሆነ እንደዛው ነው:: አይን ብቻ የሚገዛ ነገር ቢሆን ኖሮ ዋጋው ምን ይገባው ነበር? ጆሮ:- መስማት የሚገዛ ነገር ቢሆን ኖሮ ዋጋው ምን ያህል ይሆን ነበር? አቅል የሚገዛ ቢሆን ኖሮ ዋጋው ምን ያህል ይሆን ነበር? መናገር ሚገዛ ቢሆን ኖሮ መናገር በምን ያህል ነገር ይገኝ ነበር?


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
صلى الله على محمد
صلى الله على محمد وعلى ال وسلم
♥️❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀♥️

نحمد الله المقدم الى البحبوح والنعم
نبي الحق المقدم
♥️
تجلى البدر في الحرم بوصف يعلو في العالم
ويرمي يدا في الكرم
♥️
عمر الود والمدد ببيت الحب المشيد
صاحب البطحا والزمزم
♥️
غرة شيث والخليل عز قريش وتبجيل
ناموس سر المطلسم
♥️
توبة ابي البشر سيد بني مضر
ذوا المئا ثير المكرم


🖤❤️ሰሉ ዓለል ሐቢቢ❤️🖤
❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀

ከአብሬትዩ ሳኒ(ቀ.ሲ) ደላኢል ከጊዛዑል ዓቢድን የሰለዋት ኪታብ የተወሰደ👇🏽

ሰለዋት ነብያችንﷺ ላይ በብዛት የሚያወርድ ሰው ለእዩልኝ እንኳን ቢሆን የሲራጥን ድልድይ በመብረቅ ብልጭታ ፍጥነት ያልፋል በእርሳቸው በረካም በተደላደለው በጀነት ቤት ይኖራል::

اللهم صل على سيدنا محمد وعلى آل سيدنا محمد الذى من أكثر الصلاة عليه ولو رياء طار على الصراط كالبرق الخاطف، وعاش ببركته فى دار النعيم


🖤🔥የኸሚስ ስጦታ🔥🖤
❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀
😍ዒሽቅ🔥ሸውቅ 💚መደድ

አብሬት መንዙማ
በሸህ ጀማል እና በዑስታዝ ጀዋድ እስከነ ፅሁፉ

አሰላት ወሠላም ዓላ ሐቢቢ
አሰላት ወሠላም ዓላ ሐቢቢ
አሰላት ወሠላም ዓላ ሠይዲ ያረሱሉሏህ

الصلاة والسلام على حبيبى  
الصلاة والسلام على حبيبى  
الصلاة والسلام على سيدى يارسول لله

https://youtu.be/lG7dmnq3dfk


🖤ጥቂት ስንኞች ከሠይዲ መድህ🖤
❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀

ያነቢየሏህ አርሒቡ
አህለን ወሳህለን አርሒቡ
አሠላም ዓለይኩም
~~~~~~~~~~~~~~~~~

ሙሐምድ ኸይሪል በራያ
መሥለኩ አህለል ሂዳያ
ሚፍታሑ ባቡል ዓጣያ
ወካነ ዑላሁ ጋያህ ሊኩሊል ኸልቂ ኒሃያ
♥️
ሙሐመድ አልሙንተኸቢ
ሚን ዓለሚል ገይቢል ገይቢ
ቢሢጃኒል ሙረጀቢ
ቢዑላሁል ሙሕተጀቢ ኸሰስ ቢቁርቢል ቁርቢ
♥️
አንተ አሏሁ አሚይኒ
አንተ ጀውሃሩ መክኑኒ
አንተ ፊ አሏህ ማእሙኒ
ሊመላኪሂ መኪይኒ ቢኑሪል ቢሃ መዕጁኒ


🖤🔥የኸሚስ ስጦታ🔥🖤
❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀

😍ዒሽቅ🔥ሸውቅ 💚መደድ

ድምቅ ያለ የደዌ / ማሽ ሐድራ መንዙማ መሽረብ ሙቃበላ

(1) ጀማሉል ዓለም ሰለሏህ ዓለይሂ ወሠለም ጀማሉል ዓለም
(2)ሒላሉል ዓለም ሰለሏህ ዓለይሂ ወሠለም ሒላሉል ዓለም
(3)ያዘይነል ዓለም ሰለሏህ ዓለይሂ ወሠለም ያዘይነል ዓለም
(4)ያበድረል ተማም ሰለሏህ ዓለይሂ ወሠለም ያበድረል ተማም
(5)ሚስባሒል ዘላም ሰለሏህ ዓለይሂ ወሠለም ሚሥባሒል ዘሏም
(6)ጢቡል ሙሸመም ሰለሏህ ዓለይሂ ወሠለም ጢቡል ሙሸመም
(7)ሚሥኩል ሙኸተም ሰለሏህ ዓለይሂ ወሠለም ሚሥኩል ሙኸተም

https://youtu.be/UYwxpiZau0E


ሰው አይጠፉ ጠፍቶ አይሰሩ ሲሰራ
ጠፍቶ የነበረው የዲኒቱ ጮራ
ከሁሉም ባማረ በስተሰሜን በራ
ጌታ በጌታ ልጅ በሰይድ بባ شሺን رራ
በሱ በኩል ሆነ የሀበሻው ኑስራ
ፈጃአ ኢለይና በሺር ወ ነዚራ
አልሃምዱሊላህ ወል ሀምደን ከሲራ
አዲስ ጅምር ሳይሆን አብሬት እናንገራ
የተደራጀ ነው በአለመል ዘራ


ደቡብ ያስታውሳል 3
==============

ምስጋና ከሱ በሆነ እዝነት ፍጡራኑን ባማረ አለም ላይ አመቻችቶ ለፈጠረው... በመልአክቶች ፣ በነብያቶች እንዲሁም በሷሊህ ባሪያውች (አውሊያ) ወደራሱ ሰዎችን ላመላከተው ለመራው አላህ...

የአበል ራሙዝ ሀገር ሀበሻ ሆይ... ሰማይሺን እወደዋለሁ... አፈርሽን እወደዋለሁ... አየርሽን እወደዋለሁ... የሚኖሩብሽን እወዳቸዋለሁ... ሰላምሽን ያብዛልኝ... ማን ያውቃል ሰው በዱአ ከበረታ በአጭር ቀኖች የነስር ዜና እንሰማ ይሆናል...

ካለፈው የቀጠለ....

የመፃይ ቀን ቀጠሮ

💚🌹የአብሬት እንዲሁም የአቅራቢያዎቿን ነዋሪዎች ሰብስቡና "ጉራጌ ከየአቅጣጫው የፊታችን ቅዳሜ ወደቀያቹ ሊመጣ ነው... አብዛኛው የቀናት መንገዶች አቋርጦ ስለሚመጣ እዚህ ሲደርስ ተርቦ ነው... ከየጓሮአቹ የተስተካከለ አንድ አንድ ስር አምቾና አንድ ጀበና ቡና ላስቸግራቹ... ጀንበር ከርማ መመለስ የማይችሉም ስላሉ ቤቶቻቹን ክፈቱ አልጋዎቻቹን ልቀቁላቸው..." የሚል ጥሪ ለአካባቢው ነዋሪ አስተጋቡ... ተስማማም...

የቀጠሮ ቀኑም ደረሰ... የሚገኘው ሰፊ ሜዳም በአግድም ወንበሮች ቁም በተፈለጡ እንጨተቶች ተሞሉ... የአካባቢው ማህበረሰብ ቤቱን ከፍቶ ለእንግዳው በየ መንገዱ የሚጠጡ የሚበሉ ነገሮችን ማደል ጀመረ... በቅጡም ሳይነጋ በፈረስ፣ በበቅሉ ፣ በእግር ፣ አንድ ፣ ሁለት ፣ ሶስት ከዛም በላይ ሆነው እየተሳሳቁ እና እየተጨዋወቱ በመጡ የጉራጌ ተወላጆች ሜዳው ተሞላ... ጉራጌ ከየአቅጣጫው እንደ ጅረት ፈሰሰ... ያሰፊ ፈረስ የሚያስጋልብ ሜዳ ከመጣው ጉራጌ ጋር መስተካከል አቃተው...

ግን አንዱ ሌላውን ላለማየት ፊት ተነፊፈገ... ጌታ ለኧኖር ፣ እዣ ለቸሀ ፣ ጉመር ለሞህር ጀርባ ተሰጣጠ...

አዝማች ጨረቶ ብድግ አሉና "ዛሬ የሰበሰቡን ሸሆች የሚሉን ነገር ካለ እንስማቸው..." ብለው ሸሆችን ወደ መድረክ ጋበዙ...

💕ሸሆችም ህዝብን ከአንድ ዳር እስከ ሌላው ቃኙት... መቃቃሩንም አስተዋሉና እንደ ሁሉ ግዜው "ያ-ሃቅ ሀቅን አናግረኝ..." በሚለው በተለመደው ዱአቸው ንግግራቸው ከፈቱ "ጉራጌ አንድ አንዱ 15 ሌላው 20ም ድረስ አባቱን በጉራጌ ይቆጥራል... ሞህር ከኧኖር ፣ እዣ ከቸሀ ፣ ጌታ ከጉመር... ያልተዛመደ አለ?... ከሌላ አላገባክም?... ለሌላም አልዳርክም?... ለዘመናት ጠላት ያልካቸውን አንዱ በሌላው ትከሻ ስር ተደብቆ ተዋግ^ቶዋል... በአንድ ሃያቱ ያልተገናኘ በሌላ ሃያቱ ይገናኛል... አሁን ዘር ቁጠሩ... ሞህር ብቻ... ቸሀ ብቻ... ጌታ ብቻ... ኧኖር ብቻ... ከሆንን እናንተ ጀርባ ትሰጣጣላችሁ... እኛም እንደ እናንተው ጀርባ እንሰጣለን..." አሉ...

አዝማች ጨረቶ ብድግ ብለው ሞህሩ ፣ ቸሀው ሌላውም ክብ ሰርቶና ሌላውን አግሎ በተቀመጠበት ሁሉ ዘር የሚያስቆጥር ሰው መደቡ...

ከቆይታዎች በውሃላ 'አግኝተናል... አግኝተናል...' የሚል ድምፅ ከየታዳሚው መሰማት ጀመረ... እየተነሳ ቸሀ ጌትነቱን፣ ኧኖር ኧዣነቱን፣ ሞህር ጉመርነቱን ቆጠረ... ሁሉም ጀርባ የሰጠው ወንድሙን እንደሆነ ሲያውቅ እየዞረ ሳመው... ከጎኑ ተቀመጠ...

💕ሸሆች አሁንም ተነሱ "ጉራጌ እግር ጌህ... ተጎራብቶ አልያም ወንዝህን ተሻግሮ ያለው ወንድምህ ጠላትህ አይደለም... ሰፊ ሆነህ ተጎራብተህ... ተወዳጅተህ... ተዛምደህ ኖረሀል... ዛሬ ሀገራችን ምላስ ከሚቆጥራት እግር ተጉዞ ከሚጨርሳት በላይ ስትሰፋ አንተም መስፋት ሲገባህ አትቀነስ... አንዱ ጋር ያለ ጋሻ ጦ^ር ለአንድ መመኪያው ሊሆን ይገባል..." አሉና የተሰበሰበውን በሺ የሚቆጠር ህዝብ ተመለከቱ... ጥሞናውን ሰቷቸዋል... ቀጠሉ "አላህ ያለ እንደው ተፊትህ የሀቂቃ ጠላት ወደ አንተ እየገሰገሰ ነው... አላህ ያለ እንደው ጣሊያን የተሰኘ በሀገርህ ልግዛህ ብሎ ወንዝህን አቋርጦ ድንበርህን ተሻግሮ ቤትህ ሊደርስ ወራት ቀርተዋል..." ብለው ሸሆች ዝም አሉ...

የተሰበሰበውም ህዝብ ተደናገጠ... ምን ይሻላልም አለ...

💕ሼሆች ከሴንጤ እስከ መ^ድፍ ያለን መሳ^ሪያ በየ ቁመታቸው እና ግዝፈታቸው አስደረደሩ... ከየ ቤቱ የተከበሩ ሽማግሌዎች እንዲሁም ባለአባቶች እየወጡ በወንድማቸው ቸሀ በሞህር ፣ ኧኖር በኧዣ ፣ ጌታ በጉመር... በቂም አሳልፎ እንደማይሰጥ " እከሌ ላይ ከጠቆምኩ ከሴንጤው ባልፍ ከጦ^ሩ አልለፍ... ከጦ^ሩ ባልፍ ከጎራ^ዴው አልለፍ ... ከጎራደው ባልፍ...... ከመ*ድፉ አልለፍ..." እያለ እንዲምል አደረጉት...

"በል ጉራጌ እምነትህን የሚያስጥል... ሀገርን የሚያ^ስክድ ጠ^ላት እየመጣ ነው ለጦ^ርነት ተዘጋጅ... በየ ቤቱ ያስቀመጣችሁትን መሳሪያዎች አምጣ ሰለሚል... እንደ ሹልኪት፣ባለነሀስ፣ ዘመን... ያሉ እርካሽ ሽጉ^ጦች ግዙ ጣሊያኖች ሲጠይቁ እሱን ታስረክባላቹ... እንደ እስኮልት እና ጠመ^ንጃ ያሉ ሽጉ^ጦችን በጓሮአቹ ቅ^በሩ ወይንም በምሰሶዎቻቹ ስር ደብቁ... ጦ^ርነት ይጠብቀናል..." አሉና ጉራጌን አስጠነቀቁ...

ብዙም ሳይቆይ ከወራት በሁዋላ ጣሊያን ኢትዮጵያን ወ^ረረ... የጉራጌ ህዝብም በሼሁ እየተመራ የጣሊያንን ጦር ሰላም ነሳው...

ጣሊያን የሸሆችን ቀድሞ መገኘት ተከትሎ በጉራጌ ከሁለት ኧዣ ባለአባቶች በስተቀር አንድም ሰውን አልገደለም... ይህንን ተከትሎ በጥልቅ ምርምር ያልሰሩ ድርሳኖች በዶሴያቸው ጉራጌ ባን^ዳ ስለነበር ነው ይላሉ... አይ ጉራጌ ሸህ ስለነበረው ነው!!!
**************************************

በአንድ አጋጣሚ እንድብር ላይ ሱሩር ዲገታ የተባለ ግለሰቡን ሊሰ^ቅል እንጨት መቶ ጣሊያን መዘጋጀቱን ሲሰማ ፍጡር ተበድሎ የማታርፈው በቅሎአቸውን ዳግም ነድተዋታል... " ጣሊያን ለደሀ ፍትህን ሊሰጥ መምጣቱን እንጂ ደሀን የተቀዳደደን ልብስ የለበሰ... አዋራ የለበሰው ሰው ሊሰ^ቅል መምጣቱን አናውቅም ነበር... " ብለው ሸሆች አስጥለውታል... ከማስጣልም አልፎ ልብስ ከጣሊያን እልፍኝ ለሱሩር ዲገታ አሰጥተውታል...

መ^ረር ያለ እርምጃ ህዝቡ ላይ እንዳይወስድ በፖለቲካ... ሀገርን ለመታደግ ጦ^ር ሆነው ዘም^ተውበታል...

ይዞ ሊገ^ላቸው ሲያሴር ጉራጌ ከየ አቅጣጫው ሲ^ዘምት "ለኔ ግድ የለም ጌታዬ በነገሬ ላይ አዋቂ... በሚበጀኝ ላይ ፈራጅ ነው... ተመለስ..." ብለው በየ አቅጣጫው መልእክተኛ ልከዋል... ጉራጌ "ከሞ^ትንም፣ ተኖርንም ተእርሶ...." ብሎ ዘ^መተ እንጂ...

እናም... ደቡብ ጌታው(አላህ) በሰጠው ሁሉ ሳይሰስት የሰጠውን ዛሬም አልረሳም... እንደምንስ ከፅልመት ሊያድኑት አስተማሪ... መላ ሊያበጁለት ሽማግሌ... እንዳይበደል ጦ^ረኛ... እንዳይገፋ ፖለቲከኛ... ሸሪዓን እንዳይጥስ ቃዲ ሆነው ያገለገሉትን ገበና ከታቹን ይረሳ...

ለጌታቸው(አላህ) እራሳቸውን ፍፁም ሰተውት ነበር... ከተናገሩ አላህ የሚወደውን... ከሮጡ አላህ ለሚወደው ጉዳይ... ከተጓዙ ወደ ሚወደው ቦታ... ከሰሩ የሚወደውን... ፍፁም የአላህ ነበሩ... አላህም ፍፁም የነሱ ነበር...

ጊዜያት ነጉደው... ያሁሉ ዘመናት አልፈው... ዛሬም ላይ ኸውላን ግራ ገብቶታል... አንደምን ለሁሉ ጎኑ በቃከው...👇🏽


የአሽረፈል ኸልቅ ዓልይሂ ሠላት ወሰላም የተከበረው ጀሰዳቸው ያረፈበት ሰሪር በተከበረው ራእሳቸው♥️ በኩል

اللهمّ صلّ على جمال الذّات الإلٰهيّة،
وعين السّيادة الأبديّة،
وباب التّجلّيّات الأحمديّة،
سيّدنا محمد وآله أشمل الصّلاة النّورانيّة

اللهمّ صلّ على عين حدقة الشّهوديّة،
ووارث القلوب النّورانيّة،
وباب الأنوار الملكوتيّة،
سيّدنا محمد وآله بطون التّجلّيّات الأحدية

اللهم صل على شمس الضّحوة الكبرى،
وصاحب قاب قوسين أو أدنى،
وحلّة عرائس الحضرة،
وعلى آله وصحبه ألف ألف مرّة


ደቡብን ያስታውሳሉ ክፍል 2
====================repost

የሃቅ መንግስት የከለከልከን እንደው የባ*ጢሉን አትን*ፈገን ብላቹ አላህን ለምኑት... መንግስት እያለ በሰዓታት የምንጓዘው መንገድ የሌለ ግዜ ወራት ሊፈጅ ይችላል...

ከአብሬትዩ ሳኒ ሸህ ሰይድ ባኡ ሳሊስ ዋዝ የተወሰደ.
******************************************

ምስጋና በጌትነቱ ሙሉ ለሆነው አላህ... ምስጋና በሰጠውም ነገር ላይ ፀጋ በከለከለውም ነገራቶች ላይ ፀጋን ለደበቀው አላህ... ምስጋና በእሺታውም ፀጋ በእን^ቢታውም ፀጋ ላደረገው አላህ... ምስጋና ሰቶ በነ^ሳው ነገር ላይ ፣ ባስቀ^ረው ነገርም ላይ ፀጋን ባደረገው አላህ... ምስጋና ፍር^ዱ ሁሉ ፍትህን ለሆነው አላህ... ምስጋና አብሬትዮች(ባሮቹን) ልቅናን በሁሉ መንገዱ ላጎናፀፈው አላህ... አላህ ሆይ አንተ በነብሳችን የፈረድከውን እኛ በነብሳችን ላይ ወደናታል...

ሸሆች (አል አብሬትዩ ሳኒ) በሸንጎ በተቀመጡበት... ለነገር በተጓዙበት... በሽምግልና በዋሉበት... እንዲያውም በኢባዳ ባሳለፏቸው ጊዜያቶች ለዚህ በአንድ ጎኑ ላልበጃቸው ህዝብ ማጣ^ትን ቀስፈ*ውለታል... ማሸነ^ፍን ገዝተው አኑረውለታል... ሰላምን ዛሬ ላይ ሰልጥነናል እንዳሉ ሰዎች ሳይሆን በተግባር ጦ*ሩን ሰብቆ የተቆሳ*ሰለውን የተበ*ዳደለውን እንደ ፀጉር እና ሚዶ አንድ አርገውታል...

ከጣሊያን መግባት አስቀድሞ

በ16ኛው ክፍለ ዘመን ከየአቅጣጫው ይሰነ^ዘሩበት የነበሩትን የተለያዩ ጥቃ*ቶች በጋራ ለመመ*ከት አንድ የሆነው 7 ቤተ ጉራጌ የሐሰን እንጃሞ ሽን*ፈትን ተከትሎ በአፄአዊ አገ^ዛዝ ስርአት ውስጥ ወደ*ቀ... ከግዜያት በሃላ ተጎራባቾቹም ቀስበቀስ ወደ አዲሲቷ ኢትዮጵያ በመቀላቀላቸው ጉራጌ ጥንት አንድ ያረገው እራስን የመከላከል አላማ አረጀ... ናተበ... ሌላ የሚሰበስበው አላማ አንድ የሚያደረገው ምክኒያት አጣ...

7 ቤተ ጉራጌ ተብለው በአንድ ስም አንደኛውም ሰባተኛውም ሆነው የተጠሩ ጎሳዎች ለግጦሽ መሬት ፣ በወንዝ ፣ በድንበር... 'የኔ ነው... የኔ ነው...' ተነ*ካኩ... መነካ*ካትን አልፈው በንግግር ተቦላ*ለቱ... እሱንም አልፈው ጦ*ር ተማ*ዘው ደ*ም ተቃ*ቡ... አያሌ ወጣቶችም እንደ ቅ*ጠል ረ*ገፉ...

ይህንን ተከትሎ

መንገደኛው... የአላህ ፍጡር ተበዳ*ድሎ እንቅልፍ የማይቀናቸው ኸልቁን 'እበጀው ይሁን...' ባሉበት መንገድ መጓዝ መዋተን የማይደክማቸው ሸሆች (አል አብሬትዩ ሳኒ) በቅሎዋቸው ኮርቻ ተጫነ... በሺ የሚቆጠሩ ደረሳዎቻቸውን አስከትለው ወደ ሞህር ጋለቡ...

'ሸሆች እየመጡ ነው...' የሚል መልእክት ቀድሞ ደርሷቸው ነበርና የሞህር ባለአባቶች በመሰብሰብ አቀባበል አደረጉላቸው... ሸሆችም አረፍም ሳይሉ ተእህል ውሃው ሳይቀምሱ የመጡበት የተጨነቁበትን የጉራጌ ጦ*ር በአንዱ ለሌላው ከሰገባው መመ*ዘዙን እንዴት ይሻላል ብለው አማከሯቸው...

የሞህር ባለአባቶችም አንዱ ከአንዱ አፍ እየተቀበለ "ሸሆች ኧዣዎች በድንገት ወግ*ተውን አንብሌ የተበለው መሬታችንን ህዝቦቻችንን በማፈ*ናቀል ወጣቶቻችንን በመግ*ደል ወረ*ውብናል... እኛ ዝግጅት ጨርሰናል እንደውም ወግ*ተን የተወሰ*ደብንን መሬት ብቻ ሳይሆን ሌላም እንይ*ዛለን..." የሚል ቆሌን ገፋ*ፊ መልስ ሰጧቸው...

ሸሆች ሳይረ^በሹ በሰሙትም መልስ ሳይደ^ናገጡ "እኛ ኧጆካ የተባለ ቂጫ ስናቋቁም ተበ*ዳይን ለመካስ በ*ዳይን ለመቅጣት... ችግሮቻችንን በራሳችን ለመፍታት አልመን ነው... ሞህር ወደ ቂጫ ተመለስ..." የሚል ለስላሳ በሰሚው ልብ ላይ ጠብ የሚል ተማፅኖ የቀላቀለ ጥያቄን አቀረቡ...

ሞህሮች ከጥቂት መወያየት በሁዋላ መስማማታቸውን አሳወቁ... ለቀጣይ ቅዳሜ ከአብሬት አቅራቢያ የምትገኝ ካሳዬ የተባለ ቦታ ላይ ቀጠሮ ተጥሎ ተለያዩ...

ሸሆች አሁንም በቅሎአቸውን ወደ ኧዣ ነዱዋት... ከኧዣ ባለአባቶች ጋራም ተነጋገሩ... ቀጠሮውን አሳወቋቸው ተስማሙ...

መልሰው ወደ ቸሀ ጋለቡ... የቸሀ ባለአባቶችም ተቀበሏቸው... የመምጣታቸውን ምክንያት አጫወቷቸው...

የቸሀ ባለአባቶችም "ኧኖሮች አጡርየ የተባለው መሬታችንን በጉል*በት ወስ*ደዋል... ጠመንጃ*ዎቻችን ጥይ*ት ወጥተዋል... ጋሻ ፣ ጎራዴዎቻችን ተወል*ውለዋል... ልንዘምት ቀን ጥለናል... እናንተስ የጠላ*ታችን ኧኖር ወገን አይደላችሁም...." የሚል ያልጠበቁትን ምላሽ አገኙ...

ሸሆች " ወገኖቼ... የአንዱ ወንድም ጦ*ር ሌላ ወንድሙ ላይ ለምን ይቀሰራል... ኑ ወደቂጫችን... ያበላሸን ተው እንበል... ያጠፋን እንቅጣ... የተበ*ደለን አንካስ... " በማለት የሰሚወን ቀልብ የገዛ... ልቦናንም የረታ ንግግር አደረጉ... ቸሀም ለቀጠሮው ተስማማ...

የማታርፈው በቅሎዋቸው በአንድ ጀንበር መልሳ ወደ ጉመር አቀናች... የጉመር ባለአባቶችም እንደ ቀደሙት እሳት ለብሰው እሳት ጎርሰው እሳት መስለው "ጌታዎች ከኛ ብዙህ ጋሻ መሬቶችን በጉል*በት ገፍተ*ው ወስደ*ውብናል... እኛም የኛ የሆኑትን ልናስመልስ ክተ*ት አው*ጀናል... እናንተስ ብትሆኑ የጌታ ወገ*ን አይደላችሁም..." ቁጣ*ቸውን ሸሆች ፊትም ባሳበቀው ንግግር የውሳኔያቸውን አስረገጧቸው...

ሸሆቼም ባገኙት ምላሽ ፊታቸው ሳይጠ*ቁር... አንደበታቸው ሳይርድ "ልክ ልትሆኑ ትችላላችሁ... ጌታም አጥ*ፍቶ ሊሆን ይችላል... እኛ የምንለው ሌላ አይደለም... ቀን እንጣል ተበ*ዳይ ክ^ስ ይመስርት... በ*ዳይ መከላ^ከያውን ያቅርብ... በታማኝነታቸው ጉራጌ የመሰከረላቸው ሽማግሌዎች ይዳኙ... ወጣቶቻችን ይዳር... ይኳሉ ሀያት ያርጉን... የጥ*ይት እራት የሰይ*ፍ ሲሳይ አይሁኑ... የአባቶቻቸውን እርስት ይንከባከቡ... ተገ*ዳዩም በወንደም.. ገዳ*ዩም ወንድም አይሁን... ነው..." አሉ ለሰሚው በሚያሳሳ አንደበት... ጉመርም በቀጠሮ ተስማማ...

በቅሎአቸውን ወደ ጌታ አዞሩ... የጌታ ባለ አባትም "ጉመር በስጦታ የሰጠንን መሬት በጉል^በት ወሰድክ አለን..." ብሎ ለሸሆቹ አቤት አለ... እራሱንም ከሚደርስበት ማንኛውም ጥ*ቃት ለመታ^ደግ ዝግጁ መሆኑን ተናገረ... ሸሆች ጉራጌን ለመታ^ደግ አንደ መላ የዘየዱትን አጫወቱት በቀጠሮ ለመገኘት ተስማማ...

በተመሳሳይ ሁሉንም የጉራጌ ቤቶች ኧኖርን ጨምር ባልተሸነፈቺው ጀንበር ባልተሸነፈቺው ብርሀን እህል ባልቀመሰቺው አንጀታቸው ዞረው ለሽምግልና 'እሺ' አስብለው ወደ አብሬት ተመለሱ...

ይቀጥላል..... 🫵ኸውላን ሰይድ

የሸኾች ሀገር ጉራጌ
#እኔም_ጉራጌ_ነኝ_challenge

20 last posts shown.

2 830

subscribers
Channel statistics