አላሁመ ሶሊ ዓላ ሙሀመዲ፣
መለይካ አንቢያን የበለጠው፣
ሲሩ ያልተገለጠው፣²
❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀
ሥሙን የከተበው፣ غገይብ ላይ በአዘል
ጀነት በየ‘ግንቡ፣ በየ‘ዛፉ ቀንዘል
በሱ-ነው አፍርቶ፣ ያገኘው መንዘልዘል
ጀነት ላይ ቢልጁዲ ወል-ከረሚል
አጅዘል፣
በጀሊል ልግስና ለሱ ለሚሰጠው።
.
ሥሙን የከተበው፣ ለአርዋህ መዳረሻ
በሃዉዱ መርጊያ‘ላይ በተስኒም መፍሰሻ
ባህረል መስጁር ዳር ዳር፣ አለ‘መጨረሻ
ከሲበል ዘዉር‘ላይ ላህሉ‘ሏህ መንገሻ፣
በአላህ መሀባ እሳት ለተለመጠጠዉ።
ሥሙን የከተበው፣ ጌታችን ጀባሩ
በጅብሪል ክንፍ‘ላይ ባይኑ በግንባሩ
በቀልቡ በራቀዉ ማእናና አኽባሩ
ማበሉን የዋኘዉ፣ የኛ ወቅት አህባሩ፣ በነኪር በሙንከር፣ ምላስ የኸጠጠዉ።
ሥሙን የከተበዉ፣ ወሲላ ደረጅ ላይ
ቡጡን የከተበው፣ አላንድ እንኳን ሰላይ
ኣማ‘ላይ ከተበው፣ ተከዉኑ ሆኖ አግላይ
ላሁት ላይ ከተበው፣ ላየው ሆኖ አዋላይ፣
ተመለይካ ተሰው ለተመረጠው
ሥሙን የከተበው፡ በየ-ጀነቱ ዕቃ
ሥሙን የከተበው በየ-በሩ ሳንቃ
ሥሙ ያጠፋው እጅግ የሳት ላንቃ
በሥሙ ያደነው የስንቱን ሰው ጫንቃ፣ የጀሀነም እሳት እንዳይለመጥጠው
ሥሙን የከተበው ሰማይ በየ-በሩ
ጀነት በየ‘ጉልቱ፣ ባለው በሚበሩ
በሹሃዳው እቃ በራቀው ኸበሩ
በጦር በጋሻቸው ገርሞ ማጥበርበሩ፣ በኑር መከዳቸው አላህ በመረጠው
በሱለይማን ኻተም፡ ስሙን የረቀመው
የየሱፍም ቀሚስ በሱ ቀመቀመው
ሂዝቡን ከያለበት ሥሙን የለቀመው
ስሙ በመጡረድ ጥፊ ጠረቀመው፣ ኢብሊስን ከሀድራው ጀሂም አፈረጠው።
ሥሙን የከተበው፡ በአህሉላህ ደረት
ጀነት በያቁቱ፣ በሉለዎ፣ በዱረት
ሥሙን የከተበው በሙንተሃ ሲድረት
ሥሙን ለሰዓዳ ያረገው መሰረት፣
ሥሙን በስንቱ ሆድ ሲሩን አስደፈጠው
የሥሙ መክተብያ ተቆጥሮ የማያልቀው
መለይካ-ሰው ቆጥሮት ምላሰ እማይዘልቀው
ለካ ረቡል‘ጀሊል ለጉድ‘ነው ሲኸልቀው
ሙናጢን ሊሰደው መደዱን ሊያፈልቀው፣
ስንቱ እሱን በማየት ተስንቱን ሊያበልጠው።
.
.
አላሁመ ሶሊ ዓላ ሙሀመዲ፣ መለይካ አንቢያን የበለጠው፣ ሲሩ ያልተገለጠው፣²
‹መጅሙዐቱል መዳኢኽ አል-አጀምያ»
(ሼህ ሰይድ ኢብራሂም-ጫሌ 1872-1947)›
@muhammednessim
መለይካ አንቢያን የበለጠው፣
ሲሩ ያልተገለጠው፣²
❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀
ሥሙን የከተበው፣ غገይብ ላይ በአዘል
ጀነት በየ‘ግንቡ፣ በየ‘ዛፉ ቀንዘል
በሱ-ነው አፍርቶ፣ ያገኘው መንዘልዘል
ጀነት ላይ ቢልጁዲ ወል-ከረሚል
አጅዘል፣
በጀሊል ልግስና ለሱ ለሚሰጠው።
.
ሥሙን የከተበው፣ ለአርዋህ መዳረሻ
በሃዉዱ መርጊያ‘ላይ በተስኒም መፍሰሻ
ባህረል መስጁር ዳር ዳር፣ አለ‘መጨረሻ
ከሲበል ዘዉር‘ላይ ላህሉ‘ሏህ መንገሻ፣
በአላህ መሀባ እሳት ለተለመጠጠዉ።
ሥሙን የከተበው፣ ጌታችን ጀባሩ
በጅብሪል ክንፍ‘ላይ ባይኑ በግንባሩ
በቀልቡ በራቀዉ ማእናና አኽባሩ
ማበሉን የዋኘዉ፣ የኛ ወቅት አህባሩ፣ በነኪር በሙንከር፣ ምላስ የኸጠጠዉ።
ሥሙን የከተበዉ፣ ወሲላ ደረጅ ላይ
ቡጡን የከተበው፣ አላንድ እንኳን ሰላይ
ኣማ‘ላይ ከተበው፣ ተከዉኑ ሆኖ አግላይ
ላሁት ላይ ከተበው፣ ላየው ሆኖ አዋላይ፣
ተመለይካ ተሰው ለተመረጠው
ሥሙን የከተበው፡ በየ-ጀነቱ ዕቃ
ሥሙን የከተበው በየ-በሩ ሳንቃ
ሥሙ ያጠፋው እጅግ የሳት ላንቃ
በሥሙ ያደነው የስንቱን ሰው ጫንቃ፣ የጀሀነም እሳት እንዳይለመጥጠው
ሥሙን የከተበው ሰማይ በየ-በሩ
ጀነት በየ‘ጉልቱ፣ ባለው በሚበሩ
በሹሃዳው እቃ በራቀው ኸበሩ
በጦር በጋሻቸው ገርሞ ማጥበርበሩ፣ በኑር መከዳቸው አላህ በመረጠው
በሱለይማን ኻተም፡ ስሙን የረቀመው
የየሱፍም ቀሚስ በሱ ቀመቀመው
ሂዝቡን ከያለበት ሥሙን የለቀመው
ስሙ በመጡረድ ጥፊ ጠረቀመው፣ ኢብሊስን ከሀድራው ጀሂም አፈረጠው።
ሥሙን የከተበው፡ በአህሉላህ ደረት
ጀነት በያቁቱ፣ በሉለዎ፣ በዱረት
ሥሙን የከተበው በሙንተሃ ሲድረት
ሥሙን ለሰዓዳ ያረገው መሰረት፣
ሥሙን በስንቱ ሆድ ሲሩን አስደፈጠው
የሥሙ መክተብያ ተቆጥሮ የማያልቀው
መለይካ-ሰው ቆጥሮት ምላሰ እማይዘልቀው
ለካ ረቡል‘ጀሊል ለጉድ‘ነው ሲኸልቀው
ሙናጢን ሊሰደው መደዱን ሊያፈልቀው፣
ስንቱ እሱን በማየት ተስንቱን ሊያበልጠው።
.
.
አላሁመ ሶሊ ዓላ ሙሀመዲ፣ መለይካ አንቢያን የበለጠው፣ ሲሩ ያልተገለጠው፣²
‹መጅሙዐቱል መዳኢኽ አል-አጀምያ»
(ሼህ ሰይድ ኢብራሂም-ጫሌ 1872-1947)›
@muhammednessim