Apostolic Church of Bole Hermon Branch


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


"፤ እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው፤"
(ኦሪት ዘዳግም 6: 4)

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


“የሐሤት ድምፅና የደስታ ድምፅ፥ የወንድ ሙሽራ ድምፅና የሴት ሙሽራ ድምፅ፦ እግዚአብሔር ቸር ነውና፥ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና የሠራዊትን ጌታ እግዚአብሔርን አመስግኑ የሚሉ ድምፅ፥ ወደ እግዚአብሔርም ቤት የምስጋናን መሥዋዕት የሚያመጡት ድምፅ እንደ ገና ይሰማል። የምድርን ምርኮ ቀድሞ እንደ ነበረ አድርጌ እመልሳለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር።”
ኤር33፥11
የተወደዳችሁ ቅዱሳን ሰላም ይብዛላችሁ !

እጅግ የተወደደችና የመሰዊያው አገልጋይ የሆነችው የእህታችን የዘማሪ አስቴር ሰይፋና የተወደደው ወንድማችን የወንድም ልዑል መኮንን የጋብቻ ስነ ስርዓተ የሚፈጸመው ጥቅምት 8,2013ዓ. ም በመቂ ሐዋርያዊት ቤ/ክ ይሆናል።
ቅዱሳን ሁላችን ለመገኘት ብናፍቅም ከጊዜው የተነሳ በስፍራው መገኘት ባንችልም በTelegram online .እና በ facebook የቃል ኪዳኑን ስርአት እናስተላልፋለን !በእናንተና በእግዚአብሔር ፊት ቃል ኪዳን ይገባሉ,የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ማስተላለፍ ትችላላችሁ,
“ሁሉም እያንዳንዱ ባልንጀራውን ይረዳው ነበር፥ ወንድሙንም፦ አይዞህ ይለው ነበር።”እንደሚል
አይዞህ አይዞሽ መባባሉም የቅዱሳን ልማዳችን ነው። እግዚአብሔር ይባርካችሁ !

@ACEBoleHermon


"የተወደደ ጊዜ"

እግዚአብሔር ከሰጠን ብዙ ስጦታዎች
አንደኛው ጊዜ ነው ለተቀበልን ሰዎች

የተሰጠን ጊዜ ለሁሉ እኩል ነው
አጠቃቀም እንጂ አንዱን ካንዱ የለየው ።

ይሄን ውድ ጊዜ ማሪያም አስተዋለች
ከጌታ እግር ስር ማረፍን መረጠች

ከአፉ ከሚወጣው ቃል እየተማረች በመለምለም መስክ ላይ ነፍሷን አሳረፈች ።

ዕረፍትን በማጣት ጠውልገን ያለነው
የነፍሳችን ክሳት ገርጥቶ ሚታየው

መንፈሳችን ደክሞ አቅምን ያጣነው
ውድ ጊዜያችንን ስላልተጠቀምን ነው ።

ንስሃ ሳትገባ እንዲሁ እየኖርክ
በተሰጠህ ጊዜ መጠቀም አቅቶህ

በቤቱ አለሁኝ ለምትለው ሳይቀር
ይህን ውድ ጊዜ መጠቀም ብንችል

በኑሮ በቤትህ በአገልግሎትህም
ተገልጦ ታያለህ የአምላክህን ክብር ።

ከእርሱ ጋር ዘወትር የምታሳልፋት
ከውድ ጊዜዎችህ የከበረችው ናት ።


“.... በመንፈሳዊም ቅኔ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ..”

@ACEBoleHermon


📌 በእርሱ ስናርፍ አምላክነቱን እናያለን

“ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ፤ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።”
መዝ 46፥10


በቄስ ወንደሰን ታደሰ
@ACEBoleHermon




📌 እግዚአብሔርን ማወቅ

• እግዚአብሔርን ማወቅ በመፅሐፍ ቅዱስ ትምህርት መሰረት ነው።

• እግዚአብሔርን ማወቅ በእግዚአብሔር ለመታወቅ መሠረት ነው።

• እስራኤል የተባለ ህዝብ ልቆ እና ገኖ የወጣበት ምክንያት አንድ ብቸኛ የሆነውን አምላክ በማወቁ ነው።

• ክርስቶስን ማወቅ እውነተኛይቱ የህያው እግዚአብሄር ቤተክርስትያን የተመሠረተችበት የመገለጥና የመዳን አለት ነው።

• ለህይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆኑት መንፈሳዊ በረከቶች ሁሉ እርሱን ለሚያውቁ ብቻ የተሰጡ ናቸው።

• ቤቱን የእውነት አምድ እና መሠረት ያደረገው ሚስጥር እግዚአብሔርን ማወቅ ነው።

• የሀጥያት ዋነኛ ምክንያት እግዚአብሄርን አለማወቅ ነው።

• ስምን በህይወት መፅሐፍ የሚያኖረው መንፈሳዊ ዕውቀት ነው።

ምንጭ፦በቄስ ኤልያስ ሽባባው
ከተጻፈው መጽሐፍ የተወሰደ

@ACEBoleHermon


📌ዘማሪ በረከት ደስታ

በክብር ዙፋን ወደአለህበት ወደአንተ ጉያ

@ACEBoleHermon












"፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?"
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3: 16)




"፤ ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፥ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልምን ያልማሉ፥ ጐበዞቻችሁም ራእይ ያያሉ፤"
(ትንቢተ ኢዮኤል 2: 28)






"የእስራኤል ህልውና በመቅደሱ እግዚአብሔር መገኘት ነው"




"የጠላት ተልዕኮ መቅደሱን ማፍረስ ነው"



20 last posts shown.

715

subscribers
Channel statistics