"የተወደደ ጊዜ"
እግዚአብሔር ከሰጠን ብዙ ስጦታዎች
አንደኛው ጊዜ ነው ለተቀበልን ሰዎች
የተሰጠን ጊዜ ለሁሉ እኩል ነው
አጠቃቀም እንጂ አንዱን ካንዱ የለየው ።
ይሄን ውድ ጊዜ ማሪያም አስተዋለች
ከጌታ እግር ስር ማረፍን መረጠች
ከአፉ ከሚወጣው ቃል እየተማረች በመለምለም መስክ ላይ ነፍሷን አሳረፈች ።
ዕረፍትን በማጣት ጠውልገን ያለነው
የነፍሳችን ክሳት ገርጥቶ ሚታየው
መንፈሳችን ደክሞ አቅምን ያጣነው
ውድ ጊዜያችንን ስላልተጠቀምን ነው ።
ንስሃ ሳትገባ እንዲሁ እየኖርክ
በተሰጠህ ጊዜ መጠቀም አቅቶህ
በቤቱ አለሁኝ ለምትለው ሳይቀር
ይህን ውድ ጊዜ መጠቀም ብንችል
በኑሮ በቤትህ በአገልግሎትህም
ተገልጦ ታያለህ የአምላክህን ክብር ።
ከእርሱ ጋር ዘወትር የምታሳልፋት
ከውድ ጊዜዎችህ የከበረችው ናት ።
“.... በመንፈሳዊም ቅኔ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ..”
@ACEBoleHermon
እግዚአብሔር ከሰጠን ብዙ ስጦታዎች
አንደኛው ጊዜ ነው ለተቀበልን ሰዎች
የተሰጠን ጊዜ ለሁሉ እኩል ነው
አጠቃቀም እንጂ አንዱን ካንዱ የለየው ።
ይሄን ውድ ጊዜ ማሪያም አስተዋለች
ከጌታ እግር ስር ማረፍን መረጠች
ከአፉ ከሚወጣው ቃል እየተማረች በመለምለም መስክ ላይ ነፍሷን አሳረፈች ።
ዕረፍትን በማጣት ጠውልገን ያለነው
የነፍሳችን ክሳት ገርጥቶ ሚታየው
መንፈሳችን ደክሞ አቅምን ያጣነው
ውድ ጊዜያችንን ስላልተጠቀምን ነው ።
ንስሃ ሳትገባ እንዲሁ እየኖርክ
በተሰጠህ ጊዜ መጠቀም አቅቶህ
በቤቱ አለሁኝ ለምትለው ሳይቀር
ይህን ውድ ጊዜ መጠቀም ብንችል
በኑሮ በቤትህ በአገልግሎትህም
ተገልጦ ታያለህ የአምላክህን ክብር ።
ከእርሱ ጋር ዘወትር የምታሳልፋት
ከውድ ጊዜዎችህ የከበረችው ናት ።
“.... በመንፈሳዊም ቅኔ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ..”
@ACEBoleHermon