ቢቢሲ አማርኛ | BBC Amharic


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


https://bbc.com/amharic

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


















#BBCNEWS #ቢቢሲአማርኛ
@BBCAmharic_Revives
በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ታላላቅ ውድድሮች ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ብስክሌት ብሔራዊ ቡድን ፈተና
በታዋቂው ቱር ደ ሩዋንዳ የብስክሌት ውድድር ላይ ቢቢሲ የኢትዮጵያ ተወዳዳሪዎችን ሁኔታ በቅርበት ተመልክቷል። የመወዳደሪያ ብስክሌት እና ትጥቅ፣ በቂ የዝግጅት ጊዜ እና ድጋፍ የሌላቸው ተወዳዳሪዎች ውድድሩን እንዳይጨርሱ ምክንያት እንደሆናቸው ተናግረዋል። የኢትዮጵያ የብስክሌት ስፖርት ፈተናዎች አገሪቱ ወደፊት በዘርፉ እንዳትሳተፍ እንቅፋት ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት በስፖርተኞቹ ላይ ፈጥሯል።
Powered by Physics and Affiliates®
@BBCAmharic_Revives
መልካም ቀን!😊




#BBCNEWS #ቢቢሲአማርኛ
@BBCAmharic_Revives
በቱርክ ሱፐር ሊግ የፌነርባቼ ተጨዋቾቸ በተሸናፊ ቡድን ደጋፊዎች ጥቃት ደረሰባቸው
ትላንት ዕሁድ በቱርክ ሱፐር ሊግ ትራብዞንስፖር እና ፌኔነርባቼ ካደረጉት ጨዋታ በኋላ የፌነርባቼ ተጨዋቾች ወደ ሜዳ በገቡ የትራብዞንስፖር ተጨዋቾች ጥቃት ደርሶባቸዋል።በፓፓራ ፓርክ የተደረገውን ጨዋታ ፌንርባቼ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት ረትቷል። ይህንን ድል ተከትሎ ደስታቸውን እየገለጹ በነበረበት ወቅት ከተቃራኒ ብድን ደጋፊዎች ጥቃት ተሰንዝሮባቸዋል።
Powered by Physics and Affiliates®
@BBCAmharic_Revives
መልካም ቀን!😊






#BBCNEWS #ቢቢሲአማርኛ
@BBCAmharic_Revives
በአማራ ክልል የሚካሄደው ግጭት እና የመንገዶች መዘጋት የደቀኑት የጤና ቀውስ
ለወሊድ ወደ ደሴ ሆስፒታል የሄደች እናት ለቀናት ወደ ቤቷ ሳትመለስ ለመቆየት ተገዳለች፣ ለነርቭ ህመማቸው የሚወስዱት መድኃኒት ያለቀባቸው አባት ሞታቸውን እየጠበቁ ነው፣ ለአእምሮ ጤና የሚወስደው መድኃኒት የተቋረጠበት ልጃቸው እና እሳቸው በስቃይ ውስጥ መሆናቸውን እናት ይናገራሉ፣ የጤና ባለሙያዎች የጠፉ በሽታዎች እንዳያንሰራሩ ስጋት ተፈጥሮባቸዋል...እነዚህን ታሪኮች ለቢቢሲ የተናገሩት መንገድ በተዘጋባቸው አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎች ናቸው።
Powered by Physics and Affiliates®
@BBCAmharic_Revives
መልካም ቀን!😊




#BBCNEWS #ቢቢሲአማርኛ
@BBCAmharic_Revives
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት በሁለት ወራት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ለጉብኝት አሥመራ ገቡ
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በሁለት ወራት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ከልዑካን ቡድናቸው ጋር ለሥራ ጉብኝት ወደ ኤርትራ ዋና ከተማ አሥመራ መግባታቸው ተገለጸ። የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል በኤክስ ገጻቸው ላይ እንደገለጹት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ዛሬ እሁድ መጋቢት 8/2016 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ አሥመራ ገብተዋል።
Powered by Physics and Affiliates®
@BBCAmharic_Revives
መልካም ቀን!😊






#BBCNEWS #ቢቢሲአማርኛ
@BBCAmharic_Revives
ማሊያዊ- ፈረንሳዊቷ አያ በፓሪስ ኦሊምፒክ መክፈቻ ላይ ትዘፍናለች መባሉ ያስነሳው ውዝግብ
በዓለም ላይ ስማቸው ከገነነ ሙዚቀኞች መካከል አንዷ ናት - አያ ናካሙራ። አያ በፈረንሳይኛ በመዝፈን ከቋንቋው ተናጋሪዎች ባሻገር በዓለማችን ተደማጭ ከሆኑ ጥቂት ሙዚቀኞች መካከል አንዷ ናት። በዚህም ከወራት በኋላ በፓሪስ በሚካሄደው የኦሊምፒክ ውድድር መክፈቻ ላይ እንድትዘፍን ተመርጣለች። ነገር ግን ይህ ውሳኔ በፈረንሳውያን ዘንድ ውዝግብን አስከትሏል። ለምን?
Powered by Physics and Affiliates®
@BBCAmharic_Revives
መልካም ቀን!😊



20 last posts shown.

4 489

subscribers
Channel statistics