ከጾም ማዕድ
በእዝነቱ ወደር የማይገኝለት አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ለሰው ልጆች የሚያዘንበው ፀጋ ተቆጥሮ የሚያልቅ አይደለም። በተለይም ደግም ለእኛ ለሙስሊሞች በየሰዓቱ፣ በየቀኑ፣ በየሳምንቱ፣ በየወሩ፣ በየአመቱ የእዝነት አዝመራውን ያለማቋረጥ ያዘንብልናል።
በአሁኑ ወቅትም አንድ ትልቅ የበረከት እንግዳ ጥላውን ዘርግቶ ወደ እኛ እንዲገሰግስ ከፈጣሪ ትእዛዙን ተቀብሎ እየተጣደፈ እነሆ ከቤታችን ገብቷል።
ይህ እንግዳ ረመዳን ይባላል።
ለመሆኑ የረመዳንና ባጠቃላይም የፆም ትሩፋቶች ምን ይሆኑ? ይህ አጭር ፅሁፍ እነዚህን ጉዳዮች ለመዳሰስ ይሞክራል።
በመጀመሪያ ፆም ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንመልከት።
ፆም በቋንቋ ትርጓሜው ከአንድ ነገር መታቀብ ነው። ለዚህም ምሳሌ አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ መርየምን እንዲህ በማለት እንድትናገር አዟት የነበረውን እንመልከት
إِنِّي نَذَرْتُ لِلرَّحْمَٰنِ صَوْمًا فَلَنْ أُكَلِّمَ الْيَوْمَ إِنسِيًّا
“እኔ ለአልረሕማን ዝምታን (ፆም) ተስያለሁ፤ ዛሬም ሰውን በፍጹም አላነጋግርም” (መርየም 19፤ 26)
በሸሪዓ ትርጓሜው ደግም ፆም ማለት ከማንኛውም ከሚያስፈጥሩ ነገሮች ፀሀይ ከወጣችበት ጊዜ አንስቶ እስከምትጠልቅበት ጊዜ ድረስ የፈጣሪን ትእዛዝ በማሰብ መታቀብ ማለት ነው።
የፆም ትሩፋቶች አጅግ በርካታ ሲሆኑ በተወሰነ መልኩ የሚከተሉትን ሀዲሶች እንመልከት።
❶. አቡ ሁረይራ አላህ ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንዳወሩት የአላህ መልክተኛ (ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይውረድ) እንዲህ ብለዋል
كل عمل ابن آدم له إلا الصيام فإنه لى وأنا أجزى به, والصيام جُنة فإذا كان يوم صوم أحدكم لا يرفث ولا يصخب ولا يجهل فإن شاتمة أحد او قاتلة أحد فليقل إنى صائم , مرتين , و الذى نفسى بيده لخلوف فم الصائم أطيب عند الله يوم القيامة من ريح المسك , و للصائم فرحتان يفرحهما : إذا أفطر فرح بفطرة , و إذا لقى ربه فرح بصومه
“የልዕልና ባለቤት የሆነው አላህ እንዲህ አለ፡- የአደም ልጅ ሥራዎቹ ሁሉ ለራሱ ናቸው፤ ፆም ሲቀር፤ እርሱ (ፆም) ለእኔ ነው፤ በእርሱም የምመነዳው እኔ ነኝ። ፆም ጋሻ ነው። አንድኛችሁ በፆመ ጊዜ ፀያፍ አይናገር፣ አይጩህ፣ ሌሎችን አያቂል።
ሌላ ሰው ቢሰድበው ወይንም ሊጋደለው ቢሞክር ሁለት ጊዜ እኔ ፆመኛ ነኝ ይበል። የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነችው እምላለሁ የፆመኛ የአፍ ጠረን አላህ ዘንድ የቂያማ ዕለት ከሚስክ ሽታ ይጣፍጣል።
ለፆመኛ ሁለት ደስታዎች አሉት፡- ሲያፈጥር ይደሰታል፣ (በዕለተ ቂያማ) ከጌታው ጋር ሲገናኝ ደግሞ ይደሰታል።” (አህመድ፣ ሙስሊምና ነሳኢይ ዘግበውታል)
በቡኻሪና በአቡዳውድ ዘገባ ደግሞ ይሄው ሀዲስ እንዲህ ተወርቷል “ፆም ጋሻ ነው። አንድኛችሁ ፆመኛ በሆነ ጊዜ ፀያፍ አይናገር፣ ሌሎችን አያቂል።
አንድ ሰው ሊጋደለው ቢሞክር ወይንም ቢሰድበው ሁለት ጊዜ እኔ ፆመኛ ነኝ ይበል። የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነችው እምላለሁ የፆመኛ የአፍ ጠረን አላህ ዘንድ የቂያማ ዕለት ከሚስክ ሽታ ይጣፍጣል።
ለእኔ ብሎ ምግቡን፣ መጠጡን ስሜቱን ይተዋልና፤ ፆም ለእኔ ነው፣ በእርሱም የምመነዳው እኔ ነኝ፤ እያንዳንዱ መልካም ሥራ በአሥር ይባዛል።”
ከላይ ከተጠቀሰው ሀዲስ የምንረዳው አንድ ሰው አንድ መልካም ሥራ ቢሠራ ያመልካም ሥራው በአሥር ይባዛለታል።
http://t.me/Dinel_Islam_Tube
ፆም ግን በዚህ የብዜት ስሌት የታጠረ አይደለም። ስንት እንደሚመነዳው የሚያውቀው አላህ ነው፣ በብዙ እጥፍ ድርብ። ፀጋው መቸም ለማይነጥፈው ለቸሩ ፈጣሪያችን እጅግ ምስጋና ይገባውና ምንም ሳይጎድልበት ይደራርብለታል።
❷. ከአብደላህ ኢብን ዐምር አላህ ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደተወራው ነብዩ (ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይውረድ) እንዲህ ብለዋል፡-
الصيام و القرآن يشفعان للعبد يوم القيامة, يقول الصيام :أى رب منعته الطعام والشهوات بالنهار فشفعنى فية و يقول القرآن: منعته النوم بالليل فشفعنى فية فيشفعان
“ፆምና ቁርአን ለአንድ ባሪያ የቂያማ ዕለት አማላጅ ሆነው ይቀርባሉ። ፆም ይላል፡- ጌታየ ሆይ በቀን ከምግብና ከስሜት ከልክየዋለሁና ምልጃየን በርሱ ተቀበለኝ፣ ቁርአንም ይላል፡- በሌሊት ከእንቅልፍ ከልክየዋለሁና ምልጃየን በርሱ ተቀበለኝ፤ አላህም ምልጃቸውን ይቀበላቸዋል።” (ትክክለኛ በሆነ ሰነድ አህመድ ዘግበውታል)።
❸. አቡ አማማህ አላህ ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደተናገሩት:-
أتيت رسول الله صلى الله عليه و سلم فقلت : مُرنى بعمل يدخلنى الجنة , فقال: عليك بالصوم فإنه لا عدل له
“ወደነብዩ (ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይውረድ) መጣሁና ጀነት የሚያስገባኝን ሥራ እዘዙኝ አልኳቸው። ነብዩም ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በፆም አደራ እልሃለሁ እርሱን የሚስተካከል የለም አሉኝ።
ለሁለተኛ ጊዜም መጥቸ እንዲሁ ጠየቅኳቸው እርሳቸውም በፆም አደራ እልሃለሁ አሉኝ።” (አህመድ፣ ነሳኢይና ሃኪም ዘግበውታል፤ ሀዲሱንም ትክክለኛ ነው ብለዋል)።
❹. ከአቡ ሠዒድ አል-ኹድሪይ አላህ ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደተወራው ነብዩ (ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይውረድ) እንዲህ አሉ፡-
لا يصوم عبد يوماً فى سبيل الله إلا باعد الله بذلك اليوم النار عن وجهه سبعين خريفاً
“አንድ የአላህ ባሪያ በአላህ መንገድ እየታገለ (ጅሃድ) ባለበት አንድ ቀንን አይፆምም አላህ ከዚህ ሰው ፊት እሳትን ለሰባ አመት ያክል የሚያስኬድ እርቀት ቢያርቅለት እንጅ።” (ከአቡ ዳውድ በስተቀር ‘ጀመዓው’ የሀዲስ ዘጋቢዎች ዘግበውታል)።
❺. ከሠህል ኢብኑ ሰዓድ አላህ ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደተወራው ነብዩ (ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይውረድ) እንዲህ ብለዋል፡-
إن للجنه باباً يقال له الريان , يقال يوم القيامة : أين الصائمون ؟ فإذا دخل آخرهم أُغلق ذلك الباب
“ለጀነት ረያን የሚባል በር አላት፡ የቂያማ ዕለትም ፆመኞች የት አሉ? ይባላል፡ ከእነርሱም የመጨረሻው ሰው ሲገባ ይሄ በር ይዘጋል።” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)።
እንግድህ ከላይ በተጠቀሱት ሀዲሶች አጠቃላይ የፆምን ትሩፋቶች አይተናል።
.............ይቀጥላል
🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂
🍀 ዲነል ኢስላም Tube
🔑"ለመልካም ነገር ቁልፍ ሁን!!"
http://t.me/Dinel_Islam_Tube http://t.me/Dinel_Islam_Tube