በረመዳን ምን ይጠበቅብናል ?
ክፍል ❷
እስቲ እነዚህን አንቀፆች እናስተውል፡-
قَالَ كَمْ لَبِثْتُمْ فِي الْأَرْضِ عَدَدَ سِنِينَ * قَالُوا لَبِثْنَا يَوْمًا أَوْ بَعْضَ يَوْمٍ فَاسْأَلِ الْعَادِّينَ * قَالَ إِن لَّبِثْتُمْ إِلَّا قَلِيلًا ۖ لَّوْ أَنَّكُمْ كُنتُمْ تَعْلَمُونَ * أَفَحَسِبْتُمْ أَنَّمَا خَلَقْنَاكُمْ عَبَثًا وَأَنَّكُمْ إِلَيْنَا لَا تُرْجَعُونَ
“በምድር ውስጥ ከዓመታት ቁጥር ስንትንቆያችሁ?” ይላቸዋል። “አንድ ቀንን ወይምከፊል ቀንን ቆየን። ቆጣሪዎቹንም ጠይቅ”ይላሉ። “እናንተ (የቆያችሁትን መጠን) የምታውቁ ብትኾኑ ኖሮ (በእሳት ውስጥበምትቆዩት አንፃር) ጥቂትን ጊዜ እንጂአልቆያችሁም” ይላቸዋል። “የፈጠርናችሁለከንቱ መኾኑን እናንተም ወደኛ የማትመለሱመኾናችሁን ጠረጠራችሁን?” (ለከንቱየፈጠርናችሁ መሰላችሁን?)” (አል-ሙእሚኑን 23፤ 112-115)
የቀብር ሰዎች ውድ ምኞት ለአፍታም ቢሆን ወደ ዱንያ መመለስ ነው። አንድ ጊዜ ወደ ህይወት ተመልሶ አላህን ማወደስ፣ ሱብሀነሏህ ማለት፣ አንዲት ጊዜም ቢሆን ለአላህ መስገድ…
እኛስ ከነርሱ አንማርም!? አሁንም ከእንቅልፋችን አንነቃም?! የሚጠብቀንን ፍጥጫ ለመጋፈጥ አንዘጋጅም!? አሁን ዱንያ ውስጥ ፊታችን ላይ የቆሙ ለመጪው አለም የምንሰነቅባቸው አጋጣሚዎች ብዙ ናቸው።
ይኸው ረመዳን ወዲህ እየጠራን ነው። እስኪ እጅጌያችንን አጠፍ አድርገን፣ ፍራሻችንን ትተን፣ ቤተሰቦቻችንን አንቅተን፣ በነፍሳችንና በስሜታችን ላይ የጂሀድ ባንዲራ አንግበን እንነሳ!!
🎈 ኑ የአላህን ጥሪ አሺ እንበል!
اسْتَجِيبُوا لِرَبِّكُم مِّن قَبْلِ أَن يَأْتِيَ يَوْمٌ لَّا مَرَدَّ لَهُ مِنَ اللَّهِ ۚ مَا لَكُم مِّن مَّلْجَإٍ يَوْمَئِذٍ وَمَا لَكُم مِّن نَّكِيرٍ
“ለእርሱ መመለስ የሌለው ቀን ከአላህከመምጣቱ በፊት ለጌታችሁ ታዘዙ። በዚያ ቀንለእናንተ ምንም መጠጊያ የላችሁም።ለእናንተም ምንም መካድ የላችሁም።” (አሽ-ሹራ 42፤47)
🎈 ሠዎችና ረመዳን
አዎን! ረመዳን በአመት አንዴ ብቻ የሚከሰት ታላቅ እድል ነው። ነገር ግን ሙስሊሞች በዚህ መልኩ ይተዳደሩት ይሆን? አንዳንዶች የዚህን ወር መምጣት እንደ ከባድ ሸክም ይመለከቱታል። ቶሎ እንዲያልቅም ይመኛሉ።
እነዚህ ከረመዳን የሚያተርፉት ከረህመት መባረር ብቻ ነው። ረመዳን ገብቶ ወጣ እንጂ በህይወታቸው ላይ የሚጥለው መልካም አሻራ የለም። አንዳንዶች ደግሞ የረመዳንን ዋጋ ተረድተዋል። እንዲህ አይነቱ ሰው የበረታ ክንዱን አዘጋጅቷል።
የቻለውን የአምልኮ ተግባር ለመፈፀም መንፈሱ ነቅቷል። ልቡ አብሮት ባይኖርም ብዙ ጊዜ ቁርአን ለማኽተም፣ ብዙ ለመስገድ፣ ብዙ ዒባዳዎችን ለመሥራት አቅዷል። ይህ አይነቱ ሰው መዳረሻ የነበሩትን የአምልኮ ተግባራት ግብ አድርጎ ይዟቸዋል።
ፆም ሊያረጋግጠው የመጣለትን ትልቁን አላማ ግን ዘንግቷል። በእርግጥ ረመዳን በእነዚህኞቹ ልብ ላይ ጥሩ ስሜት ጥሎባቸው ያልፍ ይሆናል። ግን ረመዳን እንደወጣ ቀናት እንዳለፉ ወኔያቸው አብሮ ይከስማል።
አንዳንዶች ደግሞ ረመዳንን ቀልብን ህያው ለማድረግ፣ ከእንቅልፉ ለማንቃትና በውስጡ ላይ የተቅዋን ችቦ ለማቀጣጠልና የኢማንን ሥር ለመትከል ምርጥ አጋጣሚ አድርገው ያዙት። እነዚህኞቹ የፆምን አላማ ሲያስሱ ቆዩና አላህ እንዲህ ሲላቸው አገኙት፡-
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُتِبَ عَلَيْكُمُ الصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى الَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጾም በነዚያ ከናንተበፊት በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ እንደ ተጻፈበናንተም ላይ ተጻፈ (ተደነባ) ልትጠነቀቁይከጀላልና።” (አል-በቀራ 2፤ 183)
አላህን መፍራት የሁሉም ዒባዳዎች መሪ ዓላማ ነው። አላህ እንዲህ አለ፡-
يَا أَيُّهَا النَّاسُ اعْبُدُوا رَبَّكُمُ الَّذِي خَلَقَكُمْ وَالَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ
“እናንተ ሰዎች ሆይ! የፈጠራችሁን እነዚያንምከናንተ በፊት የነበሩትን (የፈጠረውን) ጌታችሁንተገዙ፤ (ቅጣትን) ልትጠነቀቁይከጀላልና።”(አል-በቀራ 2፤ 21)
በልብ ውስጥ ባለው የተቅዋ መጠንም የሰው ልጅ ለአላህ ያለው ቅርበትና ርቀት ይለካል።
إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِندَ اللَّهِ أَتْقَاكُمْ
“አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህንፈሪያችሁ ነው። አላህ ግልጽን ዐዋቂውስጥንም ዐዋቂ ነው።” (አል-ሑጁራት 49፤ 13)
እንደነዚህ ባሉት ሰዎች አመለካከት- ረመዳን- ሠዎችን ከጌታቸው ለማቅረብ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር የመጣ ነው። የሰዎችን ልብ ከዱንያ እድፍ ሊያፀዳ እና ምርጡን ስንቅ እንዲሰነቁ ሊያግዛቸው የተከሠተ ነው።
وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ
“ተሰነቁም፤ ከስንቅም ሁሉ በላጩ ጥንቃቄ(አላህን መፍራት) ነው። የአእምሮዎችምባለቤቶች ሆይ! ፍሩኝ።” (አል-በቀራ 2፤ 197)
እርሶም የበረታ ክንዶን ይሰብስቡ። ኢስላም በዚህ ወር ውስጥ ያኖራቸውን የተቅዋ ምንጭ የሆኑ መሳሪያዎችን ተጠቀሙ። የልብና የአካል አምልኮዎችን በአንድነት ይከውኑ። ጥርጥር የሌለው እርግጠኛ ነገር እነዚህ ሦስተኞቹ ሰዎች የወሩ አትራፊዎች ናቸው።
በረመዳን ተጠቅመው ልባቸውን አንፅተዋል። ከዚያም ወደ አላህ የሚያስጠጋቸውን የህይወት ስንቅ ይዘዋል። ለአመታት የሚቆዩበትን ወኔ ሰንቀዋል። ወደ አላህ ከሚጓዙ የአላህ ወዳጆች መሀል ተሰልፈዋል።
🔑 የቀልብ መስተካከል ምልክቶች
ረመዳን የሚያመጣው የልብ ፅዳት ምንድን ነው?! ስትል ያየሁህ መሰለኝ። ልብ ውስጥ ያለው ኢማን ሲነቃቃ… ሥሮቹም ልብ ውስጥ ሲጠልቁ የልብ ፅዳት ምልክቶች መታየት ይጀምራሉ። ነብያችን እንዲህ ይላሉ፡-
ألا إن في الجسد مضغة إذا صلحت صلح الجسد كله، وإذا فسدت فسد الجسد كله ألا وهي القلب
“ንቁ! አካል ውስጥ ቁራጭ ሥጋ አለች። እርሷከተስተካከለች ሁሉም አካል ይስተካከላል።እርሷ ከተበላሸችም ሁሉ ነገር ይበላሻል። ንቁእርሷም ልብ ናት!!”
የዚህን ልብ ባለቤት ለመልካም ሥራዎች ሲጣደፍ፣ የአላህን ዲን ምልክቶችን ሲያከብር ትመለከተዋለህ። አላህ እንዲህ ይላል፡-
ذَٰلِكَ وَمَن يُعَظِّمْ شَعَائِرَ اللَّهِ فَإِنَّهَا مِن تَقْوَى الْقُلُوبِ
“(ነገሩ) ይህ ነው። የአላህንም የሃይማኖትምልክቶች የሚያከብር ሰው እርሷ ከልቦችየኾነች ጥንቃቄ ናት።” (አል-ሐጅ 22፤ 32)
..........ይቀጥላል
🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂
🍀 ዲነል ኢስላም Tube
🔑"ለመልካም ነገር ቁልፍ ሁን!!"
http://t.me/Dinel_Islam_Tube http://t.me/Dinel_Islam_Tube