በረመዳን ምን ይጠበቅብናል?
ክፍል ❿
ከሠዎች ጋር…
ለበጎ ተግባር መሮጥ ለሠዎች መልካም ውለታ ለመዋል መጣር ለቀልብ የሚያተርፈው ትልቅ የኢማን ፀጋ አለ።
ኢማን ይጨምራል። ሠውየውንም አላህ ዘንድ ተወዳጅ እንዲሆን ያደርገዋል። የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-
أحب الناس إلي الله أنفعهم، وأحب الأعمال إلي الله عز وجل سرور تدخله علي مسلم، أو تكشف عنه كربة، أو تقضى عنه دينا، أو تطرد عنه جوعا، ولأن أمشي مع أخي المسلم في حاجة، أحب إلي من أن أعتكف في المسجد شهراً، ومن كف غضبه ستر الله عورته، ومن كتم غيظاً – لو شاء أن يمضيه أمضاه – ملأ الله قلبه رضا يوم القيامة، ومن مشى مع أخيه المسلم في حاجته حتى يثبتها له، أثبت الله قدمه يوم تزل الأقدام، وإن سوء الخلق ليفسد العمل كما يفسد الخل العسل
“ከሠዎች መሀል አላህ ዘንድ ተወዳጁ ለሠዎች ጠቃሚ የሆነው ነው። አላህ ዘንድ ተወዳጅ ሥራ ሙስሊም ልብ ውስጥ የምታስገባው ደስታ፣ የምትገላግለው ጭንቅ፣ ከዱንያ የምትፈፅምለት ጉዳይ ወይም የምትገፈትርለት ረሀብ ነው።
በአላህ እምላለሁ መስጂድ ውስጥ ወር በሙሉ ኢዕቲካፍ አድርጌ ከምቀመጥ ለሙስሊም ወንድሜ ጉዳይ ብሮጥ እመርጣለሁ።
መበቀል እየቻለ ቁጣውን የሚደብቅ አላህ ነውሩን ይሸፍንለታል። ቁጭቱን የዋጠ ሰው የቂያም ቀን አላህ ልቡን በውዴታው ይሞላለታል።
የሙስሊም ወንድሙ ጉዳይ እስኪፈፀም ድረስ የተንቀሳቀሰ የሰዎች እግር ሲራጥ ላይ በሚስትበት ቀን አላህ እግሩን ያረጋለታል። ጥፉ ስብእና ልክ ኮምጣጤ ማርን እንደሚያበላሽ መልካም ሥራን ያበላሻል።”
ውድ አንባቢዎች!
በረመዳን ውስጥ ቢሠሩ የምንመርጣቸው ውስን መልካም ተግባራትን በሚከተለው የፅሁፋችን ክፍል ላይ እናቀርባለን። ዋናው ነጥብ ግን እንዳይዘነጋ። በረመዳን የምንሠራቸውን ተግባራት ከረመዳን ውጭም ማስለመድ አለብን።
ረመዳን ግን የመለማመጃ ጊዜ ነውና መልካም ነገሮችን በሙሉ መለማመድ አለብን። “መልካም ተግባርን ተለማመዱ፤ መልካም ነገር ልምድ ነውና!” ይባል የለ!!
1.ለሚስትና ለልጆች መልካም መዋል
ለሚስትና ለልጆች መልካም ውለታ መዋል የሚጀምረው እጃቸውን ይዞ ወደ አላህ መንገድ በመምራት፣ ወደ ጀነት የሚደረግ እሽቅድድም ላይ ፈጣን ተወዳዳሪዎች እዲሆኑ በማገዝ ነው። አላህ ይህን እንድናደርግ አዞናል። አንዲህ ብሏል፡-
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا قُوا أَنفُسَكُمْ وَأَهْلِيكُمْ نَارًا وَقُودُهَا النَّاسُ وَالْحِجَارَةُ عَلَيْهَا مَلَائِكَةٌ غِلَاظٌ شِدَادٌ لَّا يَعْصُونَ اللَّهَ مَا أَمَرَهُمْ وَيَفْعَلُونَ مَا يُؤْمَرُونَ
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጋዮች ከኾነች እሳት ጠብቁ።
በእርሷ ላይ ጨካኞች፣ ኀይለኞች የኾኑ መላእክት አልሉ። አላህን ያዘዛቸውን ነገር (በመጣስ) አያምጹም። የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ።” (አት-ተሕሪም 66፤ 6)
ከረመዳን ሥጦታ መጠቀም አለብን። የቤተሰቦቻችንን ኢማን ማሳደግ አለብን።
ስብእናቸውንም ወደ ላይ ከፍ ማድረግ አለብን። ረመዳን ከመግባቱ በፊት ከነርሱ ጋር እንቀመጥ። እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል የሚመጥነውን የፕሮግራም ዝርዝር ያውጣ።
ፕግራሙም የጠቀስናቸውን ሁለቱን ምሶሶዎች (ከአላህ ጋርና ከሠዎች ጋር) ማሟላት አለበት።
እንደዚሁም ወቅታቸውን በሙሉ ልናስተናብርላቸው ይገባል።
ግዴታ የሚሆንባቸውን ተግባር የሚፈፅሙበት መንገድም ልናመቻችላቸው ያስፈልጋል። ቤት ውስጥ እንደ መስጂድ አድርገው የሚይዙት ቦታ ማመቻቸት አለብን።
በየቀኑ አብረናቸው የምንሆንበት ለሁሉም የሚመች አጭር የመሰብሰቢያ ጊዜ እናድርግ። ከዚያም የቻልነውን ያህል አብረን ቁርአን እንቅራ።
ከንባባችንም ባሻገር ውስጣችን የተፈጠረውን የማስተንተን ስሜት እንለዋወጥ። ከዚያም አንድ ጠቃሚ የሆነ መፅሀፍ እናነባለን። ምናልባት ሪያዱሷሊሂን ወይም አንድ የሲራ መፅሀፍ ቢሆን እንላለን።
በስተመጨረሻ የቀን ውሎአችንን ተገማግመን መልካም የሠራን በማመስገን ያጓደለውን ደግሞ ስሜቱን በመጠገን እና ለራሳችን እና ለሙስሊሞች በሙሉ ዱዓ በማድረግ ስብሰባችንን እናጠናቅቃለን። ይህን ስብሰባ ከፈጡር በፊት ብናደርገው ደስ ይላል።
2.ችሮታና ልግስና
ይህ የበጎ አድራጎት በር ትልቅ ነው። በተለይም በረመዳን ሁላችን እንድንገባበት ያሻል። “የአላህ መልእክተኛ ቸር ነበሩ። በተለይም በረመዳን ጂብሪል ስለሚያገኛቸው ይበልጥ ቸር ይሆናሉ።
በረመዳን በየለሊቱ ጂብሪል ያገኛቸዋል። ቁርአን ያጣናቸዋል። የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ከተለቀቀ ጎርፍ የበለጠ ቸር ነበሩ።”
በዚህ ወር ውስጥ መልካም ተግባርን በመፈፀም እራሳችንን ለአላህ እይታ እናቅርብ። እርሱ የቸርነትና የሥጦታ ባለቤት ነው።
إن الله كريم يحب الكرماء جواد يحب الجودة، يحب معالي الأمور ويكره سفسافها
“አላህ ለጋስ ነው። ለጋሶችን ይወዳል። ቸር ነው። ቸሮችን ይወዳል። ታላላቅ ነገሮችን ይወዳል። ጅላጅል ነገሮችን ይጠላል።” ይላሉ የአላህ ነብይ (ሰ.ዐ.ወ)። ከቸርና ከለጋስ ሰዎች ባህሪያት መሀል ያለሀሳብ ያላቸውን ሁሉ መስጠታቸው ነው።
ይህ ስጦታቸው ገንዘብ፣ እውቀት፣ ጊዜ ወይም ጉልበት ሊሆን ይችላል። ቁምነገሩ ያላቸውን ሁሉ ይሠጣሉ፤ አይሰስቱም።
የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) አስማእ ቢንት አቢበክርን እንዲህ ብለው መክረዋታል።
لا تحصي فيحصي عليك
“አትቁጠሪ ይቆጠርብሻል!”
የዚህ ንግግር ትርጉም- ኢማም ኢብኑ ሐጀር ፈትህ የተሰኘው መፅሐፋቸው ላይ እንዳሉት- “ያልቃል ብለሽ ሶደቃ አትከልክይ ማለታቸው ነው። ይህ በረካን የሚያጠፋ ትልቅ ሰበብ ነው። ምክንያቱም አላህ ያለሂሳብ ይመነዳል።
ምንዳው ለማይተመን ጌታ የምንሰጠውን ስጦታ ደግሞ እንዴት እንተምነዋለን! ካላሰበበት አላህ እንደሚመግበው የሚረዳ ሰው ሳያስብና ሳይቆጥር ሊሰጥ ይገባል።”
ረመዳንን ችሮታና ልግስናን የምንለምድበት አጋጣሚ እናድርገው። ከገንዘባችን፣ ከጊዜያችን እና ከጉልበታችን አላህ ላይ አንሰስት። ያለሂሳብ ለአላህ እንለግስ።
በኢማም በይሀቂይ “ሹዐቡል ኢማን” በተሰኘው መፅሀፍ ላይ እንዲህ የሚል ተዘግቧል። “የዚድ ኢብኑ መርዋን ብዙ ገንዘብ መጣለት። ከዚያም እየዘገነ ለወንድሞቹ ይልክ ገባ።
እንዲህም ይል ነበር “እኔ ለወንድሞቼ ጀነት እንዲሰጣቸው እየተማፀንኩት ከገንዘቤ ብሰስትባቸው አላህን አፍረዋለሁ!!”
3.ዝምድና መቀጠል
በረመዳን ውስጥ ያለውን የዝምድና ሐቅ ከመናገራችን በፊት ተከታዩን ሐዲስ አብረን እንድናስተነትን እጋብዛለሁ።
ከሐዲሱ በነፍሳችን ላይ ያጓደልነውን ትርፍ እንገነዘባለን። በዱንያና በአኼራ ለሚሠጡ መልካም ስጦታዎች ያለንን ቸላተኝነትም እንመለከታለን።
...........ይቀጥላል
🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂
🍀 ዲነል ኢስላም Tube
🔑"ለመልካም ነገር ቁልፍ ሁን!!"
http://t.me/Dinel_Islam_Tube http://t.me/Dinel_Islam_Tube