ጳጳስ ፍራንሲስን ለመግደል የተሸረበ ሴራ በእንግሊዝ የስለላ ድርጅት ማክሸፍ መቻሉ ተነገረ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስን ወደ ኢራቅ በሄዱበት ወቅት ለመግደል የታቀደው ሴራን የብሪታንያ የስለላ ድርጅት ባደረገው ጥቆማ መሰረት መክሸፉን በቅርቡ የህይወት ታሪካቸውን በሚያትተው ዘገባ ላይ ይፋ ሆኗል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመጋቢት 2021 በባግዳድ ካረፉ በኋላ፣ እርሳቸውን ለመገደል በሁለት አጥፍቶ ጠፊዎች ኢላማ ተደርገው ነበር።
በኋላም ሁለቱም አጥቂዎች ተጠልፈው ተገድለዋል ሲል የጣሊያን ጋዜጣ ኮሪየር ዴላ ሴራ ባሳተመው ዘገባ ላይ ተገልጿል። በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት ከሶስት ቀናት በላይ በተካሄደው ጉብኝቱ በሊቃነ ጳጳሳት ለመጀመሪያ ጊዜ በኢራቅ የተደረገ ሲሆን ከፍተኛ የጸጥታ ኃይል ተሰማርቷል።
ይህንን የግድያ ሴራ የእንግሊዝ የስለላ ድርጅት ለኢራቅ ፖሊስን አስጠንቅቆ የነበረ ሲሆን እነሱም ጉዳዩን ደርሰውበታል።በጳጳሱ ጉብኝት ወቅት አንዲት በፈንጂዎች የተጠመደች አጥፍቶ ጠፊ ወጣት ራሷን ለማፈንዳት ወደ ሞሱል እያመራች ነበር።እናም አንድ ቫን ተሽከርካሪ በተመሳሳይ አላማ በከፍተኛ ፍጥነት ሲንቀሳቀስ ተደርሶበታል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በማግሥቱ ጥቃት ሊሰነዝሩ በሚፈልጉ ሰዎች ላይ ምን እንደተፈጠረ አንድ የደህንነት ባለሥልጣንን እንደጠየቁ ተናግረዋል ።
ባለሥልጣኑም ከእንግዲህ የሉም የኢራቅ ፖሊስ ጠልፎ ወስዷቸዋል የሚል ምላሽ ሰጥቷል። በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ላይ የሚያወጋው ሆፕ የተሰኘው መጽሐፍ በጥር 14 ለንባብ ይበቃል። ሮይተርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው ቫቲካን በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጥ ለቀረበለት ጥያቄ ወዲያውኑ ምላሽ አልሰጠም።
@Ewunet_Media