ትናንት ምሽት በሬክተርስኬል 4.9 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱ ተነገረ
የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ድረገጽ ትናንት ምሽት 4:41 ላይ ከመተሐራ 13 ኪሎ ሜትር ርቀት የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደነበር አመልክቷል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከሰቱ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶችን የሚከታተለው ተቋሙ መሬት መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 4.9 የተመዘገበ ጠቅሶ ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ መሰማቱም ተነግሯል። በተጨማሪም ዳጉ ጆርናል ከተከታታዮች አንደሰማዉ ከሆነ በአዲስአበባ ካዛንቺስ ፣ ጀሞ (1፣2እና3) ፣ አያት ፣ ቱሉዲምቱ እና ቂሊንጦ ኮንዶሚኒየም ንዝረቱ ተሰምቷል ያሉን ሲሆን በክልል አካባቢዎችም እንደ በአሰበተፈሪ ፣ መተሐራ እና ሱሉልታ መሰማቱን የዳጉ ጆርናል ተከታታዮች ተናግረዋል።
@Ewunet_Media