ከቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ጫማዎችን የሰረቀው ግለሰብ በ18 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ
ተከሳሽ ደምሴ ደሳለኝ የተባለው ግለሰብ በ1996 ዓ.ም ተደንግጎ የወጣው የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 669(3)ለ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ ማይገባውን ብልፅግና ለማግኘት በማሰብ የወንጀል ድርጊቱን ፈጽሟል፡፡ በጉራጌ ዞን በምኁር አክሊል ወረዳ ሀዋርያት ከተማ ውስጥ ሰላም መንደር ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በሚገኘው ሀዋርያት ፅርሀ ፅዮን የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ህዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም በግምቱ ከሌሊቱ 7፡00 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ ወንጀል ለመፈፀም እንደሚያመቸው በከተማው የተወሰነ ማብራት ቆጣሪ ሄዶ ካጠፋ በኋላ የዘጠኝ ሰዎችን ጫማ ሰርቋል፡፡
ህዳር 21 ለሚከበረዉ ክብረ በዓል መጥተው ቤተ-መቅደስ በራፍ ጫማቸውን አውልቀው ቤተመቅደስ ከገቡ በኋላ ተከሳሽ በለበሰው ጃኬት ዘጠኝ ጫማ ሰርቆ ከቤተክርሰቲያኑ ሲወጣ በክትትል በቤተ-ክርስቲያን በር ላይ በፖሊስ የተያዘ በመሆኑ አስቦ በፈፀመዉ በከባድ ስርቆት በወረዳው የመጀመረያ ደረጃ ፍ/ቤት ተከሷል።ተከሳሽ የተከሰሰበት ተደራራቢ ክስ ከደረሰው በኋላ የእምነት ክህደት ቃሉ ሲጠየቅ ክሱ እንደማይቃወም ወንጀሉ መፈፀሙን በዝርዝር ያስረዳ በመሆኑ ባመነው መሰረት ጥፋተኛ መባሉን የጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ ኤልያስ ሰብለጋ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
በዚህም በመሰረት ችሎቱ ግራ ቀኙ ከተመለከተ በኋላ በቀን ታህሳስ 15 ቀን በዋለዉ የወንጀል ችሎት ተከሳሹ ያርማል ሌላውንም ማህበረሰብ ይህን መሰል ወንጀል ከመፈፀም ያስተምራል በሚል በ18 ዓመት ፅኑ እስራት የቅጣት ውሳኔ የጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ ኤልያስ ሰብለጋ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
@Ewunet_Media