የጡት ካንሰር ህመም በወጣት የእድሜ ክልል ባሉ ሴቶች ላይ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱ ተገለፀ
የጡት ካንሰር የሚጠቁ ሴቶች በወጣትነት እድሜ ላይ ያሉ መሆኑ በሽታውን ከሌላው ጊዜ በተለየ አሳሳቢ እንዲሆን አድርጎታል።
በርካታ ሴቶች ምልክቶቹን ባለማወቅ ለረጅም ጊዜ ከህመሙ ጋር ቆይተው ነገሩ ስር ከሰደደ በኃላ ወደ ህክምና ተቋማት ይመጣሉ። ይሄም ችግሩ ህክምናው ተሰጥቶ የመዳን እድላቸው በጣም አነስተኛ ያደርገዋል ሲሉ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በቀዶ ህክምና ክፍል ውስጥ የጡት እና የኢንዶክሪም ሰርጅን ዶክተር ህይወት የሺጥላ ለብስራት ሬድዮና ቴሌቩዥን ተናግረዋል።ኢትዮጲያ ውስጥ ሴቶች ላይ ከሚከሰቱ ካንሰሮች ሁሉ የጡት ካንሰር የመጀመሪያውን ደረጃ ይዞ ይገኛል። እንዲሁም ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በዓመት 16 ሺህ አዳዲስ የህመሙ ተጠቂዎች ሪፖርት ይደረጋል።
እንዲሁም ወደ 9 ሺህ ያህል ሞት በጡት ካንሰር ምክንያት ሪፖርት እንደሚደረግ ጥናቶች ያሳያሉ ብለዋል።በመሆኑም ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ከቸርችል ጤና ጣቢያ ጋር በመሆን አንዲት ሴት የጡት ምርመራ ማድረግ እንድትችል ቸርችል ጤና ጣቢያ ላይ የተቋቋመው ዋንስቶፕ ክሊኒክ የሚባል ከጀርመን ፕሮጀክት ጋር በመተባበር እየሰሩ እንደሚገኙ ገልፀዋል። በዚህ ፕሮጀክት ላይ ወደ 200 የሚሆኑ ሴቶች የጡት ካንሰር ቀዶ ህክምና ማድረጋቸውንም ገልፀዋል ።
በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የተሻለ የጡት ካንሰር ህክምና ለመስጠት እየተሞከረ እንዳለ የገለፁት ዶክተር ህይወት ህክምናውን የሚሰጡ የጤና ባለሙያዋች በማሰልጠን በጡት የቀዶ ህክምና ሰብ ስፕሻላይዝድ ያደረጉ ሀኪሞች ህክምናው እንዲሰጡ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል። እንዲሁም የኬሞ ቴራፒ የጨረር ህክምና እንቅስቃሴ እያደረጉ እንዳለ ጨምረው ገልፀዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሁለተኛ ማሽን ለማስገባት እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን አክለዋል በመሆኑም ለረጅም ጊዜ የጨረር ህክምና ወረፋ የሚጠብቁ ሰዎችን እንግልት ይቀንሳል። ወረፋ በመጠበቅ ህይወታቸው የሚያልፍ በርካታ ሴቶች ህይወት መታደግ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል። የጡት ካንሰር ቀድሞ ከተመረመረና ህክምናው ቶሎ ከተወሰደ ወደ ቀድሞ የኑሮ እንቅስቃሴ መመለስ እንደሚቻልና መዳን እንደሚቻል እንዲሁም ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በተቻለው አቅም ሴቶች ቶሎ ወደ ህክምና ቦታ እንዲመጡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እየሰራ እንደሚገኝም ዶክተር ህይወት የሺጥላ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።
@Ewunet_Media