ግርምቢጥ 🌀
ክፍል አራት 📖
✨ ጴጥሮስ የታምራት ሙዚቃ ልቡን ለሁለት ሰነጠቀው። አመነታና ያወጣውን ስልክ ወደ ኪሱ መልሶ በሀሳቡ ባህር ነጉዶ ሳያስበው ሰዓቱ አለፈ። ከሀሳቡም ሲመለስ የሰዓቱን መንጎድ ሲመለከት በድንጋጤ ከካፍቴሪያው ወጥቶ ወደ ቤቱ አመራ። እቤት እንደደረሰ ግን የካፍቴሪያው ሀሳብ በድጋሚ በጭንቅላቱ መመላለስ ጀመረ። አስቦ አስቦ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ወሰነና ደወለላት። 🎶🏃♂️
📞 ማክዳ፦ "ሄሎ"
ጴጥሮስ፦ "ሄሎ ማኪ"
✨ ማክዳ ምንም እንኳን ሁሉም ማኪ እያለ ቢጠራትም የጴጥሮስ ሲሆን ግን ይለይባታል። የሚጠራት ሳይሆን በስሟ የተጠራ ልዩ ዜማ የሚያዜምላት ነው የሚመስላት። ከደወለላት ዓመታት ተቆጥረዋል። የሷንም ስልክ ማንሳት ስላቆመና በሌላ ስልክ ብትደውልም እሷ መሆኗን ሲያውቅ ስለሚዘጋው ተስፋ ቆርጣ ትታዋለች። ብቸኛ ነገሩን ማስተካከል አቅም አለው ብላ የምታስበው ሰለሞንም "አይሆንሽም ተይው" ከማለት ውጪ ሌላ ምላሽ ከአንደበቱ ሲጠፋ ጭርሱን ተስፋ ቆርጣ ነበር። እና ይህ ሰው ነው ከአመታት በኋላ ስሟን እየጠራ የሚገኘው። 💔📱
"ተደገመ ማኪ"
እየተርበተበተች፦ "አ...አ...አ አቤት"
"እንዴት ነሽ?"
"አለሁ" አጭር መልስ ሰጠች።
"አውቀሽኛል?"
"አዎ"
"ፈልጌሽ ነበር" የጴጥሮስ ድምፅ ላይም ፍርሃት ይነበባል። 😟
"እና?"
"ላግኝሽ"
"እሺ"
🚶♂️ ንግግሩን መቀጠል ከበደው፤ ስልኩን ለመዝጋት ቸኮለ። "እሺ በቃ ቦታውንና ሰዓቱን ቴክስት አደርግልሻለሁ" የሷን ምላሽ ሳይጠብቅ ዘጋውና ራሱን ለማድመጥ ሞከረ። "ምንድነው የሚሰማኝ?" የሚሰማውን እንኳን መለየት አቃተው። እንደ ምንም እየተደናበረ ከሁለት ሰዓት በኋላ ሰፈራቸው በሚገኙ ካፍቴሪያ እንገናኝ የሚል ቴክስት ላከላት። ያቺ ቤት ሁለተኛ ቤታቸው ቢባል ማጋነን አይሆንም፤ ለዛ ነበር እሱን ቤት የመረጠው። 🏠☕️
⏳ ሰዓቱን ጠብቆ ወደተቀጣጠሩበት ቤት ሄደና ቦታ ያዘ። ማክዳ የለችም፤ 30 ደቂቃ አለፈ። ግን እሱ በስልኩ ቲክቶክ ላይ ተጠምዶ ስለነበር አልታወቀውም። ከስልኩ አይኑን የነቀለው ማክዳ መጥታ አጠገቡ ስትቀመጥ ነው። ተርበተበተ፤ ቃሉ ከአፉ ለመውጣት ሰነፋ መፋጠጥ ሆነ። በዚህ መሀል ዝምታውን ሰብራ፦
"ለምንድነው የፈለከኝ?" አለችው። 👁️
"ኧ... ደህና ነሽ?" አላት።
"አለሁ! መቼም ለዚህ አይደለም የፈለከኝ" እንደ አራስ ነበር ተቆጣች። 😡
"እራሱን ለማረጋጋት እየሞከረ፦ "ልክ ነሽ ግን ያው ሰላምታ ይቀድማል ብዬ ነው"
💔 የሱን ንግግር እንዳልሰማች ሆና "ለምንድነው የተውከኝ?" የሚል ድምገተኛ ጥያቄ ጠየቀች። ያላሰበበት ጥያቄ ስለሆነ መረጋጋት ጀምሮ የነበረውን ድጋሚ መረበሽ ሆነ። ጥያቄውን ድጋሚ እያነሳች እንባዋ በሁለቱም አይኖቿ መፍሰስ ጀመረ።
"እንዴ ማኪ" አላት።
💧 "አታባብለኝ! መልስ ብቻ ነው የምፈልገው። እንዲህ ፊት ለፊትህ ተቀምጬ ይሄን ጥያቄ የምጠይቅበትን ቀን ሁሌም እጠብቀው ነበር። እባክህ መልስልኝ!" አለችው ።
እየተርበተበተ ያላቀደበትን ነገራት፦ "አንተ ልክ ነህ አትሆነኝም እኔ ነኝ የተሳሳትኩት" ብላ በተቀመጠበት ጥላው ሄደች። 🏃♀️🚶♂️
ክፍል አምስት ይቀጥላል...