ግርምቢጥ 🌀
ክፍል አምስት 📖
✨ የቅዱስ ዮሐንስ ገዳም ውስጥ ዛሬ ዓመታዊ በዓሉ የሚከበርበት ቀን ስለሆነ በገዳሙ ውስጥ ያሉ ምእመናን እና በገዳሙ አቅራቢያ የሚኖሩ በርካታ ምእመናን በሌሊት ማህሌት ገብተዋል። ከነዚህም ውስጥ አንዱ ሰለሞን ነው። በቆመበት ከእንቅልፍ ጋር ይታገላል። ጠንከር ብሎ ነው የሰነበተው፤ ከአለም ጫጫታ ርቆ ከራሱና ከመንፈሱ ጋር ብቻ በገዳም ቆይታው ራሱን አዳምጧል። መንፈሳዊ ህይወቱን አድሷል፤ ከፈጣሪውም ጋር ታርቋል። ⛪️🙏
🕯️ አሁን ግን ሀሳቡን ሰብስቦ ማህሌቱን መሳተፍ ተሳነው። ከእንቅልፍ ጋር ሲታገል ቆይቶ እንቅልፍን አሸነፍኩ ሲል ደግሞ በሀሳብ ባህር ሰመጠ። ድል ያለ ሰርግ... እናቱ በደስታ ሰክረው ከፍ ዝቅ ሲሉ... እትዬ ብርቄ በኩራት ተዘፍቀው ታዳሚውን እያዩ እጅ ሲነሱ... ድንገት ያለበትን ረስቶ ፊቱ ላይ እስኪነበብ ድረስ በስጨት አለ። የማይሆን ሀሳቡ ቅዠት ይመስል በሚሰማ ድምፅ ተቁነጠነጠ። 💭😟
💧 ድንገት በሁለቱም አይኖቹ እንባ መፍሰስ ጀመረ። "ከቆይታ በኋላ ድኛለሁ ስል፣ ወጣሁት ያልኩት ህመም ተመልሶ መጣ" እያለ ሀሳቡን ወደ ሌላ ለማድረግ ሞከረ። የሰነበተበት የቤተክርስቲያን ስርአት ረዘመበት። እንደምንም የቤተክርስቲያኑን ስርአት ከጨረሰ በኋላ ወደ በአቱ ሄደና መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ ጀመረ። 📖⛪️
📖 በአጋጣሚው የገለጠው መጽሐፍ ቅዱስ ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 29 ቁጥር 35 ላይ አረፈ። የያዕቆብና የራሄል ታሪክ... ያዕቆብ ራሄልን ወደደ፤ ሊያገባትም ተመኘ። እሷንም ለማግባት ለአባቷ ሰባት አመት አገለገለ። ነገር ግን የራሄል አባት ለያዕቆብ ራሄልን ሳይሆን ታላቋን (ሊያ) ሰጠው። የፈለገውን ያላገኘው ያዕቆብ ይህን ጉዳይ ሲጠይቅ፣ ራሄልን ለማግኘት ሌላ ሰባት አመት ማገልገል እንዳለበት ተነገረው፤ አደረገውና አገኛት። 📜✨
🎯 ሰለሞን ይህን ሲያነብ ስሜቱ እየተቀያየረ ነበር። ልክ የታሪኩ መጨረሻ ላይ ሲደርስ "ይችላል!" ብሎ አጨበጨበ። "ልክ ነኝ! አደርገዋለሁ!" እያለም ደጋግሞ ጮክ ብሎ ተናገረ። ቆይቶ ነበር ወደ ራሱ መለስ ሲል ያለበትን ያስተዋለው። በሀፍረት አንገቱን ደፍቶ ተቀመጠ። "ካሁን አሁን ድምፄን የሰሙ ሊገስፁኝ ይመጣሉ" በሚል መሳቀቁ ሊገድለው ደረሰ። 😰🤐
...ይቀጥላል...