TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
  • flag English
    Site language
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Sign In
  • Catalog
    Channels and groups catalog Search for channels
    Add a channel/group
  • Ratings
    Rating of channels Rating of groups Posts rating
    Ratings of brands and people
  • Analytics
  • Search by posts
  • Telegram monitoring
የጥበብ ብልጭታ

29 Jan, 11:35

Open in Telegram Share Report

ግርምቢጥ 🌀

​ክፍል ሦስት 📖

​✨ ቤተክርስቲያን እንደደረሱም እትዬ ብርቅነሽ ነገሩን ቁርጥ አደረጉት። "ነገ ሽማግሌዎቹ ይመጣሉ፤ ትዳሩን እንቀበላለን" አሏት። ዳናዊት ያልጠበቀችው ባይሆንም በድንጋጤ ተዋጠች። "እንዴ እማ! ይህን መወሰን ያለብኝ እኮ እኔ ነኝ። አሁን ስርአቱ እንዲህ አይደለም፤ አውቄውና ወድጄው ነው ሽማግሌ የሚላከው" ብላ በትዝብት እያየቻቸው ለመከራከር ሞከረች። ⛪️🤨

​👵 እትዬ ብርቄ ግን አመረሩ። "ስርአቱስ እሱ አልነበረም! ዘመናዊነት ብላችሁ አበላሻችሁት እንጂ 'ተዋውቀን፣ ተፋቅረን' እያላችሁ ሰውነታችሁን በዝሙት እያረከሳችሁ ነው። እኔ ገና ሳልወለድ፣ ከእናቴ ሆድ ሳለሁ ነው የታጨሁት። አባቴ ከቅርብ ወዳጁ ጋር ሴት ልጅ ስትወልድ ለልጄ ብለው ቃል የተገባቡት ነው። ምን ጎደለብኝ? አተረፍኩ እንጂ አልከሰርኩም!" አሏት። በስተመጨረሻም ትዳሩን መቀበል ወይም የእሳቸውን እናትነት ማጣት ያላት ምርጫ እንደሆነ አስረግጠው ነገሯት። 👵🚫

​ዳናዊት ባትስማማም ተስማማች። ምሽቱን እንቅልፍ በአይኗ ሳይዞር አደረ። ጴጥሮስና ኤልዳናም በጉዳዩ ላይ ሀሳብ እንዲሰጡ አልተፈቀደላቸውም። 🌙🛌

​💍 በነጋታው ዳናዊት ከሰአት ስራ አስፈቅዳ ወደ ቤት ተመለሰች። የሽምግልና ስርአቱም በባህሉ መሰረት ተከናወነ፤ ለሰርጉም የአንድ ወር ቀጠሮ ተቆርጦ ተለያዩ። ነገር ግን አሁንም ሰለሞን ሄደበት ከተባለበት ገዳም አልተመለሰም። የሰለሞን መጥፋት ነገሩን ለሁሉም ግራ አጋቢ አድርጎታል። ዳናዊት ከዳኒ ጋር ያላት ግንኙነት ከመደዋወል አልፎ ወደ ተደጋጋሚ መገናኘት አምርቷል። አንድ ቀን ከስራ በኋላ ሻይ ቡና ተባብለው ወደ ቤቷ ከሸኛት በኋላ፣ መለያያቸው ላይ ሳታስበው ከንፈሯን ሳማት። 💋😲

​💧 በድንጋጤ "ውሃ" ሆነች። ምንም ማድረግ አልቻለችም፤ በዛው ቀን ማታ ዳኒን ደግማ ላለማግኘት ወስና ነበር፤ ነገር ግን አልቻለችም። ሁሉንም ከአቅሟ በላይ የሆነባትን ነገር ጊዜ ይፍታዉ ብላ ለጊዜ ሰጠችው። ጊዜያት ነጎዱ፣ ሰርጉም ተቃረበ። እትዬ ብርቄም ከሰለሞን ቤተሰቦች ጋር እየተናበቡ ወገባቸውን ታጥቀው ድግሱን ጀማምረውታል። 🥘👵

​🚶‍♂️ በዚህ ሁሉ ውስጥ ዝምታው ልክ እንዳልሆነ ያመነው ጴጥሮስ ወደ ሰለሞን ቤተሰቦች ሄደ። ሰለሞን በትክክል የት እንደሚገኝና ሂደቱ እንዴት እንደተጀመረ ለማጣራት ሞከረ። ቤተሰቦቹ ግን "ሰለሞን ራሱ ነው 'ልንጋባ ወስነናልና ሽማግሌ ላኩ፣ እኔ ለትዳሬ ፀሎት ለማድረግ ገዳም መሄድ አለብኝ' ያለን" የሚል መልስ ሰጡት። የሰለሞን የት እንዳለ አለመታወቅ ግን ለጴጥሮስ ሊዋጥለት አልቻለም። ❓🤔💭

​💔 ጴጥሮስ ከነሱ መልስ አንድ ካፌ ቁጭ ብሎ እንዲሁ ሲብሰለሰል 😔 አንድ ሲሸሸዉ የነበረዉን ነገር ለማድረግ ወሰነ፤ የልጅነት ፍቅረኛዉን የሰለሞንን እህት የቀድሞ ፍቅሯን ቀስቅሶ እዉነቱን ማወጣጣት። ✊🔥

​የሰለሞን እህት ማክዳ ለጴጥሮስ የመጀመሪያዉ ነች። ለመጀመሪያ ጊዜ ያቀፋት፣ የያዛት፣ ያወራት፣ የሳማት የሄዋን ዘር 👩‍❤️‍👨። ገና 10 ኛ ክፍል እያለ ነበር 8 ኛ ክፍሏ ማክዳ ጋር በፍቅር እፍ ያለዉ። በሷ ምክንያት ከሰለሞንም ከእህቶቹም ጋር ደጋግሞ ተጣላ 😠። በእሷ የመጣን በአይኑ እንደመጣ ቆጠረዉ። በሰለሞንና በማክዳ የወንድምነትና እህትነት ጠብ ዉስጥ ዘራፍ ባይ ሆነ 🛡️። በማክዳና በእህቶቹ በተለይ በእኩያዋ ኤልዳና ኩርፌያ ዉስጥ ተደርቦ አኩራፊ ሆነ። የእናቱን "ሁለተኛ ከእሷ ጋር ባይክ" ቁጣ ከሰፈሪ የወላጅ ግሰፃ ይልቅ እንደ ደጋግሞ የሚሰማዉ ሙዚቃ ቆጠረዉ 🎧። በሷ ቤተሰቦችም "ልጃችንን አባለገ" በሚል እንደ እርጉም ዉሻ ተጠላ 🐕🚫። ብቸኛ ፌት ያልነሳዉ ጓደኛዉ ሰለሞን ብቻ ሆነ። 🏠🤝

​በእንዲህ አይነት ሁኔታ 12 ን ጨርሶ ሐዋሳ ዩንቨርስቲ ገባ። ማክዳም አስረኛ ክፍል ደረሰች። በሱ ከሰፈሩ መራቅ ቤተሰቦቿ የመገላገል ስሜት ተሰማቸዉ፤ ነገር ግን እነሱ በስልክ ቀጠሉ 📞💞። ጴጥሮስ በዩንቨርስቲዉ ከገኛቸዉ ጓደኞቹ ጋር ሆኖ ቀስ በቀስ ከተለያዩ ሴቶች ጋር ያልተገባ ድርጊት ማድረግ ጀመረ። በዚህ በሚሰማዉም   ፀፀት ማክዳን ራቃት 😞💔። ነገር ግን በዚህ ድርጊት ጠልቆ ከመግባቱ በፊት እራሱን አወጣ፤ ነገር ግን ከልቡ ወዳልወጣችዉ ማክዳ ዳግመኛ መመለስን አልፈለገም 🛑❤️‍🩹። እስካሁንም በእህቱ ጉዳይ እጁን ያላስገባዉ ይህን ላለመቀስቀስ ነበረ።

​አሁን ግን ወስኗል፤ ለማክዳ ለመደወል ስልኩን ልክ ሲያነሳ 📱  😰 ከተቀመጠበት ካፍቴሪያ ጎን ካለ ሱቅ የሚወጣ አንድ ዘፈን ጆሮዉ ጥልቅ አለ 🎶👂፦

​"እንኳን ልሄድ እኔ ራሴ ካለችበት፣
መጣች ቢባል ያን በደሌን ረስታው ድንገት፣
አይን የለኝም አይኗን በአይኔ የማይበት... 🙈

ትቻት ሄጄ ጥቅሜን አስበልጬ፣ ንፁህ ልቧን ያን ፍቅሯን ረግጬ... 💔

ሰላሟን ህመም ልዘራበት፣ አልሄድም ረስታኝ ትኑርበት!" 🚶‍♂️🕯️

​...ይቀጥላል...

244 0 2 5
Catalog
Channels and groups catalog Channels compilations Search for channels Add a channel/group
Ratings
Rating of Telegram channels Rating of Telegram groups Posts rating Ratings of brands and people
API
API statistics Search API of posts API Callback
Our channels
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Read
Академия TGStat Telegram Research 2019 Telegram Research 2021 Telegram Research 2023
Contacts
Справочный центр Support Email Jobs
Miscellaneous
Terms and conditions Privacy policy Public offer
Our bots
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot