በ15 ቀናት በጎጃም የተደረጉ 32 ውጊያዎች እና ድሎች
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ጎጃም ውስጥ ባለፉት አስራ አምስት ቀናት ከሰላሳ ሁለት በላይ ውጊያዎች ተደርገዋል። ከፍተኛ ወታደራዊ ድልም ተመዝግቧል፣ ፋኖ ከአገዛዙ የሚያገኘው ወታደራዊ ትጥቅም በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው።ከትናንት በስቲያ ብቻ ደብረማርቆስ ላይ በአገዛዙ ላይ የደረሰው ጉዳት ቀላል አይደለም። የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ በዚያ ውጊያ የተመታው የጠላት ሐይልም ቁጥሩ ወደ 403 ማሸቀቡን ገልጿል።
ፋኖ ዮሐንስ አክሎም 15 ቀን በተደረጉ 32 ውጊያዎች ከ2197 በላይ የጠላት ኃይል ሙት መደረጉን ተናግሯል። በዚሁ በደብረ ማርቆስ በነበረው ውጊያ ከ9 በላይ የስርዓቱ ካድሬዎች በፋኖ ታይዘው መወሰዳቸውንም ተናግሯል።
ከተያዙት ካድሬዎች መካከል አንዱ ፋኖ መንገድ በዘጋበት ጊዜ ለምን መንገድ ዘጋችው እያለ አሽከርካሪዎችን 5 አምስት ሽህ ብር ሲቀጣ እንደነበርም ተጠቁሟል። የዞኑ የመንገድና ትራንስፖርት ሀላፊ ዳንኤል አበበ በጀግኖቹ የተክለ ሀይማኖት ልጆች አብሮ መወሰዱን ጨምሯል።
በሌላ በኩል የ1ኛ ክፍለ ጦር ሻለቃ አንሙት ያዛቸው ብርጌድ አዴትና አካባቢው አድርጎት በነበረው ውጊያ ተስፋ የቆረጡ 7ሚሊሻዎች ለፋኖ እጅ መስጠታቸው ሲታወቅ፣ በሌላ በኩል 2ኛ ወይም ተፈራ ክፍለ ጦር መዝገቡ ዋለልኝ ብርጌድ ሞሳባ የሚባል ቦታ ላይ ጠላትን ሲቀጠቅጠው ውሏል። በውጊያውም በርካታ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ መደረጉ ተገልጿል።ፋኖ ዮሐንስ ውጊያውም በጨበጣ የተደረገ ስለነበር በቦንብ የጋዩ መሆናቸውን ነው የተናገረው።
በተያያዘም ይሄው የአንሙት ያዛቸው ብርጌድ ባህርዳር ከተማ በመግባት የአገዛዙን ቀንደኛ ካድሬ ይዘው መውጣታቸውን ለAbc ተናግሯል።በተመሳሳይ ትናንት ሞጣ አካባቢ በተደረገው ውጊያ 61 የአገዛዙ ጦር መደምሰሱንም ገልጿል።
በጎጃም ደጋዳሞትና ደብረማርቆስ በተካሄዱት ውጊያዎችና በተገኙ ድሎች ዙሪያ ፋኖ ዮሃንስ አለማየሁ በሰጠው ማብራሪያ የሁለተኛ ክፍለጦር የደጋ ዳሞት ብርጌድ ከፈረስ ቤት ወጥቶ እየተንቀሳቀሰ የነበረውን የአገዛዙን ጦር ድባቅ መትቷል፡፡
ይሁን እንጂ ይህ ሃይል በፋኖ በደረሰበት ምት ንጹሃንን ሲጨፈጭፍ ውሏል ብሏል የህዝብ ግንኙነቱ፡፡እንዲሁም የጃዊ ስኳር ፋብሪካን ውድ እቃዎች እየዘረፉ መሆኑን የገለጸው ቃል አቀባዩ ዝርፊያው ቀጥሏል ብሏል፡፡
ፋኖ ዮሃንስ ጀነራል አበባው ታደሰንና አዳምነህ መንግስቴን ጨምሮ በደብረማርቆስ ከተማ የነበሩ 3 የአገዛዙ ጀነራሎች ሸሽተው ወደ ባህርዳር ማቅናታቸውን ገልጿል ፡፡
እንዲሁም እነ አበባው ታደሰ ተቀምጠውበት የነበረውን መስከረም ሆቴልን ቢያስከብቡም የፋኖን ክንድ ስለፈሩ ሸሽተዋል ብሏል።
403 የአገዛዙ ጦር አባላት በፋኖ ሃይሎች እንደተገደሉ የተናገረው ፋኖ ዮሃንስ በርካቶቹ ደግሞ መቁሰላቸውን ገልጿል፡፡
Abc tv