ለእረፍት ወደ ቤተሰብ ለሄዳችሁ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ
*****************************************************
በአለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተዉን የኮሮና ቫይረስን (COVID-19) ስርጭት ለመግታት እንደ አገር የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰዱ ይገኛሉ፡፡ የበሽታዉን ስርጭት የመግታት አንደኛዉ መንገድ እንቅስቃሴዎችን መገደብ ሲሆን፣ ይህንን ለማስፈጸም እንደ አገር ለሁለት ሳምንታት ጉዞዎችን ማድረግ ለጥንቃቄ ሲባል እንደማይመከር በተደጋጋሚ ተገልጿል፡፡ በመሆኑም ለሴምስቴር እረፍት ወደ ቤተሰብ የሄዳችሁ የዩኒቨርሲቲያችን ተማሪዎች ባላችሁበት እንድትቆዩ እያሳሰብን የምትመጡበትን ጊዜ ወደፊት የምናሳዉቃችሁ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ ባላችሁበት ቦታ ሁሉ ከታማኝ ምንጮች የሚወጡትን መረጃዎች በመከታተል አስፈላጊዉን ጥንቃቄ እንድታደርጉ ለማሳሰብ እንወዳለን ፡፡
በዩኒቨርሲቲዉ የተለያዩ ካምፓሶች ያላችሁ ተማሪዎቻችንም ለጤንነታችሁ ሲባል ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በተሰጠዉ አቅጣጫ መሰረት ጥንቃቄዎችን እያደረጋችሁ በግቢዉ ዉስጥ እንድትቆዩ እናሳስባለን፡፡
ጅማ ዩኒቨርሲቲ
@JUSU1