የአቡበከር ስድብ ?
ኢስላም ጠል ሚሺነሪዎች የነቢዩ ደቀመዝሙር የሆነው አቡበከር በብልግና ቃል ተሳድቧል ብለው የሚያዘዋውሩት ሪዋያዎች አሉ። እርግጥ ነው ! የተነሳው ሐዲስ ጠለቅ ብሎ ላልመረመረውና ከላዩ ብቻ እንዲሁ በግርድፉ ላነበበው ማንኛውም ክርስቲያን ይቅርና ለሙስሊሙ እንኳ ስድብ ሊመስል የሚችል ማምታቻ ነው። ለማንኛውም ዘርዘር አድርገን እንመልከት:-
በስድስተኛው ሒጅራ ነቢዩ እና ከአንድ ሺ በላይ የሚሆኑ ሙስሊሞች ዑምራ ለማድረግ ወደ መካ እያቀኑ በጉዟቸው ላይ ሳሉ እረፍት አድርገው ለመስገድ ቁጭ ባሉበት ዑርዋ ከአንዳንድ ቁረይሾች ጋር ጥቂት ሰራዊት ይዞ መጣባቸው። ነቢዩ ለጦርነት ወደ መካ የሚያቀኑ የመሰለው ዑርዋ ነቢዩንና ሙስሊሞችን ቆሞ ይሳደብ፣ ያንቋሸሽ ነበር። "እኛ ለጦርነት አይደለም የመጣነው" የሚለውን የመልዕክተኛውን ንግግር ለመስማት ፍቃደኛ ያልሆነው መሪያቸው ነቢዩን ከመሳደብ እና ከመዝለፍ ግን መቆጠብ አልቻለም። ይህ ሳያንሰው ደግሞ ❝አንተ ሙሐመድ ሆይ ! አሁን የተከተሉህ ሰዎች እኮ ጠላት ቢመጣብህ ጥለውህ የሚሮጡ ፈሪዎች ናቸው!❞ በማለት እነዚያን ደፋር ደቀመዛሙርት ቆሞ ይሳደባል። የተወዳጁ ነቢይ እና የሙስሊሞች ስም በማንም ጣዖት አምላኪ ሲንቋሸሽ መስማት ያልቻለው:-
فقَالَ لَهُ أَبُو بَكْرٍ امْصُصْ بَظْرَ اللاَّتِ أنحن نفر عنه وندعه؟
‟..አቡበክር የላትን ብልት/ቂንጥር ላስ እኛ ነን እርሱን ትተን የምንሮጠው ?” አለው።
(📚አል-ቡኻሪ 2731: መፅሐፍ 54 ሐዲስ 19)
1- እንግዲህ የዚያ ጠንካራ ንግግር ዐውዳዊ ምክንያት ይህ ነው። ከሁሉም በፊት ልብ ሊባል የሚገባው ጉዳይ እንደው ይህ ቃል ምክንያት አልባ ደረቅ ብልግና ነው ራሱ ቢባል አንድ ስድብን መቋቋም ያልቻለው ሰው ስሜታዊ ሆኖ ተናገረው ከመባል የዘለለ ምንም ጮቤ የሚያስረግጥ ነጥብ አይደለም። አቡበከር እንደማንኛችንም የሰው ልጅ ነው፣ ይሳሳታል። የሆነ ሰው ተሳደበ ወይ ደግሞ ተሳሳተ ተብሎ እስልምና ላይ ሽንጥ ገትሮ ለሙግት መሮጥ አላዋቂነትን ነው የሚያሳየው።
2- ሲቀጥል "የእገሌን ብልት ንከስ/ሳም" ብሎ ማስነወር (አፍ ማስዘጋት) በአረቦች ዘንድ የሚታወቅ "ምሳሌያዊ አነጋገር" Proverb እንጂ እንደዛሬው "ደረቅ ስድብ" አይደለም። ስመጥሩ የቃላት-ሊቅ ኤድዋርድ ዊሊያም ሌን ይህን ንግግር በተመለከተ "A proverb of the arabs" በማለት የተለመደ ምሳሌያዊ ቃል መሆኑን ዘግቧል [Lane's Arabic-English Lexicon, Book 1, p.222]
በድረዲን አል ዐይኒ (d. 855 H) የሚከተለውን ጽፏል:-
وقال ابن التين: هي كلمة تقولها العرب عند الذم والمشاتمة، لكن تقول: بظر أمه، واستعار أبو بكر، رضي الله تعالى عنه، ذلك في اللات لتعظيمهم إياها
‟ኢብኑ ቲን እንደሚለው ይህ አይነቱ አነጋጋር ዓረቦች ሌላውን ለመውቀስ እና ለማንቋሸሽ የሚጠቀሙበት ሐረግ ነው። አቡበከርም እነርሱ ለጣዖቷ አክብሮት ስለነበራቸው ይህን ንግግር ተጠቅሞበታል።” ብሏል።
(📗አል-ዐይኒ: ኡምደቱል ቃሪዕ ጁዝዕ 14 ገፅ 10)
እንደምንመለከተው እነዚህ መሰል ንግግሮች ጥንት ዓረቦች ሌላውን የሚያንቋሽሹበት የተለመደ አይነት ምሳሌያዊ ንግግር እንጂ ዛሬ ላይ ባለው መልኩ ደረቅ የሆነ የስድብ አይነት አይደለም። አረቦች ይህን ሐረግ መጥፎ የሆነ የትኛውንም ነገር ለመግለጽ የሚጠቀሙበት መሆኑን ተጨማሪ ማስረጃ እንይ፣ ኢብኑ ረሺቅ የሚከተለውን ጽፈዋል:-
إن الشعراء ثلاثة: شاعر، وشويعر، و ماص بظر أمه
‟ገጣሚ ሦስት አይነት ነው። እጅግ ጥሩ የሚባል፣ ሌላው ተራ ገጣሚ እና (የመጨረሻው) ደግሞ የእናቱን ብልት የሚነክስ ነው።”
(ቀይረዋኒ: አል-ዑምደህ ፊል መሓሲን ቅፅ 2 ገፅ 116)
ልብ በል ! ይህ ንግግር:- ሦስተኞቹ ምድብ ገጣሚያን ምንም ዋጋ የሌለውን ሥራ ስለሚሰሩ ጥቅም አልባ ውጤታቸውን የሚገልጽ አስተያየት ነው እንጂ ተራ ስድብ አይደለም። በአጭሩ እነዚህ ገጣሚያን እጅግ መጥፎ ሥራ (ግጥም) ይጽፋሉ እያለ ነው፣ የተጠቀመው ገለጻ ግን "ብልት ይነክሳሉ" ብሎ ነው። ከዚህ የምንረዳው አረቦች ይህን መሰል ሐረግ የማይረባ ለሆነው የትኛውም ነገር እንደሚጠቀሙበት ነው። ይህ ከሆነ አቡበከር ስሜታዊ ሆኖ ይህን አረቦች ጥንት የሚጠቀሙበትን ምሳሌያዊ አነጋገር በመጠቀም የተሳዳቢውን አፍ ቢያሲዝ ምንም የሚያስገርም ነገር የለውም።
ወደ ቻናሉ
https://t.me/officialdemas
ወደ ግሩፑ
ጁሀር ኡመር
https://t.me/Dimase_11