ዲማስ


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


Similar channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


የምትዋሸው እናቴ ናፍቃኛለች 😭
=====================

አንድ የስምንት አመት ልጅ እናቱን በሞት ያጣል በዚህም የተነሳ ተጫዋች
እና ደስተኛ የነበረው ልጅ ድብርታም ፣ብቻውን የሚያዝን እና ዝምተኛ ሆነ፡፡
እናቱ ከሞተች ከአመት በኃላ አባቱ ሌላ: ሚስት አገባ ኑሮም ቀጠለ አንድ ቀን ልጁን አባቱ ጠራውና

"በእናትህ እና በእንጀራ እናትህ መሀል ልዩነት አለ?"

ብሎ ጠየቀው ፡፡ ልጁም "አዎ አለ" ብሎ መለሰ፡፡ አባቱም "ልዩነታቸው ምንድን
ነው?" ሲል መልሶ ጠየቀው፡፡ ልጁም "እናቴ ውሸታም ነች የእንጀራ እናቴ
ግን ውሸታም አይደለችም" አለ ያልጠበቀውን መልስ ያገኘው አባትም በመገረም "ምን ማለትህ ነው?" ይለዋል ልጁም እንዲህ አለ

"እናቴ እያለች ጓደኞቼ ቤት እየሄድኩ እጫወት ነበር፡፡ እናቴም በተደጋጋሚ ጓደኞቼ ቤት ሄጄ መጫወቱን እንድተው ካልተውኩ ግን ምግብ እንደማትሰጠኝ ትነግረኝ ነበረ፡ ሆኖም ግን እኔን ቤት ውስጥ ስታጣኝ የምትሰራውን ስራ አቁማ እኔን ፍለጋ ትመጣ ነበር ወደ ቤትም ወስዳ ምግብ ትሰጠኝ ነበር፡ የእንጀራ እናቴ ግን ቃልዋን ታከብራለች፡፡

ለዛም ነው ላለፉት ሁለት ቀናት ምግብ ያልበላሁት እርቦኛል ፡እናቴም ናፍቃኛለች፡፡ "እያለ ማልቀስ ጀመረ አንጀት የሚበላ የሰቀቀን ለቅሶ ፡፡ እ...ና...ቴ..ን እያለ😢

የወለደች እናት መቼም ቢሆን አትጨክንብህም


እስቲ ከሰው እስከ እንሳሳት ድረስ እናት አዛኝ ናት


ለዚህም ነው ነብያችንﷺ ከሰዎች ሁሉ ወዳጅ አድርጌ የምይዘውና ልንከባከው የሚገባኝ ማነው ብሎ 4 ጊዜ ሲጠይቅ እናትህ እናትህ እናትህ ነው ያሉት።

የሜዳ አህያ እና ጎሽ ለልጆቻቸው ሲሉ በአንበሳ ይበላሉ።።

ለእናቶቻችን አሏህ በእዝነቱ ይዘንላቸው በእርዳታው ይድረስላቸው

ዲማስ group

https://t.me/Dimase_11

ቻናሉን

https://t.me/officialdemas




የአቡበከር ስድብ ?

ኢስላም ጠል ሚሺነሪዎች የነቢዩ ደቀመዝሙር የሆነው አቡበከር በብልግና ቃል ተሳድቧል ብለው የሚያዘዋውሩት ሪዋያዎች አሉ። እርግጥ ነው ! የተነሳው ሐዲስ ጠለቅ ብሎ ላልመረመረውና ከላዩ ብቻ እንዲሁ በግርድፉ ላነበበው ማንኛውም ክርስቲያን ይቅርና ለሙስሊሙ እንኳ ስድብ ሊመስል የሚችል ማምታቻ ነው። ለማንኛውም ዘርዘር አድርገን እንመልከት:-

በስድስተኛው ሒጅራ ነቢዩ እና ከአንድ ሺ በላይ የሚሆኑ ሙስሊሞች ዑምራ ለማድረግ ወደ መካ እያቀኑ በጉዟቸው ላይ ሳሉ እረፍት አድርገው ለመስገድ ቁጭ ባሉበት ዑርዋ ከአንዳንድ ቁረይሾች ጋር ጥቂት ሰራዊት ይዞ መጣባቸው። ነቢዩ ለጦርነት ወደ መካ የሚያቀኑ የመሰለው ዑርዋ ነቢዩንና ሙስሊሞችን ቆሞ ይሳደብ፣ ያንቋሸሽ ነበር። "እኛ ለጦርነት አይደለም የመጣነው" የሚለውን የመልዕክተኛውን ንግግር ለመስማት ፍቃደኛ ያልሆነው መሪያቸው ነቢዩን ከመሳደብ እና ከመዝለፍ ግን መቆጠብ አልቻለም። ይህ ሳያንሰው ደግሞ ❝አንተ ሙሐመድ ሆይ ! አሁን የተከተሉህ ሰዎች እኮ ጠላት ቢመጣብህ ጥለውህ የሚሮጡ ፈሪዎች ናቸው!❞ በማለት እነዚያን ደፋር ደቀመዛሙርት ቆሞ ይሳደባል። የተወዳጁ ነቢይ እና የሙስሊሞች ስም በማንም ጣዖት አምላኪ ሲንቋሸሽ መስማት ያልቻለው:-
فقَالَ لَهُ أَبُو بَكْرٍ امْصُصْ بَظْرَ اللاَّتِ أنحن نفر عنه وندعه؟
‟..አቡበክር የላትን ብልት/ቂንጥር ላስ እኛ ነን እርሱን ትተን የምንሮጠው ?” አለው።
(📚አል-ቡኻሪ 2731: መፅሐፍ 54 ሐዲስ 19)

1- እንግዲህ የዚያ ጠንካራ ንግግር ዐውዳዊ ምክንያት ይህ ነው። ከሁሉም በፊት ልብ ሊባል የሚገባው ጉዳይ እንደው ይህ ቃል ምክንያት አልባ ደረቅ ብልግና ነው ራሱ ቢባል አንድ ስድብን መቋቋም ያልቻለው ሰው ስሜታዊ ሆኖ ተናገረው ከመባል የዘለለ ምንም ጮቤ የሚያስረግጥ ነጥብ አይደለም። አቡበከር እንደማንኛችንም የሰው ልጅ ነው፣ ይሳሳታል። የሆነ ሰው ተሳደበ ወይ ደግሞ ተሳሳተ ተብሎ እስልምና ላይ ሽንጥ ገትሮ ለሙግት መሮጥ አላዋቂነትን ነው የሚያሳየው።

2- ሲቀጥል "የእገሌን ብልት ንከስ/ሳም" ብሎ ማስነወር (አፍ ማስዘጋት) በአረቦች ዘንድ የሚታወቅ "ምሳሌያዊ አነጋገር" Proverb እንጂ እንደዛሬው "ደረቅ ስድብ" አይደለም። ስመጥሩ የቃላት-ሊቅ ኤድዋርድ ዊሊያም ሌን ይህን ንግግር በተመለከተ "A proverb of the arabs" በማለት የተለመደ ምሳሌያዊ ቃል መሆኑን ዘግቧል [Lane's Arabic-English Lexicon, Book 1, p.222]

በድረዲን አል ዐይኒ (d. 855 H) የሚከተለውን ጽፏል:-
وقال ابن التين: هي كلمة تقولها العرب عند الذم والمشاتمة، لكن تقول: بظر أمه، واستعار أبو بكر، رضي الله تعالى عنه، ذلك في اللات لتعظيمهم إياها
‟ኢብኑ ቲን እንደሚለው ይህ አይነቱ አነጋጋር ዓረቦች ሌላውን ለመውቀስ እና ለማንቋሸሽ የሚጠቀሙበት ሐረግ ነው። አቡበከርም እነርሱ ለጣዖቷ አክብሮት ስለነበራቸው ይህን ንግግር ተጠቅሞበታል።” ብሏል።
(📗አል-ዐይኒ: ኡምደቱል ቃሪዕ ጁዝዕ 14 ገፅ 10)

እንደምንመለከተው እነዚህ መሰል ንግግሮች ጥንት ዓረቦች ሌላውን የሚያንቋሽሹበት የተለመደ አይነት ምሳሌያዊ ንግግር እንጂ ዛሬ ላይ ባለው መልኩ ደረቅ የሆነ የስድብ አይነት አይደለም። አረቦች ይህን ሐረግ መጥፎ የሆነ የትኛውንም ነገር ለመግለጽ የሚጠቀሙበት መሆኑን ተጨማሪ ማስረጃ እንይ፣ ኢብኑ ረሺቅ የሚከተለውን ጽፈዋል:-
إن الشعراء ثلاثة: شاعر، وشويعر، و ماص بظر أمه
‟ገጣሚ ሦስት አይነት ነው። እጅግ ጥሩ የሚባል፣ ሌላው ተራ ገጣሚ እና (የመጨረሻው) ደግሞ የእናቱን ብልት የሚነክስ ነው።”
(ቀይረዋኒ: አል-ዑምደህ ፊል መሓሲን ቅፅ 2 ገፅ 116)

ልብ በል ! ይህ ንግግር:- ሦስተኞቹ ምድብ ገጣሚያን ምንም ዋጋ የሌለውን ሥራ ስለሚሰሩ ጥቅም አልባ ውጤታቸውን የሚገልጽ አስተያየት ነው እንጂ ተራ ስድብ አይደለም። በአጭሩ እነዚህ ገጣሚያን እጅግ መጥፎ ሥራ (ግጥም) ይጽፋሉ እያለ ነው፣ የተጠቀመው ገለጻ ግን "ብልት ይነክሳሉ" ብሎ ነው። ከዚህ የምንረዳው አረቦች ይህን መሰል ሐረግ የማይረባ ለሆነው የትኛውም ነገር እንደሚጠቀሙበት ነው። ይህ ከሆነ አቡበከር ስሜታዊ ሆኖ ይህን አረቦች ጥንት የሚጠቀሙበትን ምሳሌያዊ አነጋገር በመጠቀም የተሳዳቢውን አፍ ቢያሲዝ ምንም የሚያስገርም ነገር የለውም።
ወደ ቻናሉ
https://t.me/officialdemas

ወደ ግሩፑ
ጁሀር ኡመር

https://t.me/Dimase_11




ሰይጣናዊ ማስፈራርያ!!!!!

እባካችሁ ተዉ❗️⚠️
▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭
💬:#ሸይጣን የሚሸነፈው ፅሁፎችን ሼር በማድረግ ነው ያለው ማነው? ይህ መልዕክትና የዚህ አይነት መሰል መልዕክቶች(text) በብዙ ግሩፖች ላይ ይሰራጫሉ።

✅:ሸይጧን የሚሸነፈው በቁርኣንና በሀዲስ ስንመራና ስንሰራበት፣ ከሽርክ፣ ከኒፋቅ፣ ከፊስቅ፣ ከቢድዓ፣ ከጃህልና ከአጠቃላይ ወንጀሎች ስንጠነቀቅና ስንርቅ ብቻ ከሆነ ነው እንጂ ማንም #የደቀደቀውን ልብወለድ ፅሁፍ ሼር ስናረግ አይደለም ሆኖም ኣያውቅም❗️

📝:እንደዚህ አይነት ፅሁፎችን የምትፅፉም ሆናችሁ ተቀብላችሁም ሼር የምታረጉ ሁሉን አላህን ልትፈሩት ይገባል። ምክንያቱም ማንኛውም መልዕክት ከየትም ይምጣ ከየት ከአላህ ቁርኣን ኣያቶች፣ ከነብያችን ሀዲሶች፣ ከሰሃባዎችና ከዑለማዎች ንግግሮች የተገኘና የተወሰደ መሆን አለበትና ነው።

🔎:አብዛኛውን ጊዜ ያለምንም አድራሻ እንዲህ አይነት ፅሁፎችን መፃፍ የሚቀናቸው ሰዎች የዐቂዳና የሱና #ችግር ያለባቸው ሰዎች ናቸውና ዝም ብላችሁ ፅሁፋቸውን አትቀበሉ

ይህንን በመላክ የነብዪን ሸፈዓ ታገኛላችሁ

ይህንን መልእክት ችላ ካልክ ብዙ መጥፎ አጋጣሚዎችን ይገጥምሃል።

ለብዙ ሰው ሼር ካደረግክ ብዙ ጥሩ እድሎችን ታገኛለህ ምናምንና የመሳሰሉት
እኔምለው ትልቁ ሽርክም ቢኖርበት የነብዩን ሸፈዓ ያገኛልን?

ነብዩﷺ ሸፋዓዬ በአሏህ ላይ ለማያጋሩት ነው ብለዋል ።

እና ለዚህ በህልም ታየ ተብሎ ለሚሰራጭ ወረቀት የነብዩን ንግግር ይሻራል ማለት ነው?

ምን አይነት እቃ እቃ ጨዋታ ነው የተያያዝ ነው?

ደሞ ቁርጡን ልንገራችሁ እኔ የዛሬ ሁለት አመት ተው ይሄ ነገር ከሀዲስ ይጋጫል ብያለሁ አልኸምዱሊሏህ ምንም አልሆንኩ።
✍ ጁሀር ኡመር
ቻናል
https://t.me/OfficialDemas

ግሩፕ
https://t.me/Dimase_11


አንድ ወጣት ሲመጣ ካገኘሁ ግደለውና....................



🌴🌴🌴መልካም ብትሰሩ ለራሳችሁ ነው መጥፎም ብትሰሩ በራሳችሁ ላይ ነው።

إِنْ أَحْسَنتُمْ أَحْسَنتُمْ لِأَنفُسِكُمْ ۖ وَإِنْ أَسَأْتُمْ فَلها

መልካም ብትሠሩ ለነፍሶቻችሁ መልካምን ሠራችሁ፡፡


መጥፎንም ብትሠሩ በነርሱ (በነፍሶቻችሁ) ላይ ነው፤ (አልን)፡፡

ሰዎች መጥፎ ነገር ሲሰሩም አሏህ ዝም ብሎ ያቆያቸዋል።

🌿አንዳንዶቹን ደሞ በዚያው ቅፅፈት የሰሩት በራሳቸው ላይ ይሆናል።
አሏህ በአመፃችን ማቆየቱም ይሁን በፍጥነት መመለሱ ከረቀቀ ጥበቡ እንጂ አቅቶት ረስቶት ችላም ብሎት አይደለም ።

ብዙ ሰዎች በብዙ ግፈኞች እየተበደሉ በየ ቀኑ ያለቅሳሉ።

እውነትም ተበድለው ሊሆን ይችላል ። ግን አሏህ ሆይ አንተም ከጥጋበኞች ጎን ሆንክብኝ ብለው ምርር ብለው ንዴታቸው ሲገልፁ ይስተዋላሉ።


ግን አንድ ጥያቄ ላንሳ፦፦፦

ሁሉም በሰራ ግፍ ቢቀጣውና ቢያጠፋው በዚህ ምድር መንቀሳቀሱ አይናፈቅም ነበርን?

ይህንን ፅሑፍ የምታነብ ሁላ አንተ ጭራሽ በሰው ላይ ግፍ ሰርተህ አታውቅምን?

አልሰራሁም የምትል ከሆነ ማሻ አሏህ ግን ሰርቻለሁ የምትል ከሆነ አሏህ በግፍህ ልክ ቢቀጣህ የዛሬውን ቀን ባላየሃት ነበር።

አየህ አይደል አሏህ ከጥበቡ ነው ጊዜ የሚሰጠን ።

ወይ ከወንጀላችን ከግፋችን ልንመለስ አልያም ሰብስቦልን በመጨረሻ የሰዎች ማስተማሪ ሊያደር ገን ነው።

የተበዳይ እምባና ዱዓ በከንቱ አይቀርም።

አንዳንዴም አንዳንድ ሰዎች እራሳቸው የተካኑ ግፈኛ ሆነው በግፋቸውም ሰውን እንዲሳተፋ ይገፋፋሉ።

👉ያም ይሁን ይህ በየትኛውም ሁኔታ እራሳችን የሰራነው ግፍያ ያለጥርጥር በራሳችን ላይ ይሆናል ።

እስቲ አንድ ከሰማሁት ላጫውታችሁ።

ከእለታት አንድ ቀን አንዱ ከሚስቱ ጋር በሆነው ባልሆነው ይነታረኩና በሆነ ነገር አንስቶ ጭንቅላቷ ይላታል። እናም ሚስቱ ከዚህ አለም ትለያለች።

በዚህ ጊዜ ጭንቀት ውስጥ ይገባና ጓደኛውን በሚስጥር መልኩ ምን ማድረግ አለብኝ? ሲል ይጠይቀዋል።
ሁለቱ ሰዎች እራሳቸው ይተዋወቁ እንጂ ቤተሰቦቻቸው አያውቁም አንዱን የአንዱ ማለት ነው።
እናም ምክር ተጠያቂው ጓደኛ እንዲህ ሲል ምክሩን ለገሰው።
ነገ ጥዋት በዚህ በኩል የሚያልፍ ወጣት ወንድ ካገኘህ አስተባብለህ ቤት አስገባውና

ገድለኸው ከሚስትህ ጋር አስተኛው ። ከዚያም ውጭ ወጣና ጩህ ሚስቴ ከሌላ ወንድ ጋር ተኝታ አግኛት በንዴት ገደልኳት በል ይለዋል።
ምክር ጠያቂው ጥዋት አንድ ዘለግላጋ ወጣት ያገኝና እንደ ተባለው ያደርግና ውጭ ወጥቶ ጩኸቱን ያቀልጠዋል።

ሰውም ተሰበሰበ መካሪም ተመካሪም ከህዝቡ ጋር ወደ ቤት ይገባሉ ወደ ጀናዛው ሲጠጉ የተከሰተው ነገር ግፍ ይገለበጣል እንደሚባለው የተገደለው የመካሪው ልጅ ነው።

ስለዚ በመጥፎ ሰዎችን ስንመክ መጀመሪያ ማሰብ ያለብን ለራሳችን ነው።

ጨው ለራስህ ብለህ ጣፍጥ አልያ.......
ግሩፕ
https://t.me/Dimase_11



ቻናል
✍️ጁሀር ኡመር
https://t.me/officialdemas


ያገባችሁ ከሚስቶቻችሁ ጋር ተዝናኑበት

ኮሟች (አስተያየት ሰጪ ሴቶች )ማለት እኔ ብሆን እንዲህ አደርግ ነበር የሚሉት ናቸው።

እንቀጥል ።።።።።።።።።

ባልሽ በጠና ታሞ ዶክተር መድሀኒቱ ሁለተኛ ሚስት ማግባት ነው ካለሽ ትስማማያለሽ እንዲያገባ ወይስ እንዲሞት ትተይዋለሽ?

ያዝናናኝ ኮመንት በጥቂቱ
አንደኛ ኮሟች እያንዳንዷ ነፍስ ሞትን ቀማሽ ናት

2ኛ ኮሟቿ
ሞት እውነት ነው ሁላችንም ወደዛ ተጏዦች ነን

3ኛ አላህ ይርሀሙ በእውነቱ ምርጥ ባል ነበር

4ኛ መድሀኒቱ ሁለተኛ ሚስት ከሆነች እድርዋለው ይዳን ከሚሞት ሌላም አግብቶ ታሞ 3ተኛ እንዳይጠይቅ እንጅ

5ኛ አላህ ሰጠኝ አላህ ነሳኝ ብዬ ሰብር አደርጋለው ሁለተኛም አግብቶ ሞት አይቀርለት ስለዚህ እኔም ሁለተኛዋም ሴት የሙት ሚስት ከምንሆን ብቻዬን ሀዘኑን ብሸከም ይሻላል

6ኛዋ ማንም ያለቀኑ አይሞትምና አላህ የጀነት እንዲያደርገው እድሜዬን በሙሉ ዱአ አደርግለታለው

ሌላዋ ኮማች ደሞ ሁለተኛ ሚስት ኦክስጅን ናት እንዴ ? ለምን እኔ መሆን አልችልም? የላ እንግዲያውስ አላህ ይዘንለት

እናንተስ ምን ትላላቹ ሴቶች?




ሴት
ግን እስከ አራት ትፈቅድለታለች

وَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تُقْسِطُوا فِي الْيَتَامَىٰ فَانكِحُوا مَا طَابَ لَكُم مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۖ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَلَّا تَعُولُوا

በየቲሞችም (ማግባት) አለማስተካከላችሁን ብትፈሩ (ዝሙትንና ከተወሰነላችሁ በላይ ማግባትንም ፍሩ)፡፡ ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት ሦስት ሦስትም አራት አራትም አግቡ፡፡ አለማስተካከልንም ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ወይም እጆቻችሁ ንብረት ያደረጉትን ያዙ፡፡ ይህ ወደ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው፡፡
👉
ዝም ብሎ ሳይችልና በቃ ተፈቅዳል ተፈቅዳል ብሎ ዘሎ የሚያገባ ሰው ቁርኣኑን በደንብ ይረዳው (ፈኢን ኺፍቱም አላ ተዕዲሉ ፈዋሂደህ) ችሎታውን ማወቅ አለበት

ይህን ካረጋገጠ በቀረው በአሏህ ላይ መመካት ነው
ያንተስ ሚስት ምን አለችህ?

ምንም ትበል ግን ቤት ውስጥ ጭቅጭቅ እንዳታነሳ አደራ።።።።።

ቻናሉን

https://t.me/OfficialDemas


ግሩፑ
https://t.me/Dimase_11

✍️✍️✍️ጁሀር ኡመር




Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ባህሩ እየተቃጠለ ከግጥም ጋር

በሜክሲኮ (MEXICO) በባህር ውስጥ ባለ


ነዳጅ ምክንያት የተነሳ እሳት ባህሩ ሲቃጠል 2015 EC

ሱረቱል አተክዊር 6
وَإِذَا الْبِحَارُ سُجِّرَتْ

ባሕሮችም በተቃጠሉ ጊዜ፤
ቤቴ ቤታችሁ ነው እንኳን

ደህና መጣችሁ

ቁልፉን ይሄ ነው ከፍታችሁ ግቡ

ቤቴ የገባ ሰው ተከፍቶ አይወጣም

ሊንኩን አንዴ ብቻ ጫን በሉት👇👇👇👇

ግሩኝ
https://t.me/Dimase_11
✍ጁሀር ኡመር

ቻናሉ

https://t.me/https://t.me/OfficialDemas
✍️ጁሀር ኡመር


Forward from: እውነት
ፈገግ በሉ

https://t.me/+In1odJ3z9DNlMTRk


Forward from: እውነት
በቀጥታ ስርጭት


በሳምንት ሶስት ቀናት ከመግሪብ እስከ ዒሻ


አርብ


ቅዳሜ


እሁድ

በሚያመር አንደበት ባለው ኡስታዛችን

አቡ አብድል መናን ኻሊድ ቢን ጦይብ አሏህ ይጠብቀው።

ገባ ገባ በሉ ምን አልባት የጀነት መግቢያ ሰበብ ሊሆናችሁ ይችላል


ሊንኩን አንዴ ብቻ ጠቅ በማድረግ

https://telegram.me/Al_Furqan_Islamic_Studio?voicechat


Forward from: አል ፉርቃን ኢስላማዊ ስቱዲዮ
↪️ ተተተ                              ተተተ ↩️

     ↪️ ጀጀጀ                    ጀጀጀ ↩️

          ↪️ መመ           መመ ↩️
 
               ↪️ ረረረ    ረረረ ↩️


              ↪️ ተተተ    ተተተ ↩️

          ↪️ ጀጀጀ             ጀጀጀ ↩️

     ↪️ መመ                       መመ ↩️

↪️ ረረረ                                    ረረረ ↩️
          📖📖 የቁርዓን ተፍሲር 📖📖

    © «ተ»   «ጀ»   «መ»   «ረ» ©

«««© የደርስ ፕሮግራም ©»»»


🕰️ የዛሬ ከመግሪብ እስከ ዒሻ የቀጥታ ስርጭት ደርስ ተጀመረ።

📖የ68ኛው የሱረቱ ቀለም ተፍሲር 📖
                   ቁጥር 0
2

🎙️ በኡስታዝ አቡ አብድልመና ኻሊድ ቢን ጠይብ አላህ ይጠብቀው።

🔄 Play ▶️ ────◉ 12:55 PM

👇👇 ደርሱን ለመከታተል 👇👇
📎
https://telegram.me/Al_Furqan_Islamic_Studio?voicechat

📚 የኪታቡን pdf ለማግኘት 📚
🔗
t.me/Al_Furqan_pdf/694

💬 ሀሳብ ለምስጠት ⤵️⤵️⤵️
@Al_Furqan_Islamic_Studio_bot


እውነተኛ ፍቅር ማለት፦

☞ ነብዩ ﷺ ለባልደረባቸው ሰውባን ረዲየሏሁ ዐንህ ምንድነው ፊትህን የቀየረው? ብለው ሲጠይቁት «በሽታም ሆነ ህመምም የለብኝም፤ ግን አንቱን ሳላገኝ ስቀር ከባድ የሆነ ብቸኝነት ይሰማኛል፤ አንቱን እስከማገኞዎ ድረስ» ማለቱ ነው።

✅:እውነተኛ ፍቅር ማለት፦

☞ አቡበከር አስ-ሲዲቅ ረደዲየሏሁ አንህ ከነብዩ ጋር በሂጅራ ጉዟቸው ወደ ዋሻ ከመግባታቸው በፊት
«ወሏሂ ካንቱ በፊት ካልገባው በስተቀር አትገቡም፣ የሆነ ነገር ቢኖር እንኳ ካንተ በፊት እኔን ይጉዳኝ» ማለታቸው ነው።

✅:እውነተኛ ፍቅር ማለት፦

☞ ዐሊይ ኢብን አቢ-ጧሊብ ﷺ ረዲየሏሁ አንህ በነብዩ ፋንታ በፍራሻቸው መተኛታቸው ነው፤ የመካ ካፊሮች ነብዩን ﷺ ለመግደል መስማማታቸውና በዛ ፍራሽ ላይ ሊሞቱ እንደሚችል እያወቁ መተኛታቸው ነው።

✅:እውነተኛ ፍቅር ማለት፦

☞ ቢላል አል-ሐበሺይ ረዲየሏሁ አንህ ነብዩ ﷺ ሲሞቱ የነብዩ ﷺ ፍቅር መዲና አላስቀምጥ ብሎት አዛን ማድረጉን መተዉና መዲናን ጥሎ መሄዱ ነው፤ ይህ ብቻም ሳይሆን ነብዩ ﷺ በህልሙ መጥተውበት ምንድነው እንዲህ መጥፋት? ለምን አትዘይረንም? ሲሉት ገና ሌሊቱ እንደነጋ የነብዩን ﷺ ቀብር ዚያራ ለማድረግ መጓዙ ነው፤ ከዛም አዛን እንዲያደርግ ለምነውት ያን ጣፋጩን አዛን ሲያደርግ የመዲና ህዝብ
በሙሉ በእንባ መራጨቱ ነው። ነብዩ ﷺ ከሞቱ በኃላ እንጂ እንደዛ አይነት እልቅሻ አልታየም ተብሎ በታሪክ ኢስኪፃፍ ድረስ።

✅:እውነተኛ ፍቅር ማለት፦

☞ ከበኒ ዲናር የሆነች ሴት ባሏ፣ አባቷና ወንድሟ ወደ «ኡሑድ» ዘመቻ ወጥተው ሳለ ሙስሊሞች ከውግያው ሲመለሱ ሁሉም እንደሞቱ ሲነገራት «ነብዩ ﷺ እንዴት ሆኑ? ብላ መጠየቋ ነው፤ ከዛም እሳቸው አልሞቱም ሲሏት እሳቸውን ካላየው ብላ ነብዩን ﷺ ስታያቸው «ካንቱ በኃላ ያለ ሙሲባ ሁሉ ለኔ ገር ነው» ማለቷ ነው።

✅:እውነተኛ ፍቅር ማለት፦

☞ ዙበይር ﷺ የ15 አመት ወጣት ሆኖ የነብዩን ﷺ መገደል የውሸት ወሬ ሲሰማ የመካ መንገዶች ላይ ሰይፉን እየጎተተ መውጣቱ ነው።

✅:እውነተኛ ፍቅር ማለት፦

☞ ረቢዐተ ኢብን ከዕብን ረዲየሏሁ አንህ ነብዩ ﷺ ምንድነው ሓጃህ (ጉዳይህ) ሲሉት ካንቱ ጋር
በጀነት ጓደኛ መሆን ነው ማለቱ ነው።

♻️ነብዩን ﷺ የምንወድ ፣ እነሱን መውደዳችንም በተግባር የምናሳይ ፣ የነሱን ሱና አምነውበት ከሚተገብሩት አላህ ያድርገን ~~~https://t.me/Dimase_11

✍ጁሀር ኡመር
┊  ┊  ┊  ┊


ወንድማችን ሰልሟል ቃለ ምልልሱን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑት ይማሩበትhttps://t.me/Dimase_11

✍ጁሀር ኡመር


Forward from: እውነት
ወንደማችን ደምስ ሰልሟል ስሙም ሙሐመድ እንዲባል ፈልጓል ብለነዋልም ማሻ አሏህ ዱዓ አድርጉለት ሁላችሁ የሰለመበትን የተመላለስንበት ወደ ላይ ማንበብ ትችላላችሁ ኧልኸምዱሊሏህ
ከአሁን በኋላ ቴሌ ግራሙ መደበኛ ስርጭቱ ይቀጥላል ኢንሻ አሏህ

https://t.me/Dimase_11

✍ጁሀር ኡመር


Forward from: እውነት
ክርስቲያኑን ደምስ በኔቱ ምክንያት አድሚን ማድረግ ስላልቻልኩ አውፍ በሉኝና ኔቱ ሲስተካከል እኔና እሱ ብቻ እዚሁ ቦታ እንገናኛለን ኢንሻአላህ ።
http://t.me/Dimase_11


Forward from: እውነት
ዲማስ ማለት ምን ማለት ነው ለምትሉ በሉእ ሉእ መርጃን ኪታቡል ኢማን ገፅ 46-47 ሀዲስ ቁጥር 106 ላይ كأنّما خرج من ديماس ብለው የተናገሩት ስለ ነብዩሏህ ዒሳ ዓለይሂ ሰላም ሲናገሩ የፊቱና የገፅታው ማማር ሲገልፁ ከዲማስ የወጣ ይመስላል ብለው ገልፀውታል ትርጉሙም ሁሉም ያጠለለህ ነገር ከሙቀትና ቅዝቃዜ የሚከላከል ቦታ ነው ። http://t.me/Dimase_11


Forward from: እውነት


Forward from: እውነት
የአሏህ ፈቃድ ከሆነ ውይይቱ ዛሬ ከአስር ሰኣት ጀምሮ ከላይ በገለፅኩት መሰረት መከታተል ይችላሉ።

https://t.me/Dimase_11

✍ጁሀር ኡመር


Forward from: እውነት
ማሳሰብያ
ኧሰላም ዓለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱህ

በዚህ ቴሌግራም ያላችሁ የተከበራችሁ የሰው ልጆች በሙሉ ፦
አንድ የዚህ ፕሮግራም ተከታታይ የሆነ ክርስትያን ወገን ከላይ በለቀቅኩት ወይም ሙሀመድ የሚለው ስም በመፅሐፋቸው የሰራሁት ቪድዮ የቪድዮው ርዕስ ሚስጥሩ ተጋለጠ የሚለውን መልሶ መላልሶ በማየት ውስጡ ጥያቄ ስለፈጠረበት ለአንድ ቀን የሆነ ሰአት ......ለውይይት ክፍት ብታደርገው ከዚያም የምወስነውን እወስናለሁ ስላለኝ ።
የአሏህ ፈቃድ ከሆነ

እኔም ይህን የአስተያየት ጥያቄው በመቀበል ፦ ነገ አርብ ወይም እሁድ።

ማንም ሰው ጥያቄና አስተያየት መፃፍ እንዲችል ይህንን ቴሌግራም ለተከታታዮቹ ክፍት ይደረጋል ።

ሰኣቱ እንነግራችኋለን።

ከዚያ በኋላ መደበኛ የፕሮግራም ስርጭቱ ዘግቶ ይጀምራል ። ኢንሻ አላህ ይህንን ሊንክ ተጭናችሁ ወደ መድረክ ገብታችሁ እንድትጠብቁን እጋብዛችኋለሁ https://t.me/Dimase_11

✍ጁሀር ኡመር

20 last posts shown.

212

subscribers
Channel statistics