እውነተኛ ፍቅር ማለት፦
☞ ነብዩ ﷺ ለባልደረባቸው ሰውባን ረዲየሏሁ ዐንህ ምንድነው ፊትህን የቀየረው? ብለው ሲጠይቁት «በሽታም ሆነ ህመምም የለብኝም፤ ግን አንቱን ሳላገኝ ስቀር ከባድ የሆነ ብቸኝነት ይሰማኛል፤ አንቱን እስከማገኞዎ ድረስ» ማለቱ ነው።
✅:እውነተኛ ፍቅር ማለት፦
☞ አቡበከር አስ-ሲዲቅ ረደዲየሏሁ አንህ ከነብዩ ጋር በሂጅራ ጉዟቸው ወደ ዋሻ ከመግባታቸው በፊት
«ወሏሂ ካንቱ በፊት ካልገባው በስተቀር አትገቡም፣ የሆነ ነገር ቢኖር እንኳ ካንተ በፊት እኔን ይጉዳኝ» ማለታቸው ነው።
✅:እውነተኛ ፍቅር ማለት፦
☞ ዐሊይ ኢብን አቢ-ጧሊብ ﷺ ረዲየሏሁ አንህ በነብዩ ፋንታ በፍራሻቸው መተኛታቸው ነው፤ የመካ ካፊሮች ነብዩን ﷺ ለመግደል መስማማታቸውና በዛ ፍራሽ ላይ ሊሞቱ እንደሚችል እያወቁ መተኛታቸው ነው።
✅:እውነተኛ ፍቅር ማለት፦
☞ ቢላል አል-ሐበሺይ ረዲየሏሁ አንህ ነብዩ ﷺ ሲሞቱ የነብዩ ﷺ ፍቅር መዲና አላስቀምጥ ብሎት አዛን ማድረጉን መተዉና መዲናን ጥሎ መሄዱ ነው፤ ይህ ብቻም ሳይሆን ነብዩ ﷺ በህልሙ መጥተውበት ምንድነው እንዲህ መጥፋት? ለምን አትዘይረንም? ሲሉት ገና ሌሊቱ እንደነጋ የነብዩን ﷺ ቀብር ዚያራ ለማድረግ መጓዙ ነው፤ ከዛም አዛን እንዲያደርግ ለምነውት ያን ጣፋጩን አዛን ሲያደርግ የመዲና ህዝብ
በሙሉ በእንባ መራጨቱ ነው። ነብዩ ﷺ ከሞቱ በኃላ እንጂ እንደዛ አይነት እልቅሻ አልታየም ተብሎ በታሪክ ኢስኪፃፍ ድረስ።
✅:እውነተኛ ፍቅር ማለት፦
☞ ከበኒ ዲናር የሆነች ሴት ባሏ፣ አባቷና ወንድሟ ወደ «ኡሑድ» ዘመቻ ወጥተው ሳለ ሙስሊሞች ከውግያው ሲመለሱ ሁሉም እንደሞቱ ሲነገራት «ነብዩ ﷺ እንዴት ሆኑ? ብላ መጠየቋ ነው፤ ከዛም እሳቸው አልሞቱም ሲሏት እሳቸውን ካላየው ብላ ነብዩን ﷺ ስታያቸው «ካንቱ በኃላ ያለ ሙሲባ ሁሉ ለኔ ገር ነው» ማለቷ ነው።
✅:እውነተኛ ፍቅር ማለት፦
☞ ዙበይር ﷺ የ15 አመት ወጣት ሆኖ የነብዩን ﷺ መገደል የውሸት ወሬ ሲሰማ የመካ መንገዶች ላይ ሰይፉን እየጎተተ መውጣቱ ነው።
✅:እውነተኛ ፍቅር ማለት፦
☞ ረቢዐተ ኢብን ከዕብን ረዲየሏሁ አንህ ነብዩ ﷺ ምንድነው ሓጃህ (ጉዳይህ) ሲሉት ካንቱ ጋር
በጀነት ጓደኛ መሆን ነው ማለቱ ነው።
♻️ነብዩን ﷺ የምንወድ ፣ እነሱን መውደዳችንም በተግባር የምናሳይ ፣ የነሱን ሱና አምነውበት ከሚተገብሩት አላህ ያድርገን ~~~https://t.me/Dimase_11
✍ጁሀር ኡመር
┊ ┊ ┊ ┊