አንድ ወጣት ሲመጣ ካገኘሁ ግደለውና....................
🌴🌴🌴መልካም ብትሰሩ ለራሳችሁ ነው መጥፎም ብትሰሩ በራሳችሁ ላይ ነው።
إِنْ أَحْسَنتُمْ أَحْسَنتُمْ لِأَنفُسِكُمْ ۖ وَإِنْ أَسَأْتُمْ فَلها
መልካም ብትሠሩ ለነፍሶቻችሁ መልካምን ሠራችሁ፡፡
መጥፎንም ብትሠሩ በነርሱ (በነፍሶቻችሁ) ላይ ነው፤ (አልን)፡፡
ሰዎች መጥፎ ነገር ሲሰሩም አሏህ ዝም ብሎ ያቆያቸዋል።
🌿አንዳንዶቹን ደሞ በዚያው ቅፅፈት የሰሩት በራሳቸው ላይ ይሆናል።
አሏህ በአመፃችን ማቆየቱም ይሁን በፍጥነት መመለሱ ከረቀቀ ጥበቡ እንጂ አቅቶት ረስቶት ችላም ብሎት አይደለም ።
ብዙ ሰዎች በብዙ ግፈኞች እየተበደሉ በየ ቀኑ ያለቅሳሉ።
እውነትም ተበድለው ሊሆን ይችላል ። ግን አሏህ ሆይ አንተም ከጥጋበኞች ጎን ሆንክብኝ ብለው ምርር ብለው ንዴታቸው ሲገልፁ ይስተዋላሉ።
ግን አንድ ጥያቄ ላንሳ፦፦፦
ሁሉም በሰራ ግፍ ቢቀጣውና ቢያጠፋው በዚህ ምድር መንቀሳቀሱ አይናፈቅም ነበርን?
ይህንን ፅሑፍ የምታነብ ሁላ አንተ ጭራሽ በሰው ላይ ግፍ ሰርተህ አታውቅምን?
አልሰራሁም የምትል ከሆነ ማሻ አሏህ ግን ሰርቻለሁ የምትል ከሆነ አሏህ በግፍህ ልክ ቢቀጣህ የዛሬውን ቀን ባላየሃት ነበር።
አየህ አይደል አሏህ ከጥበቡ ነው ጊዜ የሚሰጠን ።
ወይ ከወንጀላችን ከግፋችን ልንመለስ አልያም ሰብስቦልን በመጨረሻ የሰዎች ማስተማሪ ሊያደር ገን ነው።
የተበዳይ እምባና ዱዓ በከንቱ አይቀርም።
አንዳንዴም አንዳንድ ሰዎች እራሳቸው የተካኑ ግፈኛ ሆነው በግፋቸውም ሰውን እንዲሳተፋ ይገፋፋሉ።
👉ያም ይሁን ይህ በየትኛውም ሁኔታ እራሳችን የሰራነው ግፍያ ያለጥርጥር በራሳችን ላይ ይሆናል ።
እስቲ አንድ ከሰማሁት ላጫውታችሁ።
ከእለታት አንድ ቀን አንዱ ከሚስቱ ጋር በሆነው ባልሆነው ይነታረኩና በሆነ ነገር አንስቶ ጭንቅላቷ ይላታል። እናም ሚስቱ ከዚህ አለም ትለያለች።
በዚህ ጊዜ ጭንቀት ውስጥ ይገባና ጓደኛውን በሚስጥር መልኩ ምን ማድረግ አለብኝ? ሲል ይጠይቀዋል።
ሁለቱ ሰዎች እራሳቸው ይተዋወቁ እንጂ ቤተሰቦቻቸው አያውቁም አንዱን የአንዱ ማለት ነው።
እናም ምክር ተጠያቂው ጓደኛ እንዲህ ሲል ምክሩን ለገሰው።
ነገ ጥዋት በዚህ በኩል የሚያልፍ ወጣት ወንድ ካገኘህ አስተባብለህ ቤት አስገባውና
ገድለኸው ከሚስትህ ጋር አስተኛው ። ከዚያም ውጭ ወጣና ጩህ ሚስቴ ከሌላ ወንድ ጋር ተኝታ አግኛት በንዴት ገደልኳት በል ይለዋል።
ምክር ጠያቂው ጥዋት አንድ ዘለግላጋ ወጣት ያገኝና እንደ ተባለው ያደርግና ውጭ ወጥቶ ጩኸቱን ያቀልጠዋል።
ሰውም ተሰበሰበ መካሪም ተመካሪም ከህዝቡ ጋር ወደ ቤት ይገባሉ ወደ ጀናዛው ሲጠጉ የተከሰተው ነገር ግፍ ይገለበጣል እንደሚባለው የተገደለው የመካሪው ልጅ ነው።
ስለዚ በመጥፎ ሰዎችን ስንመክ መጀመሪያ ማሰብ ያለብን ለራሳችን ነው።
ጨው ለራስህ ብለህ ጣፍጥ አልያ.......
ግሩፕ
https://t.me/Dimase_11
ቻናል
✍️ጁሀር ኡመር
https://t.me/officialdemas