TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
  • flag English
    Site language
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Sign In
  • Catalog
    Channels and groups catalog Search for channels
    Add a channel/group
  • Ratings
    Rating of channels Rating of groups Posts rating
    Ratings of brands and people
  • Analytics
  • Search by posts
  • Telegram monitoring
الۡفِرۡقَتُ نَاجِيَة

20 May 2025, 19:25

Open in Telegram Share Report

በዩኒቨርስቲ ካሉ መጥፎ ልማዶች መካከል፦

➧ እንደሚታወቀው ዩኒቨርስቲ ማለት የአስተሳሰብ ለውጥ የሚመጣበት የስልጣኔ መስመሩ የሚገኝበት ከሌላው በተሻለ መልኩ ሀገር ለመረከብ ቤተሰብ ለመምራት ወዘተ የተሻለ መንገዶች የሚቀመሩበት መድረክ ነው ተብሎ ይታሰባል።
➜ ከመሆኑም ጋር የሰለጠኑ ሀገር ለመረከብም ሆነ ለየትኛውም ሀላፊነት ዝግጁ የሆኑ ተማሪዎች እንዲመመረቁ ሁሉ በሌላ በኩልም ከመሰልጠን ይልቅ መሰይጠን፣ ከመትጋት ይልቅ መተኛት፣ ከመለወጥ ይለቅ መቀወጥ፣ ከመማር ይልቅ መሽቀርቀር... የሚያምራቸው በርካቶች ናቸው።
➧ እዚህ ስራ ፈቶች ትምህርቱን ትተዋልና የሚቀላቸው የተለያዩ ፈሳዶችን ወደተማሪዎች ማምጣት ነው። በተለይም ተመራቂ ተማሪዎችን ወደተለያዩ ጥፋቶች ለማስገባት የሚጥሩ የሸይጧን አገልጋዮች በርካታ ናቸው። Half life, GC birth day... እያሉ በርካታ ኮተቶችን ወደተማሪዎች ያስጠጋሉ።
🔎 አንቺ ሙስሊም እህቴ ሆይ! አንተ ሙስሊም ወንድሜ ሆይ! እነዚህ ስራ ፈቶች ወደፈበረኳቸው ኮተቶች ዘወር እንዳትሉ እናንተን አይመለከትም። እናንተኮ የላቀ አላማ ያላችሁ የዘላለሙን ህይወት ለመውረስ ጉዞ የጀመራችሁ የሀያሉ አላህ ባሮች ናችሁ።

➜ በተለይ ደግሞ አብዛኛው ሙስሊም ተማሪ ጭምር የሚሳተፍበት ተመራቂዎች ከመመረቃቸው በፊት አብረው ለአመታት ከቆዩዋቸው ጓደኞቻቸው ጋር እንዲሁም ከመምህራን ጋር በመሆን የተለያዩ ዝግጅቶችን በማዘጋጀት ሴትም ወንድም በተቀላቀለበት መልክ በአንድ ቦታ በማሳለፍ የሚከውኑት ዝግጅት አለ። ይህ ድርጊት በሚከተሉት ሰበቦች አይፈቀድም።
1ኛ ያለምንም አስቀዳጅ ምክንያት ኢኽቲላጥ አለበት። ❴ካፊር ሴቶችም ወንዶችም ሙስሊም ሴቶችም ወንዶች ያለምንም ግርዶሽ ይደባለቃሉ❵
2ኛ አብዛኞቹ እንደሚያደርጉት ሴቶችም ወንዶችም ዝግጅት ያቀርባሉ። ❨ግጥም፣ ምስጋና፣ ጭውውት ወዘተ❩ ሴት ልጅ ወንዶች ባሉበት ማንኛውም ነገር ማቅረብ አትችልም። ❮{ስለሙስሊሟ እያወራሁ እንደሆነ ተገንዘቡ}❯
3ኛ በካሜራ የታጀበ የፎቶ ትርዒት ሊያደርጉት ይችላሉና በቀጥታ ከሸሪዓ ጋር በሚቃረን ተግባር ተሳታፊ ለማድረግ ያቀርባል።
4ኛ ከባድ ፈተና ይፈጠራል።
   🔎 ተማሪዎቹ ወደ ፕሮግራሙ ሲሄዱ ለምርቃት ያሰፉትን ሙሉ ልብስ (ሱፍ) በመልበስ ነው። ሌላም የሚዋቡበት ነገር ካለ ለመፈፀም ወደኋላ አይሉም። በዚህ መልኩ ሙሽራ ከመሰለ በኋላ ከሴቶች ፊት ይቀርባል። እሷም አላህን ካልፈራች ሽቅርቅር ብላ ትመጣለች። በየመሃሉ እየተያዩ ፕሮግራሙ ይቀጥላል። በሱፉ ገጭ ብሎ ፕሮግራም ሊያቀርብ ከፊቷ ገጭ ይላል። ልብ ይባል 98% የሚሆነው ተማሪ ያላገባ (ማግባት የሚፈልግ ነው) በዚህ ሁኔታ ይቀጥላሉ። ታዲያ ሴቶች አይፈተኑምን? በጣም ይፈተናልንጅ! ወንዱም በተመሳሳይ መፈተኑ አይቀርም። በዚህ ላይ የሸይጧን ሴራ እና የነፍስያ ድክመት ሲደመርበት የሚፈጠረውን አስቡት!

➧ በየትኛውም ዩኒቨርሲቲ የምትገኙ ሙስሊም ወንድም እህቶች ሆይ! በዚህ አይነት ዝግጅት ላይ አትሳተፉ! መምህሮቻችንን እናመስግን ካሉ በአግባቡ ይሁን እንጂ በምስጋና ስም በሱፍ ሽክ ብሎ በመገኘት ለምስጋና ነው ብሎ መፎገር ሸም ነው። በዚህ አይነት ቀውጢ ካላመሰገንከኝ የሚልህ ካለ የራሱ ጉዳይ ዋና ያንተ የእምነት ጥንካሬ ነው። አንተ ዛሬን የምትኖር ነገን የማታውቅ ጭፍን አይደለህም። በዚህ ሀገር ዘርተህ በነገው ዘውታሪ ህይወት ምርትህን ትወስዳለህና ተጠንቀቅ!

✅ ነገሮችን ቀለል አታድርጉ! ለሸይጧን በር አትክፈት ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ለትንሽ ደቂቃዎች ነው ምን ችግር አለው አይባልም። በሱፍ ሽክ ብለህ እህትህን አትፈትናት! አንድ ልታገባ 20 መፈተን ምን ይሉታል። በእርግጠኝነት ሴቶች ባይኖሩ እንደሙሽራ መዋቡ ትኩረት አያገኝም ነበር ግን እነሱን ለመፈተን ሽር ማለት የልብ መታመምን ያሳያል። አንቺስ ብትሆኚ እህቶ እውነት ቦታዬ ነው ብለሽ አምነሽበት ነውን? አንቺም ተውበሽ ፊትሽን ቀይረሽ በጠባብ ልብሶች ተወጣጥረሽ ከሆነ የምትሄጅው መጨረሻው ይከፋል። ኒቃቢስቷማ ለምን ትሄድ? እራሷን ለመፈተን? አዎ ጥናት ያላንገላታው በስንፍና የተከነባ ከልቡ ውበት ይልቅ የቆዳው ውበት በሚያሳስበው ሚስኪን በሱፍና በመሳሰሉት ፏ ስላለ በሱ ለመፈተን ትሄድ? በፍፁም ቦታሽ አይደለም አዎ በፍፁም።

🏝 እንደጥቅል እኛ ሙስሊሞች በዘፈቀደ የምንቀሳቀስ አይደለንም እያንዳንዱ ተግባራችን ሸሪዓችንን የማይቃረን መሆን አለበት። ከምንም በላይ ጥንቃቄ በሚያስፈልግበት ሁኔታ መዘናጋት ዋጋ ያስከፍላል።

▣ ካለንበት ተጨባጭ አንፃር ተገቢ ስለሆነ በድጋሚ የተለቀቀ መልዕክት

🌴   🌱    🌴   🌱    👇👇👇
https://t.me/AbuImranAselefy/10716
Abu Imran Muhammed Mekonn
በዩኒቨርስቲ ካሉ መጥፎ ልማዶች መካከል፦ ➧ እንደሚታወቀው ዩኒቨርስቲ ማለት የአስተሳሰብ ለውጥ የሚመጣበት የስልጣኔ መስመሩ የሚገኝበት ከሌላው በተሻለ መልኩ ሀገር ለመረከብ ቤተሰብ ለመምራት ወዘተ የተሻለ መንገዶች የሚቀመሩበት መድረክ ነው ተብሎ ይታሰባል። ➜ ከመሆኑም ጋር የሰለጠኑ ሀገር ለመረከብም ሆነ ለየትኛውም ሀላፊነት ዝግጁ የሆኑ ተማሪዎች እንዲመመረቁ ሁሉ በሌላ በኩልም ከመሰልጠን ይልቅ መሰይጠን፣ ከመትጋት ይልቅ መተኛት፣ ከመለወጥ ይለቅ መቀወጥ፣ ከመማር ይልቅ...

107 0 1 4
Catalog
Channels and groups catalog Channels compilations Search for channels Add a channel/group
Ratings
Rating of Telegram channels Rating of Telegram groups Posts rating Ratings of brands and people
API
API statistics Search API of posts API Callback
Our channels
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Read
Академия TGStat Telegram Research 2019 Telegram Research 2021 Telegram Research 2023
Contacts
Справочный центр Support Email Jobs
Miscellaneous
Terms and conditions Privacy policy Public offer
Our bots
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot