الۡفِرۡقَتُ نَاجِيَة


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


የሰለፎችን ኮቴ እንከተል

Related channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


አቂዳና መንሃጅ ቁጭ ብለህ ቅራ

እንቢ ካልክ

ወይ ሱፍያ ሆነህ ጫት ተሸክመህ ትዞራለህ
ወይ ደሞ ተብሊኽ ሆነህ ድስጥ ተሸክመህ ትዞራለህ

🔊Abu_Mehreen

https://t.me/Sunna_tube


✉️ የሮሬ የሆንት ሪሳለ 📨

ኣዋጅ    ኣዋጅ   ኣዋጅ
የስልጤን ኡመት ጴንጤ ወረሬት ሁሊምነ ለንቂነ ዋ!!

🎙 በትሀበዱይ ሸይኺነ በሸይኽ አቡ ዐብዱልሃሊም ዐብዱልሐሚድ ብን  ያሲን አል'ለተሚይ አሱኒይ አስሰ'ለፊይ አላህ የቂራይሙ!
🎙 لفَضِيلَةِ الشَّيخِ أبي عبد الحليم عبد الحميد بن ياسين السني السلفي السلطي اللتمي «حفظه الله ورعاه»

ሁልማሙ Share አሱይ አደራ !!
https://t.me/abu_hessan
https://t.me/abu_hessan


🚫የስልጤ ያለሀ ሀደጊና ውር በል ዋ ውር በል!!

ላኢላሀ ኢለሏህ ሙሐመዱን ረሱሉሏህ ﷺ!፣ ሰበቻው ሞቴንስ አሊ ዋ ሞቴን ሞቴን!! ለደር በፎቶይ ታንዙያሙይ ኪታበ ካፊርቻይ የኛነይ የስልጤ ኡመተ ላኪፍሮት ባሎ ተልትጣሀረይ ዱምኒሙ ሀንፈሶ የፃፉይ የአማርኛይ ፁፈ በስልጢኛ ትሮጎሞኔን ያመጡይ!! ሂነይ ሁለ የለፍቡይ መሳምከ ሚንን ለባሙ የኛይ የስልጤ ኡመት በዲንከ ጠንካረ ሁነተከ ዋ ለዲንከ ኤተ ዋቦተከ ሊሽሎነንከ። ኢኘ ያአሏህነ ዋ የነቢዩነ ኡንገ ኤንዜነ ተጀሀነም ጂረ ሰለጥናኔ የኒዕመቴ ባደ ጀነተ ፉኖ ሂዶተነ ምኜት አተረይማን፣ ሉሃመ በዱቄት በዘይት በሱካር ሰበ አብላልጦቲ (ሸውዶቲ) አነሰይማኒ ሂነይ አሏህነ ዋ ሰዪዳችነ ﷺ ዪሳደቡያን ለአሏህ ወልድ አለይ ይጬኛን ባሎ ሙስተ የሆነይ ኪዝበ ዪኬዝቡቡያነይ ተዱምኒሙ ዮጠይ ጢዠት የፃፍቡዪ ኪታበኒሙ በኢስላማኘት (በስልጥኘቴ) አፍነ ፌሰሮኔ አመጡ፣

ሰብቻው ኢኘስ አይኔን አለን አለገ ሰብ መጣኒ አበሮሰነ ላኪፍሮት የቆተከ ሊከ ኢለፋን የኛዊ የስልጤ ኡመት አይኔን አለ ሰብቻው ሂነይ የመሰለ ኑረይ ዋ ነቢዩምﷺ ማልዳዶምነ ደመኒሙ አፈሰሶኔ የኛን ኤተ ያጄጉነይ ዲነነ ሰብ ሂንኩ ቲትፌቀርቢ ሀንዤን ጂግ አልበልነስ በማልዳዶነ ዘማን ሀዲምከ ተይደፈረይ የሮርነተከ ቄራ ነበራኒ የኛነ ኢት በጄጄ ዞፍ ለሚን ሰብ ሂንኩ ደፈረይ አይነኮ ለትፊቀሮት ሀሰበ እኛነም አይነክ ደፈረነ!? መሰከ ሚንግዝን? ጀዋብምከ ቀለመ ኤት ኡሃም የኛነ ተጫጪጦት ዋ ተዲነ ዡቦኮ ዱኒየነ አቢሶትን ለረከቡኮ፣ ያለፈይ አለፋን ታኩ ለጀምርናኔ ሁልምነ ብላቀትልነያን ጊዝ ሁልም ለልፊነ ዓሊም ዋ ደረሰ በዒልሚከ ሹም በሹምነትከ ቀላ ወደልምከ ኢንዳቻ አባችምከ በቆትከ ልክ የትርዋወጥ!!

📝 የሙሐመዲ ሀፊድ አቡ ሐሳን
https://t.me/abu_hessan
https://t.me/abu_hessan


🖌በሀገረ እንግሊዝ የምትኖር አንዲት ሚስኪን ትውልደ ሶማሊያዊት ሙስሊም ሴት እርዳታን ለማግኘት ወደ ሬዲዮ ጣቢያ ደወለች። አምላክ የለም በሚለው እምነቱ የሚታወቀው ሰው የስልኩን እጀታ አነሳና አዳመጣት።

📍ፋጡማ ቤቷ የሚላስ የሚቀመስ አለመኖሩን በመንገር ለችግሯ መፍትሄ እርዳታ ያደርግላት ዘንድ ተማፅና ቁጥሯን እና አድራሻዋን ሰጥታ ስልኩን ዘጋችው።

✒️ምግብና ሌሎች እርዳታዎች ተዘጋጅተው ወደ አድራሻዋ እንዲያደርስ ለግል ጸሃፊው መመሪያ ሰጠ። እንዲህም አለ፡- 

💠"የእርዳታውን ምንጭ ከጠየቀችሽ ከሸይጣን የተሰጣት ስጦታ መሆኑን ንገርያት" በማለት ሴትየዋ ላይ እየተሳለቀ አዘዛት።

⏺ፀሐፊዋ የሚያስፈልጋትን ሁሉ ሸክፋ ወደ ሴትየዋ ቤት አቀናች።

❇️ምስኪኗ ሴት በደስታ እያነባች የተላከላትን ተቀብላ ወደ ውስጥ ለመግባት በመራመድ ላይ ሳለች ጸሃፊዋ
"የዚህን እርዳታ ምንጭ ማን እንደላከልሽ ማወቅ አትፈልጊምን?"  ስትል ጠየቀቻት።

🔰ይህች ማንበብና መጻፍ የማትችል ሙስሊሟ ፋጡማ የሰጠችው ምላሽ እምነት አልባውን ዶ/ር ቲሞሲ ቬንተርን አስተሳሰብ ቀይራ እስልምናን እንዲቀበል አደረገው ስሙንም ዐብዱልሀኪም ሙራድ ብሎ እንዲሰይም አስገደደው።
ምላሿ ይህ ነበር፡-

❤️ "ለማወቅ አልፈልግም ማንነቱም ግድ አይሰጠኝም። ጌታዬ አላህ አንድን ነገር ከፈለገ ሰይጣኖችም እንኳ ቢሆኑ ይታዘዙታልና"

#አላህ ሆይ" እምነታችንን አፅናልን!!

        
ኮፒ የተደረገ ነው።

https://t.me/Sunna_tube


በዩኒቨርስቲ ካሉ መጥፎ ልማዶች መካከል፦

➧ እንደሚታወቀው ዩኒቨርስቲ ማለት የአስተሳሰብ ለውጥ የሚመጣበት የስልጣኔ መስመሩ የሚገኝበት ከሌላው በተሻለ መልኩ ሀገር ለመረከብ ቤተሰብ ለመምራት ወዘተ የተሻለ መንገዶች የሚቀመሩበት መድረክ ነው ተብሎ ይታሰባል።
➜ ከመሆኑም ጋር የሰለጠኑ ሀገር ለመረከብም ሆነ ለየትኛውም ሀላፊነት ዝግጁ የሆኑ ተማሪዎች እንዲመመረቁ ሁሉ በሌላ በኩልም ከመሰልጠን ይልቅ መሰይጠን፣ ከመትጋት ይልቅ መተኛት፣ ከመለወጥ ይለቅ መቀወጥ፣ ከመማር ይልቅ መሽቀርቀር... የሚያምራቸው በርካቶች ናቸው።
➧ እዚህ ስራ ፈቶች ትምህርቱን ትተዋልና የሚቀላቸው የተለያዩ ፈሳዶችን ወደተማሪዎች ማምጣት ነው። በተለይም ተመራቂ ተማሪዎችን ወደተለያዩ ጥፋቶች ለማስገባት የሚጥሩ የሸይጧን አገልጋዮች በርካታ ናቸው። Half life, GC birth day... እያሉ በርካታ ኮተቶችን ወደተማሪዎች ያስጠጋሉ።
🔎 አንቺ ሙስሊም እህቴ ሆይ! አንተ ሙስሊም ወንድሜ ሆይ! እነዚህ ስራ ፈቶች ወደፈበረኳቸው ኮተቶች ዘወር እንዳትሉ እናንተን አይመለከትም። እናንተኮ የላቀ አላማ ያላችሁ የዘላለሙን ህይወት ለመውረስ ጉዞ የጀመራችሁ የሀያሉ አላህ ባሮች ናችሁ።

➜ በተለይ ደግሞ አብዛኛው ሙስሊም ተማሪ ጭምር የሚሳተፍበት ተመራቂዎች ከመመረቃቸው በፊት አብረው ለአመታት ከቆዩዋቸው ጓደኞቻቸው ጋር እንዲሁም ከመምህራን ጋር በመሆን የተለያዩ ዝግጅቶችን በማዘጋጀት ሴትም ወንድም በተቀላቀለበት መልክ በአንድ ቦታ በማሳለፍ የሚከውኑት ዝግጅት አለ። ይህ ድርጊት በሚከተሉት ሰበቦች አይፈቀድም።
1ኛ ያለምንም አስቀዳጅ ምክንያት ኢኽቲላጥ አለበት። ❴ካፊር ሴቶችም ወንዶችም ሙስሊም ሴቶችም ወንዶች ያለምንም ግርዶሽ ይደባለቃሉ❵
2ኛ አብዛኞቹ እንደሚያደርጉት ሴቶችም ወንዶችም ዝግጅት ያቀርባሉ። ❨ግጥም፣ ምስጋና፣ ጭውውት ወዘተ❩ ሴት ልጅ ወንዶች ባሉበት ማንኛውም ነገር ማቅረብ አትችልም። ❮{ስለሙስሊሟ እያወራሁ እንደሆነ ተገንዘቡ}❯
3ኛ በካሜራ የታጀበ የፎቶ ትርዒት ሊያደርጉት ይችላሉና በቀጥታ ከሸሪዓ ጋር በሚቃረን ተግባር ተሳታፊ ለማድረግ ያቀርባል።
4ኛ ከባድ ፈተና ይፈጠራል።
   🔎 ተማሪዎቹ ወደ ፕሮግራሙ ሲሄዱ ለምርቃት ያሰፉትን ሙሉ ልብስ (ሱፍ) በመልበስ ነው። ሌላም የሚዋቡበት ነገር ካለ ለመፈፀም ወደኋላ አይሉም። በዚህ መልኩ ሙሽራ ከመሰለ በኋላ ከሴቶች ፊት ይቀርባል። እሷም አላህን ካልፈራች ሽቅርቅር ብላ ትመጣለች። በየመሃሉ እየተያዩ ፕሮግራሙ ይቀጥላል። በሱፉ ገጭ ብሎ ፕሮግራም ሊያቀርብ ከፊቷ ገጭ ይላል። ልብ ይባል 98% የሚሆነው ተማሪ ያላገባ (ማግባት የሚፈልግ ነው) በዚህ ሁኔታ ይቀጥላሉ። ታዲያ ሴቶች አይፈተኑምን? በጣም ይፈተናልንጅ! ወንዱም በተመሳሳይ መፈተኑ አይቀርም። በዚህ ላይ የሸይጧን ሴራ እና የነፍስያ ድክመት ሲደመርበት የሚፈጠረውን አስቡት!

➧ በየትኛውም ዩኒቨርሲቲ የምትገኙ ሙስሊም ወንድም እህቶች ሆይ! በዚህ አይነት ዝግጅት ላይ አትሳተፉ! መምህሮቻችንን እናመስግን ካሉ በአግባቡ ይሁን እንጂ በምስጋና ስም በሱፍ ሽክ ብሎ በመገኘት ለምስጋና ነው ብሎ መፎገር ሸም ነው። በዚህ አይነት ቀውጢ ካላመሰገንከኝ የሚልህ ካለ የራሱ ጉዳይ ዋና ያንተ የእምነት ጥንካሬ ነው። አንተ ዛሬን የምትኖር ነገን የማታውቅ ጭፍን አይደለህም። በዚህ ሀገር ዘርተህ በነገው ዘውታሪ ህይወት ምርትህን ትወስዳለህና ተጠንቀቅ!

✅ ነገሮችን ቀለል አታድርጉ! ለሸይጧን በር አትክፈት ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ለትንሽ ደቂቃዎች ነው ምን ችግር አለው አይባልም። በሱፍ ሽክ ብለህ እህትህን አትፈትናት! አንድ ልታገባ 20 መፈተን ምን ይሉታል። በእርግጠኝነት ሴቶች ባይኖሩ እንደሙሽራ መዋቡ ትኩረት አያገኝም ነበር ግን እነሱን ለመፈተን ሽር ማለት የልብ መታመምን ያሳያል። አንቺስ ብትሆኚ እህቶ እውነት ቦታዬ ነው ብለሽ አምነሽበት ነውን? አንቺም ተውበሽ ፊትሽን ቀይረሽ በጠባብ ልብሶች ተወጣጥረሽ ከሆነ የምትሄጅው መጨረሻው ይከፋል። ኒቃቢስቷማ ለምን ትሄድ? እራሷን ለመፈተን? አዎ ጥናት ያላንገላታው በስንፍና የተከነባ ከልቡ ውበት ይልቅ የቆዳው ውበት በሚያሳስበው ሚስኪን በሱፍና በመሳሰሉት ፏ ስላለ በሱ ለመፈተን ትሄድ? በፍፁም ቦታሽ አይደለም አዎ በፍፁም።

🏝 እንደጥቅል እኛ ሙስሊሞች በዘፈቀደ የምንቀሳቀስ አይደለንም እያንዳንዱ ተግባራችን ሸሪዓችንን የማይቃረን መሆን አለበት። ከምንም በላይ ጥንቃቄ በሚያስፈልግበት ሁኔታ መዘናጋት ዋጋ ያስከፍላል።

▣ ካለንበት ተጨባጭ አንፃር ተገቢ ስለሆነ በድጋሚ የተለቀቀ መልዕክት

🌴   🌱    🌴   🌱    👇👇👇
https://t.me/AbuImranAselefy/10716


ወላሂ ይህንን ታሪክ አርብ ማታ አካባቢ አነበብኩት።ሳላቀው አስለቀሰኝ።
ከዛ ቅዳሜ ጠዋት በሂወቴ ትልቅ ፊትና ደረሰብኝ።በፍጥነት ይህንን ታሪክ አስታወስኩኝ።ሃዘኔ ለመቋቋም ብርታት ሆነኝ።

ኡስታዝ በሃሩ ለኔ ብለህ የፃፍከው በሚመስል መልኩ
አንተ ሳታቀው ወደኔ ደረሰ።
ጀዛከሏህ

ለካ ሳናቀው እንኳን ምናሰራጨው መልካም ነገር ለብዙ ሰዎች
ደርሶ ወደአላህ እንዲቃረቡ ሰበብ ይሆናል?


👉  ሸይኽ አልባኒን ያስለቀሰ ታሪክ

   ዒሳም ሃዲይ የተባለ ተማሪ ሸይኽ አልባኒን በተኽሪጅ ያግዛቸው ነበር ። ከሳቸው ጋር ወደ አምስት አመት አካባቢ አሳልፏል ። የኢብኑ ሒባንና ኢብኑ አሳኪርን ኪታቦች ተኽሪጅ እየሰራ በነበረበት ጊዜ ሸይኽ አልባኒ በእነዚህ ኪታቦች ውስጥ ለየት ያለ ጠቃሚ ነገር ስታገኝ ንገረኝ አሉኝ ይላል ።
    የሲቃት ኢብኑ ሒባንን ኪታብ እያነበብኩ ሳለ የአቡ ቂላባን ታሪክ በአምስተኛው ሙጀለድ መጀመሪያ ላይ ለሸይኻችን ማንበብ ጀመርኩ ። በጣም አስገራሚ ሶብሩን ይናገራል ወደ መጨረሻ አካባቢ ደርሼ ቀና ብዬ ሳይ ሸይኻችን በእንባ ታበዋል ። የለቅሶ ሀይል ከውስጣቸው ገንፍሎ ድምፃቸው እንዲወጣ ስላደረገው ተነስተው ወደ ቤት ገቡ ። ከቆይታ በኋላ ተመልሰው መጥተው በጎረነነ ድምፅ ሰላም ብለውኝ ስራቸውን ቀጠሉ ። ታሪኩ ጠቃሚ ስለሆነ ላቅርብላችሁ ይላል የሸይኽ አልባኒው ተማሪ ዒሳም ታሪኩ እንዲህ ነው ።
     ኢብኑ ሒባን ከዐብዱላሂ ኢብኑ ሙሐመድ ይዞ እንዲህ ይላል : –
      " አንድ ጊዜ ወደ ዳርቻ ሄጄ ዒባዳ ለማድረግ ወጣሁ ። ዳርቻ ላይ ማረፊያችን ከቅጠላቅጠል የተሰራ ዳስ ቢጤ ነው ። ወደ ዳርቻ ስደር አሸዋማ በሆነው በባሕር ዳር ባለው ዳርቻ ላይ የሆነ ድንኳን አየሁ ። ወደ ድንኳንኩ ጠጋ አልኩኝ ። በውስጡ የሆነ ሰው አለ ይህ ሰው ሁለቱም እጅና እግሮቹ የሉም ። አይኑም ተይዟል ፣ ጆሮውም ያስቸግሯል ፣ ከአካሉ ሙሉ ጤነኛው ምላሱ ብቻ ነው ። ጠጋ ስል እንዲህ እያለ ዱዓእ ያደርጋል : –
       " አላህ ሆይ በኔ ላይ የዋልከውን ፀጋና ከብዙ ፍጥረታቶችህ ለማስበለጥህ የማሸኩርበት ምስጋና እንዳመሰግንህ አድርገኝ  " ።!!!
    ዐብዱላህም በአላህ ይሁንብኝ ይህን ሰው ቀርቤ መጠየቅ አለብኝ የትኛው ፀጋ ነው አላህ ከሌሎች አስበልጦ የሰጠው ? ፈህም ነው ወይስ እውቀት ወይስ ኢልሃም ነው አላህ በልቡ ላይ የጣለለት አለ ። ዐብዱላሂ ሄደና ሰላም ካለው በኋላ ስታደርገው የነበረውን ዱዓእና ምስጋና ሰምቻለሁ ከአላህ ፀጋዎች የትኛውን ነው የምታመሰግነው አልኩት ይላል ። እንዲህ ብሎ መለሰልኝ : –
     " አላህ በኔ ላይ የዋለውን ፀጋ አታይምን አላህ ሰማይን እሳት እንድታዘንብብኝ አዞ ቢያቃጥለኝ ፣ ተራራን አዞ ቢያጠፋኝ ፣ ባሕርን አዞ ቢያሰምጠኝ ፣ ምድርን አዞ ቢውጠኝ አሁን ካለሁበት ምስጋና አልወገድም ነበር ። እሱን የማመሰግንበት ምላስ እስከሰጠኝ ድረስ !!!!! ነገር ግን እስከመጣህ ድረስ ካንተ አንድ ሀጃ አለኝ ። እንደምታየኝ እኔ ራሴን መጥቀም አልችልም አንድ ልጅ ነበረኝ የሶላት ሳአት ሲደርስ ውዱእ የሚያስደርገኝ ፣ ሲርበኝ የሚያበላኝ ፣ ሲጠማኝ የሚያጠጣኝ,  ነገር ግን ከሶስት ቀን ጀምሮ አጣሁት እኔ እንደምታየኝ ነኝና እስኪ ፈልግልኝ አለኝ ። በአላህ ይሁንብኝ አንድም ሰው በሰው ሀጃ አይሄድም በምንዳ የላቀ በሆነ ባንተ ሀጃ ከመሄድ የበለጠ ብዬው ፍለጋ ቀጠልኩ ።
ብዙም ሳልቆይ በሁለት ኮረብታዎች መካከል አሸዋማ በሆነ ደለል ላይ አውሬ በልቶት አየሁ ‼ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን ብዬ በምን መልኩ ነው ቀርቤ የሆነውን የምነግረው ብዬ ጭንቀት ውስጥ ገባሁ ። የተወሰነ ጊዜ በሀሳብ ከተሰወርኩ በኋላ መመለስ ጀመርኩ ።
    መንገድ ላይ እያለሁ የነብዩላሂ አዩብ ታሪክ ትዝ አለኝ ። ከዛም ደርሼ ሰላም አልኩት መለሰልኝ ቀጥሎም አንተ ጓደኛዬ ነህ አይደል አለኝ አው አልኩት ። ጉዳዬን ምን አደረከው አለኝ ።
እኔም አላህ ዘንድ አንተ ነህ ወይስ አዩብ ነው የበለጠ ቦታ ያለው አልኩት ።
እሱም አዩብ አለኝ ።
እሺ ጌታው ምን እንዳደረሰበት ታውቃለህ አይደል በአፍያው ፣ በልጆቹና በሀብቱ ፈትኖታል አይደል አልኩት ።
እሱም አው አለኝ ።
ታዲያ ጌታው እንዴት አገኘው አልኩት ።
እሱም ታጋሽ ፣ አመስጋኝ ሆኖ አገኘው አለኝ ።
አዩብ ጌታው በሱ ላይ ያደረሰበትን ቤተሰቦቹንና ጓደኞቹን እስከሚያስገርም ወዶ ተቀብሏል አይደል አልኩት ።
እሱም አው አለኝና አሳጥረው አላህ ይዘንል አለኝ  ።
ልፈልገው የላክኸኝ ልጅ አውሬ በልቶታል አላህ አጅርህን ያብዛልህ ትእግስቱንም ይስጥህ አልኩት ።
የመከራው ባለቤትም እንዲህ አለ " ምስጋና ለዚያ ከዘሬ ውስጥ እሱን አምፆ በእሳት የሚቀጣው ያልፈጠረ ለሆነው ጌታዬ የተገባ ይሁን " ብሎ  ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን አለና የማቃሰት ድምፅ አውጥቶ ሩሑ ወጣ ። ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን ብዬ ትካዜ ውስጥ ገባሁ ።
     ትቼው ከሄድኩኝ አውሬ ይበላዋል ቁጭ ካልኩም ምን እንደማደርግ አላውቅም ብዬ በላዩ ላይ በነበረው ፎጣ ሸፍኜው ቁጭ ብዬ ማልቀስ ጀመርኩ ። ብዙም ሳይቆይ አራት ሰዎች ሲያልፉ አዩኝና መጡ ። ምንድነው ነገርህ አሉኝ ታሪኩን ነገርኳቸው ። እስኪ ክፈተው አሉኝ ከፈትኩት ። ተንበርክከው በአይኖቹ መካከል ይስሙት ጀመር ሐራም ያላየ አይን ይላሉ ። እጅና እግሮቹን እየሳሙ ሰው ሲተኛ ለጌታቸው በመስገድ ያልተኙ አካሎች ይላሉ ። አላህ ይዘንላችሁ ለመሆኑ ይህ ሰው ማን ነው አልኳቸው ። እነርሱም አላህና ነብዩን በጣም ይወድ የነበረው አቡ ቂላባ የኢብኑ ዐባስ ባልደረባ ነው አሉኝ ። 
     አጥበን እኛ ጋር በነበረ ልብስ ከፍነን ቀበርነው ። ሰዎቹም ሄዱ እኔም ወደ ዒባዳ ቦታዬ ሄድኩ ። ማታ ላይ ጋደም አልኩኝ የተኛ ሰው እንደሚያየው ያን የአላህ ባሪያ በጀነት ጨፌ ላይ የጀነት ልብስ ለብሶ የሚከተለውን የቁርኣን አንቀፅ ሲቀራ አየሁት :–

  «سَلَامٌ عَلَيْكُم بِمَا صَبَرْتُمْ ۚ فَنِعْمَ عُقْبَى الدَّارِ»
             الرعد  ( 24)
«ሰላም ለእናንተ ይኹን፡፡ (ይህ ምንዳ) በመታገሳችሁ ነው፡፡ የመጨረሻይቱም አገር ምን ታምር!» (ይሏቸዋል)፡፡

    አንተ ያ ጓደኛዬ አይደለህምን አልኩት ። አው አለኝ ። ታዲያ ይህን ደረጃ እንዴት አገኘኸው አልኩ ። አላህ ደረጃዎች አሉት በመከራ በመታገስ ፣ በደስታ በማመስገን ፣ አላህን በድብቅም በግልፅም በመፍራት እንጂ የማይገኝ አለኝ " ።

    አስሲቃት ሊብኒ ሒባን የአምስተኛው ሙጀለድ መጀመሪያ የአቡ ቂላባ ታሪክ

https://t.me/bahruteka


👉 ሐዲስ የሃፈዛችሁ ተጠቀሙበት
       🌱🌱🌱🌱🌱

إعلان   ማስታወቂያ

▣ تعلن الملحقية الثقافية بسفارة المملكة العربية السعودية بأديس أبابا عن موعد تصفيات مسابقة السنة النبوية للرجال في أثيوبيا في نسختها الثانية لعام 1446 هـ - 2025 م؛ وذلك يوم الأحد 26/12/1446 هـ - 22/06/2025 م - 15 سني2017 بالتقويم الأثيوبي.

▣ የሳኡዲ አረቢያ ኤምባሲ የባህል ዘርፍ 2ተኛ ዙር ሀገር አቀፍ የወንዶች ሀዲስ ሂፍዝ ዉድድር ለእሁድ - ሰኔ 15-2017 ተዘጋጅቷል።

📘 عنوان الكتاب: بلوغ المرام من أدلة الأحكام - المؤلف: أحمد بن علي بن حجر العسقلاني - المحقق: سمير بن أمين الزهيري

📘 በዚህኛው ዙር ለውድድር የቀረበው ኪታብ በሰሚር ኢብኑ አሚር አልዙሀይሪ አርትኦት የተዘጋጀው የኢብኑ ሀጀር አል አስቀላኒ ቡሉገ-ል-መራም ሚን አዲለቲ-ል-አህካም ነው።
رابط التحميل:   የመፅሐፉ PDF: https://down.ketabpedia.com/files/bkb/bkb-ha1853-ketabpedia.com.pdf

🌴 الفروع التي يتم التسابق عليه (الاشتراك في مستوى واحد فقط)
الفرع الشروط
الأول حفظ أحاديث من رقم ١- ٥٧
الثاني حفظ أحاديث من رقم ١- ١٠٨
الثالث حفظ أحاديث من رقم ١- ١٥٠
الرابع حفظ أحاديث من رقم ١- ٢٠٣

🌴 የመወዳደሪያ ደረጃዎች (አንድ ሰው በአንድ ደረጃ ብቻ ነው መወዳደር የሚችለው)
1. 1 - 57 ያሉ ሀዲሶችን መሐፈዝ
2. 1 - 108 ያሉ ሀዲሶችን መሐፈዝ
3. 1 - 150 ያሉ ሀዲሶችን መሐፈዝ
4. 1 - 203 ያሉ ሀዲሶችን መሀፈዝ

ለመመዝገብ በዋትስአፕ ቁጥር:- للتسجيل
📲 +251928933333
📲 +251945777744

🌴    🌱     🌴    👇👇👇
https://t.me/AbuImranAselefy/10714


Galaxy m15
Storage 128/6
Network 5g
battery 6000mAh
ሰሞኑን የተገዛ ነው ብሩን አሁን ስለፈለኩት ነው
ዋጋ አዳማ ላላቹ 19,500
ሌሎች 20,000

@Abu_Mehreen
👆እዚህ ላይ contact አርጉ


♨️ በትዳር ስም አታላዮች
🌴¯¯¯🌱¯¯¯🌱¯¯¯¯¯🌴

⁉️ ሸይኻችን ❝አንዳንድ ወንድሞች የሱና እህቶቻችንን በትዳር ስም የሚሸነግሉ ወጣቶች አሉ❞ ምን ይመክራሉ?
⁉️ በነዚህ አጭበርባሪ ሰዎች የሚሸወዱ እህቶችንስ ምን ይመክሩልናል?

✅ ወላሂ ሰው አይቀመስ እንደሚባለው ሰዎች የተለያዩ ባህሪዎች ስላሏቸው ተጠንቀቁ!
✅ በእህቶቻችን ገንዘብ፣ ጊዜ እና ስነ-ልቦና ላይ የምትጫወቱ ሰዎች ሆይ! አላህን ፍሩ! አላህ አይለቃችሁም!
✅ አንድ ሴትን ከመበደልህ በፊት እናትህን እህትህን አስታውስ!
✅ እህቶቻችን ደግሞ ገንዘባችሁን ክብራችሁን ጠብቁ!
✅ አገባሻለሁ እያሉ ከሚዘርፉ አደገኛ አጭበርባሪ ሰዎች ራቁ!!!

🎙 በሸይኽ ዐ/ሐሚድ حَفِظَهُ الله

💬 የፍቅር ቤት ❨ @YeFkrBet_1❩

💬 ለተጨማሪ ነጥቦች ↙️
🌐
https://t.me/YeFkrBet_1


ኢብኑ_ተይምያ 
መስአላዎች ከያዘ የሚገባበት ጥልቀት ሲታይ።
ምድርን ከአንድ በኩል ቀዶ ገብቶ በሌላ በኩል ሰንጥቆ እንደሚወጣ ቢጤ ነው።

የሱና አንበሳ
አላህ ይርኸመው።

🔊Abu_Mehreen
https://t.me/Sunna_tube


لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ الْعَظِيمُ الْحَلِيمُ
  لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ رَبُّ الْعَرْشِ الْعَظِيمِ
  لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ رَبُّ السَّمَاوَاتِ
  وَرَبُّ الْأَرْضِ وَرَبُّ الْعَرْشِ الْكَرِيمِ


ኢብኑ_ተይምያ እንዲህ ይላል።
አላህ ኸይር የሻለት ሰው ሁሉ አላህ በዲኑ ግንዛቢ ሊሰጠው ግድ ነው።በዲኑ ግንዛቤ ያልሰጠው ሰው ደግሞ አላህ ኸይር አልሻለትም።
መጅሙእ አል_ፈታዋ 28:80

🔊Abu_Mehreen

https://t.me/Sunna_tube


الصلاة_على_النبي_ﷺ،_فضلها،_وكيفيتها.pdf
591.5Kb
📝 الصلاة على النبي ﷺ : فضلها، وكيفيتها
•عبدالمحسن العباد
•#مجلة_الجامعة_الإسلامية_للعلوم_الشرعية_بالمدينة_المنورة


አስተማሪ ታሪክ።

ሰውዬው የሴቶችን ተፈጥሮአዊ ተንኮል ሳልረዳ አላገባም ይልና ይህንን ጥያቄው መልስ ለማግኘት ከአካባቢው ርቆ መንገድ ይጀምራል።
አጋጣሚ መንገድ ላይ ጉድጓዶ ውስጥ ውሃ ስትቀዳ አንዲት ቆንጆ ሴት ይመለከታል። በአጠገቧ ስያልፍ ቀረብ አለና እንዲህ አላት።
የሴት ልጅ ተፈጥሮአዊ ተንኮል ምንድነው ?አላት
እሷም መልስ ሳትሰጠው ከፍ ባለ ድምፅ እሪሪሪ ብላ ጮኸች ።ሰውዬውም በድንጋጤ። ምንድነው ምያስጮኽሽ? አላት እሷም።
የሰፈሩ ሰው ሰምቶ መጥቶ አስቸገርካት ብሎ እንዲገልህ ነው። አለችው እሱም እኔኮ ላስቸግርሽ አደለም ሳይሽ መልካም ሴት ስለመሰልሽኝ መልስ ፈልጌ ነው የጠየኩሽ አላት።
ልጅቷ ውሃ መቅጃዋ አወጣችና ከአናቷ ጀምራ ውሃውን በላይዋ በመድፋት ልብሷን አበሰበሰችው።
በዛው ፍጥነት የሰፈሩ ሰዎች ከየ አቅጣጫው በጩኸቱ ሰበብ መጡና ተሰበሰቡ።

ምንድነው ምን ሆንሽ አሏት እሷም
ውሃ ስቀዳ ጉድጓድ ውስጥ ወድቄ ይሄ ሰውዬ ደርሶ አዳነኝ አለቻቸው። ሰዎቹም እሱን ማመስገንና ማሞገስ ጀመሩ።

ሰውዬ ይህንን የማድረግሽ ሚስጥር ምንድነው ብሎ ጠየቃት።እሷም ሴት ልጅ ማለት እንደዚህ ነች ካስቸገርካት ትገልሃለች። ካከበርካት ከደረጃህ ከፍ ታረግሃለች ብላ መለሰችለት።

https://t.me/Sunna_tube


ፖለቲካ ወይስ ረድ?

ሰሞኑ ኢኽዋኖች ከየ ጉድጓዳቸው ወጥተው
አህባሾችን ሲተቹና ምላሽ ሲሰጡ አየሁኝ።

ጥሩ ነው ግን አህባሽ ዘወትር ኡማውን
ጀሃነም የሚነክር ሽርክ ስያስተምሩ ወደ
ቀብር አምልኮ ሲጠሩት የጥመት አቂዳ
ሲሰብኩት ዝምታ ተመርጦ ነበር። ከዛም
አልፎ አደባባይ እየተቃቀፉ በሰዎች ላይ
ተልቢስ እየተደረገ ተቆየ።

ዛሬ አንድ አህባሽ ስለ ሰለምቴዎች ተናገረ
ተብሎ በየ ኹጥባው ማውራት ምን የሚሉት
ነው? እኔ ይበልጥ የገረመኝ ግለሰቡ ላይ
ለመመለስ በተነሱበት ኢብኑ_ተይምያን ማንሳታቸው ነው።

ቆይ ሲጀመር ኢብኑ_ተይምያ መች ኢኸኽዋን
ነበረ? ዛሬ ለምን ወደዳቹት? ታዳ ለምን የሱን
ትግል ና ዳእዋ ዘወትር ለኡማው አትናገሩም?

👉የምርጫ ሰሞን ስለሆነ ተቃራኒው (አህባሽ)
ድምፅ እንዳያገኝ ሰዎችን ዘንድ ቦታ ለማሳጣት
እንጂ የሀቂቃ  ንግግሩ አሳስቧቹ አደለም።

ምነው ሽርካቸው ጭፈራቸው ላይ ስትተባበሩ
ያላሳሰባቹ ቀብር አምልኮ ቦታ ሄዳቹ ምን እናግዝ? እንዳላላቹ ዛሬ ይሄ ንግግር ብቻ
ለምን ከበዳቹ?

እንኳን ሰለምቴዎች አልሰለሙም መባል ቀርቶ
ሙስሊሙ አደል እንዴ ውሃብያ ካፊር ነው አያሉ
ሚናገሩት ? ታዳ የት ነበራቹ ኡማውን ካፊር ሲሉ?

👉በተደጋጋሚ ለስልጣን መጠቀምያ የሚሆን
ሰው ዳግም አታገኙም።

https://t.me/Sunna_tube


ከጀርባ ምንም ያህል ብትለፋ ሰዎች
ዋጋ ሚሰጡህ ውጤትህ አይተው ነው።

አላህ ግን ምንምኳ ውጤት አልባ ብትሆን
በልፋትህ ብሎም በንያህ ውጤት ይሰጥሃል።

🔊Abu_Mehreen

https://t.me/Sunna_tube


ሙብተዲእን ማወደስ።።።።።።።።።።።
እከሌ እከሌን አወደሰ  እከሌ ከእከሌ አብሮ ሆነ በእከሌ ቴሌቭዥን ታየ ታዳ ምን ይጠበስ?

ይቺ ሃገራችን የወረረችው ቃኢዳ ከሰለፎች
ዘንድ ትታወቃለችን?? ኡለሞቻችንስ እንዴት ያዩታል።?

ذكر ابن بطة في الإبانة عن ابن عون رحمه الله أنه قال : «الذي .«يجالس أهل البدع أشد علينا من أهل البدع
(2/473) الإبــانـــة


☝️هل الثناء على المبتدع يخرج من السنة؟
السلف والسلفيون كلهم مجمعون على معادات أهل البدع واحتقارهم وتخذيلهم قال الفضيل ابن عياض "من وقر صاحب البدعة فقد أعان على هدم الإسلام"
قال الصابوني "واتفقوا مع ذلك على القول بقهر أهل البدع وإذلالهم وإخزائهم وإبعادهم وإقصائهم والتباعد منهم…" اهـ عقيدة السلف صـ ٢٣١.

إن كان السلف أجمعوا على تخذيلهم وإذلالهم وإخزائهم علمنا من هذا أن موقف السلف خلاف الثناء علهم وقد قال ابن تيمية "نعم من خالف الكتاب المستبين والسنة المستفيضة أو ما أجمع عليه سلف الأمة خلافا لا يعذر فيه فهذا يعامل بما يعامل به أهل البدع" ٢٤/ ١٧٢

فمن أثنى المبتدع يعامل معاملة المبتدع فمن معاملة المبتدع التبديع والتضليل له والتحذير منه وغير ذلك
وقد سؤل العلامة ابن باز الذي يثني على أهل البدع ويمدحهم هل يأخذ حكمهم؟ فأجاب "نعم ما فيه شك من أثنى عليهم ومدحهم هو داع لهم يدعوا لهم هذا من دعاتهم نسأل الله العافية" اهـ شرح فضل الإسلام فجعل المثني على المبتدع مثله بل من دعاة منهجه.

☝️وقال الشيخ أحمد ابن يحيى النجمي "ومن أثنى على المغراوي وبعد أن علم نزعته الخارجية يجب أن يلحق به ولا أعلم أن أحدا من أهل السنة المعروفين سيتوقف عن إلحاقه يه" وانظر قوله (يجب أن يلحق به) وقوله (لا أعلم أحدا من أهل السنة يتوقف عن إلحاق المثنى على المبتدع به)

☝️وقال العلامة حمود التويجري رحمه الله تعالى "فمن كان منهم ـ من الذين يمدحون التبلغيين ويجادلون عنهم ويهماشونهم ـ عالما بأن التبلغيين من أهل البدع والضلالات والجهالات وهو مع هذا يمدحهم ويجادل عنهم بعد العلم بهم فإنه يلحق بهم ويعاملون بما يعاملون به" اهـ القول البليغ صـ ٢٣٠ فانظر أيها السلفي قوله "فإنه يلحق بهم ويعاملون بما يعاملون به"

فإن قال قائل بعض أهل العلم من العلماء السلفيين لا يرى أن الثناء على أهل البدع مخرجا من السنة مطلقا بل يقيده بالثناء على بدعته قيل له: هذا خلاف اطلاق كلام السلف والعلماء لأنهم لم يقيدوا الثناء بالبدعة لإخراج الرجل من السنة قال الدكتور عبد العزيز الريس "ومن الأخطاء الشائعة ما يذكره بعضهم أنه إن عُظم لبدعته فإن كلام السلف منزل على هذا بخلاف إن عظه لغير بدعته.
وهذا خطأ وهو مخالف لإطلاق السلف وكلامهم العظيم" اهـ من موقعه



وقال أبـي قــلابــــة: «لا تجالسوا أهل الأهواء ولا تجادلوهم فإني لا آمن أن يغمسوكم في الضلالة، أو يلبسوا عليكم في 
.«الدي الشريعة للآجري ص (67)


قال الفضيل بن عياض – رحمه الله
من صاحب بدعة فقد أعان على هدم الاسلام، ومن  عظ تبسم في وجه مبتدع فقد استخف بما أنزل الله على محمد- صلى الله عليه وسلم-، ومن زوج كريمته من مبتدع فقد قطع 
رحمها، ومن تبع جنازة مبتدع لم يزل في سخط الله حتى
يرجع شرح السنة للبربهاري ص (139)


👉መከተል የፈለከ በሞት የቀደሙትን ይከተል በሂወት ያለ ፊትና አይታመንለትም።
አላህ የሰለፎች ላይ አፅንቶ ይግደለን።

✍️جمعته

🔊Abu_Mehreen

https://t.me/Sunna_tube
https://t.me/Sunna_tube


وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا مِنْ قَبْلِكَ رُسُلًا إِلَىٰ قَوْمِهِمْ فَجَاءُوهُمْ بِالْبَيِّنَاتِ فَانْتَقَمْنَا مِنَ الَّذِينَ أَجْرَمُوا ۖ وَكَانَ حَقًّا عَلَيْنَا نَصْرُ الْمُؤْمِنِينَ
٣٠-٤٧
ካንተ በፊትም ነብያቶች ወደየህዝቦቻቸው በርግጥም ላክን። በግልጥ ማስረጃም መጧቸው።ከነዚያ ካመፁትም ተበቀልን።
ሙእሚኖች መርዳት በኛላይ ተገቢ ሆነ።
30:47

https://t.me/Sunna_tube


ቀለበትና የቁርአን አያው ምን አገናኛቸው?
ኒካህ ማለት ቀለበት ነው እንዴ ወይስ
የካፊሮችን ጋብቻ ነው መግለፅ ምትፈልጉት?

ሁሉም ፕሮፋይል አርጎት ሳይ ይገርመኛል።
ከቻልን ቀለበት ሱና አርጎ ከመያዝ እንቆጠብ
የኛ ሱና ሳይሆን የካፊሮች ነው።

🔊Abu_Mehreen

https://t.me/Sunna_tube

20 last posts shown.

322

subscribers
Channel statistics