♦ ለሹበሀ ሰባት መልስ
ባለፋት ተከታታይ ሳምንታት እንዴት ቁርዓን ስለ ውርስ ህግ ባዘዘው አከፋፈል ውስጥ የሂሳብ ስህተት እንደፈጸመ አይተናል።
ይህ በቁርዓኑ ውስጥ የሚገኝ ግልጽ ስህተት ሆኖ ሳለ ሙስሊም ሰባኪያን እሱን ለመከላለከል ብዕራቸውን አንስተዋል። ለዚያም ከበቂ በላይ ምላሽ ሰጥተን ነበር
ዛሬ ደግሞ እንደተለመደው እነዚሁ ሙስሊም ሰባኪያን መልስ ሰጥተናል ብለው ተነስተዋል። ጌታ ኢየሱስ ቢፈቅድ የነሱን ምላሽ እንዳስሳለን
🚩 መሰረታዊ ነጥባችን
የኛ መሰረታዊ ነጥብ፥ ቁርዓን በአከፋፈል ሂደቱ ውስጥ ከሀብቱ የበለጠ የአከፋፈል እጅ ሰጥቷል (112.5%) ይህንን የቁርዓኑን ስህተት ቁርዓናዊ በሆነ ውጫዊ ሂሳብ (ዐውል) ማረም ማለት የቁርዓኑን ስህተት ማጽደቅ ነው
እነሱ ግን እኛ ያላልነውን በማለት፥ የኛን ነጥብ አጣሞ በማቅረብ፥ ፍሬ ነጥብ ሳያቀርቡ "አላዋቂ" ብለውናል። እስቲ አብረን እንመልከት
✒ እነሱ
1ኛ) ቁርአን ለወራሾች የሸነሸናቸው የውርስ ድርሻዎች መፈጸም ባለባቸው አጋጣሚ ተደምረው የግድ አንድ መምጣት አለባቸው በፍጹም እንደማይል ይሰመርበት፡፡ ኹሉም ድርሻዎች ተደምረው አንድ ሊሰጡ፣ ሊበልጡ ወይም ሊያንሱ ይችላሉ፡፡ ለዚህ ሐሳባችን ቡኻሪ ( ሐዲስ ቁጥር 6732 ወይም 5) እና ሙስሊም (1615) በጋራ የዘገቡት የመልክተኛው (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ቃል ግልጽ ማስረጃ ይኾናል፡-
ألْحِقوا الفرائض بأهلها، فما أبقت الفرائض فلأَوْلَى رجلٍ ذَكر
“ውረስን ለሚገባቸው አካላት አድርሱ፤ የተረፈ ካለ ለሟቹ ቅርብ ለኾነው ወንድ ልጅ ስጡት”
“የተረፈ ካለ” የሚለው ቃል ኹሉም ድርሻውን ካነሳ በኋላ የሚተርፍ ሊኖር እንደሚችል፣ በሌላ አባባል የወራሾቹ ድርሻ የግድ አንድ ሊመጣ እንደማይችል በግልጽ የሚያስረዳ ነው፡፡ ይህንን ሐዲስ ምናልባት ወገናችን ከተረዳው በሚል በሹብሀ ስድስት ላይም ጠቅሼው ነበር፡፡ ኾኖም ግን ያው የገልባጭ ነገር ኾነና “ይህ ከኛ ነጥብ ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም” ብሎ በለሆሳስ ዘሎታል፡፡
♦ መልስ
ከላይ በምንመለከተው "ምላሽ" ውስጥ ሁለት ከባባድ ስህተቶች አሉ።
አንደኛው ስህተት፥ የግድ አንድ መምጣት አለበት አይልም ማለታቸው ነው። ይህ ፍጹም አመክንዮአዊ ያልሆነ ስሁት ሙግት ነው። ምን ማለት ነው የግድ አንድ ይምጣ አይልም? ይህ ማለት አይሳሳት አይልምና ቢሳሳት ችግር የለዎም ማለት ነው።? ምክንያቱም 112.5% ከመቶ እጅ ስህተት ነውና
ሲቀጥል ጉዳያችን ክፍፍሉ ከ100% ይበልጣል ሆኖ ሳለ ከተረፈ ምን መደረግ እንዳለበት የሚናገርን ሀዲስ መጥቀስ ምን ማለት ነው? ተረፈ ማለትኮ ከ100% አንሶ ሲገኝ ነው። ወገኔ! ክፍፍሉኮ 112.5% ሆኗል። ስለዚህ የጠቀስከው ሀዲስ ከነጥባችን ጋር አይገናኝም
✒ እነሱ
ለዚህ ሙግታችን ሌላ ገቢራዊ ማስረጃ ብናይ መልካም ይኾናል፣ ለምሳሌ አንድ ግለሰብ አንዲት ሴት ልጅን ብቻ ትቶ ቢሞት በቁርአን መሰረት ይህች ልጅ ግማሽ ንብረቱን ወይም ½ ኛውን ትወርሳለች፡-
“አንዲትም ብትኾን ለርሷ ግማሹ አላት” አኒሳእ/11
ይህንን ጥቅስ ልብ ብለን ከተረዳን፣ ሟች ጥሎት ከሄደው ንብረት ሴት ልጁ ግማሹን ብቻ ነው የወረሰችው የተቀረው ግማሽ ካልተደመረ በስተቀር አንድ ሊመጣ አይችልም፡፡ ጉዳዩን ስንጠቀልል፣ የቁርአንም ኾነ የሐዲስ የውርስ አስምህሮዎች የወራሾች ጠቅላላ ድርሻ ተደምሮ አንድ መምጣት አለበት እንደማይሉ ልብ ይሏል፡፡ ይህች ብቸኛ ወራሽ ሴት 1/2ኘኛው ከወሰደች በኋላ፣ “አረ’ድ” በሚባል በሌላ የውረስ ሥርዓት ቀሪውን ገንዘብ (1/2ኛውን) ደግማ እንድትወስድ ይደረጋል፡፡ በሌላ አባባል ሴት ልጅ ሙሉ ገንዘብ የምትወርስበት መንገድ እንዳለ ልብ ይሏል፡፡
♦ መልስ
ይህ ከኛ ነጥብ ጋር ባይገናኝም ቁርዓን የሚያዘውን ነገር በጥልቀት እስቲ እንመልከተው።
" አንዲትም ብትኾን ለርሷ ግማሹ አላት" ሱራ 4:11
በዚህ ትዕዛዝ መሰረት ብቸኛይቱ ልጅ 1/2ኛ ትወርሳለች። እናትና አባቱም እርሱ (ሟች) ልጅ ካለው እነርሱ እያንዳንዳቸው 1/6ኛ ይወርሳሉ። ሱራ 4:11
ሚስተም እንዲሁ ባሏ ልጅ ካለው እሱ ከተወው 1/8 ትወርሳለች። ሱራ 4:12
ስለዚህ ስንደምረው 1/2 + 1/6 + 1/6 + 1/8 = 0.95 ~ 1 ነው። ከላይ አንተ የጠቀስከው የትርፍ ህግ የሚመጣው በእንዲህ አይነት ሁኔታ እንጂ በኛ ምሳሌ አይደለም
✒ እነሱ
2ኛ) ቁርአን የሸነሸናቸው ድርሻዎች ከጠቅላላው ገንዘብ አኳያ መከፈል ያለባቸው ሳይኾኑ፣ ሊወርሱ ከመጡ ሰዎች አንጻር እንደኾነ ይታወቅ፡፡ ለምሳሌ ወገናችን ከሌላ ቦታ ገልብጦ ያመጣቸውን ወራሾችን (ሚስት ፣3 ሴቶች፣አባት፣እናት) ብንጠቀም፣ ከነዚህ የወራሽ ስብስቦች መካከል ሚስት (1/8)፣ አባትና እናት እያንዳንዳቸው (ልጅ ወይም ወንድሞችና እህቶች ከሌሉ) (1/6) ፣ 3 ሴቶች (2/3) ከጠቅላላው የሽንሸና ድምር ውስጥ ይወርሳሉ ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ የኹሉንም ድርሻ ስንደምር (1/8 + 1/6+ 1/6+ 2/3) = 9/8 ይመጣል፡፡ የቁርአንን ሕግጋት እዚህ ጋር ስንጠቀም፣ ከሚወረሰው ገንዘብ አኳያ ሳይኾን፣ ከሽንሽኑ ጠቅላላ ድምር 9/8ኛ ውስጥ ሚስት 1/8 ኛውን ትወስዳለች፣ አባትና እናት እያንዳንዳቸው 1/6 …ይወርሳሉ ማለት ነው፡፡
♦ መልስ
ሀሰት! ይህ ጸሐፊ " ቁርአን የሸነሸናቸው ድርሻዎች ከጠቅላላው ገንዘብ አኳያ መከፈል ያለባቸው #ሳይኾኑ፣ ሊወርሱ ከመጡ ሰዎች አንጻር እንደኾነ ይታወቅ፡፡ " እያለ ነው
እውነታው ግን ቁርዓን ንብረቱ እንዲከፋፈል ያዘዘው ሟች ከተወው ጠቅላላ ንብረት ነው።
" ከሁለት በላይም የኾኑ ሴቶች ብቻ ቢሆኑ ለእነሱ (ሟች) #ከተወው ረጀት (ድርሻ) ከሶስት ሁለት እጁ አላቸው። " ሱራ 4:11
" ለእናንተም ልጅ ቢኖራችሁ #ከተዋችሁት ንብረት ለእነርሱ ከስምንት አንድ አላቸው ... " ሱራ 4:12
🚫 ቁርዓኑ በግልጽ ውርሱ ከተተው ንብረት እንደሆነ ይናገራል። " ከመጡት ሰዎች አንጻር.. " የሚለው አፈታት ምንም ቁርዓናዊ መረጃ የለውም!!!
ከዚህ በፊት እንዳልነው፥ ውርሱን በመጡት ሰዎች አንጻር ብንሸነሽነው ቁርዓኑ ከሚለው ያነሰ ይሆናል። ቁርዓን ካዘዘው ያነሰ ካወረስን ደግሞ ቃላቱን እንመለወጥ ይሆናልና። የኛም ነጥብ ይህ ነው
✒ እነሱ
{ዐውል}
ቁርአን ውስጥ ከውርስ አኳያ የተቀመጡ ድርሻዎችን በዚህ መልኩ ከተረዳን ዘንድ፣ ዐውል ስለሚባለው የውርስ ሂደት ትንሽ እናውጋ፡፡ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሱ) ኸሊፋ በነበረበት ዘመን አንዲት ሴት ባሏንና ኹለት እህቶቿን ትታ ሞተች፡፡ ባልና እነዚህ ኹለት እህቶች ወራሾች ኾነው መጡ፡፡ ለባል ልጆች በሌሉበት 1/2 ሲደርሰው ለእህቶች ደግሞ 2/3 ይደርሳቸዋል፡፡ የ 1/2 እና 2/3 “አስል” 6 ነው፡፡ አስሉን ይዘን ስንሸነሽን፣ ባል 3 እጅ ሴቶቹ ደግሞ 4 እጅ ይደርሳቸዋል፡፡ ድርሻቸውን ስንደምር ግን 7 ይመጣል፡፡ ይህ ደግሞ ከአስሉ (6) ስለሚበልጥ ዑመር ምን ማድረግ እንዳለበት ቁርአንን በቅጡ ከሚረዱት ከሰሐባ (ረዲየላሁ ዐንሁም) ጋር ተወያያ፡፡ በኋላም “አስሉ”ን ትቶ “ዐውል” እንዲጠቀም ሐሳብ አቀረቡለት፤ እሱም በሐሳቡ ተስማማና አስሉ 6 መኾኑ ቀርቶ 7 እንዲኾንና ባል 3 እጁን እህትማማቾቹ ደግሞ 4 እጁን እንዲወርሱ ኾንዋል፡፡
ዑመርና ሌሎች ሰሓባ (ረዲየላሁ ዐንሁም) ዐውል ማድረጉን የፈለጉት ችግሩን ለመቅረፍ እንዲያው በዘገደው ከቀጭን ዐየር ላይ የታፈሰ ሐሳብ ይዘው እንዳልኾነና ይልቁንም ከላይ ባስቀደምነው ሐዲስ ኹሉም