የ 1 ጢሞ 2 ማብራሪያ
" አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤"
(1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:5)
በትምህርተ ስላሴ የማያምኑ ወገኖች ይህንን ክፍል በመጥቀስ ትምህርተ ሰ
ስላሴን ለመካድ ይሞክራሉ
እንዲህ ሲሉም ይሰማሉ " በዚህ ስፍራ የአብን እና የኢየሱስን ማንነት እንመለከታለን። አብ አንዱ አምላክ ነው፥ ኢየሱስ ደግሞ አንዱ ሰው ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር ስላሴ አይደለም፥ ኢየሱስም አምላክ አይደለም "
▶ ነገር ግን ይህ ደምዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስን አውድና ክፍሉን ጠንቅቆ ካለመረዳት የመነጨ ነው
በመጀመሪያ ይህ መረዳት ሐዋሪያው ጳውሎስ ስለጌታ በሌላ ስፍራ ላይ የተናገረውን ያላማከለ ነው። ሐዋሪያው በማያሻማ መልኩ ወልድ ከአብ ጋር የነበረ መለኮት መሆኑን፥ በኋላም ስጋ መሆኑን በግልጽ ተናግሯል። (ፊሊ 2:3-7 ቲቶ 2:13)
ሲቀጥልም ይህ ክፍል በኢየሱስ አማካኝነት ወደ አብ እንደምንደርስ የሚናገር ክፍል ነው። ኤፌ 2:18
1ጢሞ 2 በጥንቃቄ ስንመለከተው አንድ ሰው የተባለው ይህ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ብቻ አለመሆኑን እንረዳለን
" ራሱንም ለሁሉ #ቤዛ ሰጠ፥ ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ፤"
(1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:6)
▶ ይህ ክፍል እንዴት ወልድ ሰው ብቻ አለመሆኑን ያሳያል?
ጌታ የሁሉ ቤዛ መባሉ መለኮት መሆኑን የሚያሳይ ነው። ምክንያቱም የትኛውም ሰው ብቻ የሆነ አካል ቤዛ ሊሆን ስለማይችል
" ወንድም ወንድሙን አያድንም፥ ሰውም አያድንም፤ #ቤዛውን ለእግዚአብሔር አይሰጥም፥"
(መዝሙረ ዳዊት 49:7)
መለኮት ያልሆነ ነገር ግን ሰው ብቻ የሆነ አካል፥ ቤዛ ሊሆን አይችልም። በተቃራኒው ደግሞ የሰው ቤዛ እግዚአብሔር እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል
" ነገር ግን እግዚአብሔር ይቀበለኛልና ነፍሴን ከሲኦል እጅ #ይቤዣታል።"
(መዝሙረ ዳዊት 49:15)
በዚህ መሰረት ከ1 ጢሞ 2 ኢየሱስ መካከለኛ የሆነ ሰው ብቻ ሳይሆን፥ ቤዛ የሆነም መለኮት መሆኑን እንረዳለን። ምክንያቱም ጌታ ቤዛ የተባለበት አውድ ለመለኮት ብቻ የሚውል ነው ሮሜና 3:24
➤ ሌላው ከዚህ ክፍል (ከ1 ጢሞ 2:5-6) የምንረዳው መሰረታዊ ነጥብ ደግሞ መለኮት ከአንድ በላይ አካል መሆኑን ነው
በቁ.5 አብ አንድ አምላክ ተብሎ በቁ.6 ደግሞ ኢየሱስ/ወልድ አንድ ቤዛ ተብሏል። በዚህም መሰረት አብና ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት መለኮታዊ አካላት መሆናቸውን እንረዳለን
ይህ አይነቱ አገላለጽ በአዲስ ኪዳን ውስጥ የተለመደ ነው። በ 1 ቆሮ 8:6 ላይ አብን አንድ አምላክ ብሎ ኢየሱስን አንድ ጌታ (ያህዌ) በማለት ሁለት መለኮታዊ አካላት መሆናቸውን ገልጿል
( ስለ 1 ቆሮ 8:6 ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህንን ይጫኑ
http://t.me/TheTriune/155 )
ይህ ደግሞ ከመላው የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ጋር ይስማማል። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን ለኛ ቤዛ ሊሆን የመጣው ወልድ ነው
" በውድ #ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ #ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት።"
(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1:7)
▶ መደምደሚያ
ከ 1ጢሞ 2:5-6 ኢየሱስ መለኮትም ሰውም መሆኑን፥ በተጨማሪም አብና ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት መለኮታዊ አካላት መሆናቸውን እንረዳለን
ጌታ ይርዳን!