የነፍስ መልህቅ


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


ኢየሱስ የነፍሳችን ባላቤት 🙏❤

Related channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


Forward from: Light
🛑 ነፍሴ የምትወደው እርሱ የሚኖረው እኔ ውስጥ ነውና፣ እርሱን ፍለጋ ሩቅ አልሄድም።
       

💕@sela3m

@worlds_light
@worlds_light
join & share


ወፎችን ተመልከቱ 🦅🦆 ፤ #እግዚአብሔር የሚመገቡትን ሰጥቷቸዋል ።
ነገር ግን ሄደው የተሰጣቸውን መፈለግ
አለባቸው ።
ፈልፍለው ካለበት እንዲያወጡ ይጠበቅባቸዋል 🤷‍♂🤷‍♂🤷‍♂
#ለእኛም #ቢሆን #እንዲሁ #ነወ።

#AKILILU

@የነፍስ መልህቅ


የቆዳ ቀለማችን ቢለያይም ሁላችንም በእጣ-ፋንታ ተፀንሰን፣ በአላማ ተፈጥረን፣
ትርጉም ያለዉ አመርቂ ህይወት
ለመኖር
#በእምቅ አቅም የተጠቀለልን ፍጡራን
#ነን 😎


Forward from: Ashe Zeleke
ፀሎት ማለት፣የአባት እና ልጅ ውይይት ነው ፣ እንጅ ያማሩ ቃላትን እየመረጥን የምናደርገው ንግግር አይደለም።


''..... ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነወ፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተነዉ ጋር መዉጫዉን ደግሞ ያደርግላችኃል
1ኛ ቆሮንቶስ 10፥13
@Akililu
@የነፍስ መልህቅ


Forward from: Super christian tube ሱፐር ክርስቲያን ቱብ
ፍቅር እንደዚህ ነው
#አንድ -አባት በማለዳ ተነስቶ በሚኖርበት አካባቢ ወዳለው ወንዝ ሲሄድ በወንዙ ላይ የነበረው ድልድይ ተሰብሮ ይመለከታል ...ድልድዩ ላይ ደግሞ የባቡር ሀዲዲ የተዘረጋበት እና ወደሚቀጥለው ከተማ የሚሄዱ ብዙ ሰዎችን የሚያጉዋጉዝ ባቡር የሚያልፍበት መሆኑን ስለሚያውቅ ቶሎ ወደ ቤቱ በመሄድ ሰራተኞቹን ጠርቶ ሁኔታውን በመንገር ለባቡሩ ሾፌር ምልክት እንዲያሳዩት በጨርቅ ላይ የድልድዩን መስበር የሚገልፅ ፅሁፍ ፅፎ ሰጣቸው ....አንደኛው ሰራተኛ በአምስት ኪሎ ሜትር ሌላኛው በአራት ኪሎ ሜትር ሌላኛው በሶስት ኪሎሜትር ሌላኛውን ደግሞ በሁለት ኪሎ ሜትር ላይ ቆመው ባቡሩ ሲመጣ ምልክቱን እንዲያሳዩ አደረገ .... የባቡሩ ሾፌር ግን የሰራተኞቹን ፅሁፍ አይቶ እንዳላየ ሁሉንም በቸልታ አለፋቸው .... ይህም አባት በሾፌሩ ቸልተኝነት አዘነ .... ባቡሩም ይበልጥ እየቀረበ ሲመጣ የራሱን ልጁን ከወንዙ በአንድ ኪሎሜትር ርቀት ላይ “ እባክህ ድልድዩ ስለተሰበረ ባቡሩን አቁመው " የሚል ፅሁፍ ይዞ እንዲቆም አደረገው ..... ሾፌሩም ሳያቆም ወደ ልጁ ሲደርስ ልጁ ሀዲዱ ላይ ተኛ ........ ባቡሩም ገጭቶት አለፈ ወንዙ ጋር ሊደርስ እጅግ ጥቂት ሜትሮች ሲቀረው የልጁ አጥንት ስብርባሪው የባቡሩ ሰንሰለት ውስጥ ስለገባ ባቡሩ በራሱ ቆመ !!!!! ሾፌሩም ከባቡሩ ወርዶ ሲመለከት እውነትም ከፊት ለፊቱ ያለው ድልድይ ተሰብሮ በጣም ብዙ አዞዎች አፋቸውን ከፍተው ሲያፋሽኩ አየ ....ያኔም ከልቡ አዘነ ለካስ ይህ ልጅ በተለያዩ ሰዎች በርቀት ምልክቶችን አሳይቶኝ አልሰማ ስላልኩት እኔ እና ይህ ሁሉ ህዝብ እንዳንሞት ነው ራሱን መስዋዕት ያደረገው ብሎ አለቀሰ ........በዚያም ልጅ ሞት ህዝቡ ሁሉ ከሞት ዳነ !!!!

እንግዲህ እግዚአብሔርም ለእኛ በተለያየ ጊዜ ነቢያትን ልኮ እየሄድንበት ካለው የሀጥያት መንገዳችን እንድንቆም እና ከጥፋት እንድንድን በተደጋጋሚ ጊዜ ቢያስጠነቅቀንም ልንሰማው አልቻልንም።
በየጊዜው የተለያዩ እድሎችን ሰጥቶ የሰውን ልጅ ቢያየው ቢያየው ያው ሰው ታጥቦ ጭቃ ከመሆን አላለፈም ....ስለሆነም የገዛ ክንዱ መድኃኒትን አመጣለት ተብሎ እንደተፃፈው ፣ ከሀጢያተኛ ባህሪያችን የተነሳ ስለደከመ ለህግ ያልተቻለውን እግዚአብሔር አብ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስን በሀጢያተኛ ስጋ ምሳሌ አድርጎ ለሀጢአት መስዋዕት አደረገው !!!!
በክርስቶስ ስጋ በኩል በመስቀሉ አማካኝነት በሀጢያተኛ ባህሪያችን ላይ የሞት ፍርድን ተፈፃሚ በማድረግ ከአዳም ዘመን ጀምሮ ለዘመናት ታሰረንበት የነበረውን የግዞት ሰንሰለት በጣጥሶ ...የተጫነብንን ቀንበር ሰባብሮ ... በነፃነት እንድንኖር ከነበረብን የውርስ ሀጢያት ባርነት ነፃ አወጣን ....
አንድ ልጁን ለሞት ሰጥቶ ለእኛ የዘላለም ህይወትን ሰጠን ...... !!!!!!!

በዚህ አጋጣሚ ይሄን ጌታን ያልተቀበለችሁ ሰዎች ወደዚህ የፍቅር አምላክ ትመጡ ዘንድ ግብዣችን ነው።

ቅዱሳን ይሄንን መልዕክቴን ለሌሎች በመድረስ ወንጌልን አብረን እንስራ።

በእርሱ ሞት እኛ በህይወት እንድኖር ላደረገው ጌታ ክብር እና ምስጋና ይሁን አሜን !!!!!!

    🧔ወንድማችሁ ፍሬ ነኝ🧔
@abit9

🔹🔸🔹Join Us🔹🔸🔹
@superchristiantube7
@superchristiantube7
@superchristiantube7
sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ
ለአንድ ጓደኛችሁ ሼር አድርጉለት


ወደ ቼርች እየሄደን መጽሐፍ ቅዱስ መያዛ የግድ ያስፈልጋል
በsoftware አሌኝ የምትሉት ከለችሁ በጣም አዝናለሁ 🥹

የጴንጤነት ዋና መገለጫ hardware መጽሐፍ ቅዱስ መያዝ ነወ
በመጽሐፍ ቅዱስ የማያፍር ሰዉ በእጁ ይዞ በልቡ ላይ አስቀምጦ ይኖራል

🥰 @Akenaldo


Forward from: ማርከን ዜማ Marken Zema ✟ 🇪🇹
የቀኑ መልዕክት

መሪህ ልክ ነው!
የትኛውንም ርቀት ሂድ የሄድከውም መንገድ አስደሳች ይሁን እንዲሁም መንገዱ አሰልቺ አስጨናቂም ይሁን የሄድክበት ርቀት ሚለካው በአንተ የአካሄድ ጥበብ ሳይሆን የእግዚአብሔር ርህራሄ መጠን ነው።
እስራኤላውያን በሙሴ በኩል ከእግዚአብሔር ከመጣ ትእዛዝ የግብፃውያንን ብር ወርቅ ከሰበሰብ በኋላ ሁሉም ተሰብስበው ከግብፅ በመልአኩ ምሪት ቀይ ባህር ጋር ደረሱ ከኋላ ደግሞ ምርጥ ሚባሉ የግብፅ ሰረገሎች ተከተሏቸው። በእንደዚህ አይነት በማይመስል ሁኔታ ውስጥ የግብፅን ወርቅ የበዘበዙት እስራኤላውያን የባህሩን ግርማ አይተው ፈርተው እንኳን እንዳይመለሱ ግብፅን በመበዝበዛቸው ብቻ የመመለስ ሞራል እንኳን አልነበራቸውም ግን የመራቸው በዚያም ሁኔታ ውስጥ ልክ ነበር። ከዛም ድንቅ መልእክት ሙሴ ለህዝብ እንዲህ ሲል ነገራቸው “እግዚአብሔር (ያህዌ) ስለ እናንተ ይዋጋል፤ እናንተ ያለባችሁ መታገሥ ብቻ ነው።” ዘጸአት 14፥14 ሚመራህ ተዋጊ ነው........በሌላ በኩል ደግሞ እግዚአብሔር ስርአትን ሊያስተምርህ ምንም ወደ ማይኖርበት ወደ ምድረበዳ ይመራሀል። ብዙ ጊዜ ለልቤ ምነግራት "ምድረበዳ የእግዚአብሄርን የሀሳብ ማሳያ ናት" እያልኩ ነው ካስታወሳችሁ ሆሴዕ 2:14-15
“ስለዚህ እነሆ፤ አባብላታለሁ፤ ወደ ምድረ በዳም እወስዳታለሁ፤ በፍቅር ቃል አነጋግራታለሁ።በዚያም የወይን ተክሏን እመልስላታለሁ፤ የአኮርንም ሸለቆ የተስፋ በር እንዲሆናት አደርጋለሁ። በዚያም ከግብፅ እንደ ወጣችበት ቀን፣ እንደ ልጅነቷም ጊዜ ትዘምራለች።" አንዳንድ ምድረበዳዎች እግዚአብሔር ሚያወራባቸው ናቸው።የጣልናቸውን ነገሮች ማንሻ ናቸው። እናም እግዚአብሄር ምድረበዳ ወደሚመስል ሚወስዳችሁ የልብን ሊያወራችሁ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ትንሽ ነገሮች ሲሳኩልን እና ስንለወጥ በእግዚአብሔር ፊት ልባችን እንዳያብጥ ማስተንፈሻ ቀስት ናት እስራኤላውያን ነገር ሞልቶላቸው ከእግዜር ለመራቅ ሲሞክሩ እግዚአብሔር በሙሴ በኩል ሁሌ ሚናገራቸው ቃል አለ "በበረታች ክንድ ከግብፅ ያወጣኋቹ" እያለ የትላንታቸውን ጭንቅ እያስታወሰ የዛሬ ሙላት እንዳያጠፈቸው ያደርጋቸዋል። ስለዚህ መሪያችሁን ተከተሉት እርሱ ልክ ነው!
መልካም አዳር!
@Gift29
@Markengeta


ሰሞኑን ገጹ የተካፈተበት ዓላማ ይጀመራል ሰዎች ተቀላቀሉ 🙏

@የነፍስ መልህቅ

9 last posts shown.

167

subscribers
Channel statistics