“ደህና እደር ሳትዪኝ ለምን ተኛሽ?”
“ባልልህም ይኸው አድረህ የለ እንዴ ምንድነው ሰላም ሳያድር በተኛበት እንደቀረ ሰው የምትነተርከኝ...”
“እሺ አሁን ልሄድ ነው...”
“እና?”
"ቢያንስ ደህና ዋል በዪኛ”
“ወገኛ...”
“እ?”
“ደህና ዋል...”
ፈገግ ብሎ አይቷት...
“አንቺን ነበር ማግባት...”
“በጭቅጭቅ ልትደፋኝ...”
“በይ ደህና ዋዪ”
ሄደ...
አስፓልቱን በአይኖቿ አሻገረችው...
“አንተን ነበር ማግባት” አለች እሷጋ ብቻ በሚቀር ድምፅ...
ድንበር በሌለበት ለመድረስ ከፈለጉበት ራስን ማገድ፤ ከልካይ በሌለበት ከወደዱት ሁሉ መቆጠብ፤ ልባችን መልካሙን ያልለየ ብቻ ሳይሆን ያላየም ይመስል በሩቁ ሆኖ የተፈቀደውን መመኘት... ሚስኪንነት መልክ ሲኖረው ፍቅር የነፈግናት ነፍሳችንን ይመስላል።
~ ~ ~
✍🏾 በየአብስራ ፀጋ
YOUTUBE TIKTOK INSTAGRAM