ፎቶ ፦ የአልነጃሺ መስጂድ መልሶ የመጠገን ስራ በመከናወን ላይ እንደሆነ ተገልጿል።
ከትግራይ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በተገኘው መረጃ ፥ በትግራይ ጦርነት ከባድ ጉዳት ከደረሰባቸው ቅርሶች አንዱ የሆነው ቅዱሱ መስጂድ አልነጃሺን መልሶ የመጠገን እና የማልማት ስራ ከያዝነው ወር መጀመሪያ ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል።
ጥገናው የመስጂዱን ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ይዘት በጠበቀ መልኩ በመከናወን ላይ ነው ተብሏል።
በሚቀጥሉት 8 ወራት ጥገናው ተጠናቅቆ ክፍት እንደሚደረግ ተመላክቷል።
የትግራይ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የአልነጃሺ ቅዱስ መስጂድን መልሶ ለመጠገን ከቱርክ ልማት ኤጀንሲ (ቲካ) ጋር መፈራረሙ ቢሮው አስታውሷል።