Forward from: Dr. Eyob
ጥያቄ፡-
ሰላም ዶ/ር ለእድሉ እግዚአብሔር ይስጥልኝ እኔ ብዙ ጊዜ ነገሮች ሳይሳኩልኝ ሲቀሩ ወደ እደለቢስነት እቀይረዋለሁ በእርግጥም እድለቢስ የሚያስብል እድል አለኝ፡፡ ለኔ ሲሆን በህሩ ደርቆ አፈር ይሆናል ለኔ ሲሆን ምርኩዜ ይቀልጣል ግን የእውነት እድል አለ? እድለ ቢስነት አለ? ወይስ በተግባር ስሳት ስያሜ እየሰጠሁት ነው የእውነቴን ነው ምልህ ለኔ ሲሆን አይሳካም ሌሎች ያደረጉትን ባደርግ እንኳ በእኔ ግዜ አዲስ ህግ ይወጣል እስኪ ምን ትለኛለህ?
መልስ፡-
“ነገሮች ሳይሳኩልህ ሲቀሩ ትርጉሙን ወደ እድለ ቢስነት ለምትቀይረው”፡-
“እድል” የሚባለው ሃሳብ የብዙ መከራከሪያ ነጥብ ነው፡፡ ከሁለት ጽነፎች እንድትጠበቅ ልምከርህ፡፡ አንዳንድ ሰዎች “እድል የሚባል ነገር ፈጽሞ የለም” ይላሉ፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ “እድል የሚባል ነገር አለ፣ ምንም ብንለፋ እድለኞች ካልሆንን የትም አንደርስም” ይላሉ፡፡ ከእነዚህ ሁለት አመለካከት መካከል ላይ ሚዛናዊ አመለካከት አለ ብዬ አምናለሁ፡፡ “እድል” የሚባል ነገር አለ፣ ነገር ግን እድል የሚባለው ነገር ሲመጣ እድሉን የሚመጥን ዝግጁነት ከሌለ ግን የትም አንደርስም፡፡
ከዚህ በፊት ለአንድ ጥያቄ ስመልስ “የፖሰትኩትን” ላስታውስህ፡- አጋጣሚን የሚመጥን ዝግጁነት ያለመኖር ችግር፡- ይህ ብዙ ሰዎች “እድል” ብለው የሚጠሩት ጉዳይ ነው፡፡ አንድ አጋጣሚ ሲገኝ አንዳንዶች ዝግጁ ስለሆኑ ይዘውት ሲሮጡ ሌሊች ግን ያልፋቸዋል፡፡ የመጀመሪያዎቹን በልማድ እድለኞች፣ እነዚያኞቹን ደግሞ እድለ-ቢሶች እንላቸዋለን፡፡ አጋጣሚ ሲመጣ እንዳያመልጥህ ዝግጁ ሁን፡፡
አንተ ያለህበት አመለካከት አደገኛነቱ እዚህ ላይ ነው፡፡ አንድ ሰው እድለቢስ ነኝ ብሎ ካሰበ በሄደበት ቦታ ሁሉ የሚያየው ያልተሳካውን፣ ያልሆነውንና የተሰናከለውን ነው፡፡ እሱን ከማየቱ የተነሳ ሌላኛውን የሚጓጓ ነገር ለማየት የሚያበቃ ሁኔታ አይኖረውም፡፡
ለአንተ ሲሆን ባህሩ ከአንተ በፊት እኮ ለእኔ ሲሆን ደረቁ መሬት በውኃ ተሞላና ባህር ሆነብኝ ብሎ ራሱን እንደ እድለ ቢስ የቆጠረ ሰው እንደነበር አትጠራጠር፡፡ አሁን ደግሞ ባህሩ ደርቆ አፈር ሲሆን ያኛው ሰው እኔ ስፈልገው ያልመጣ ባህ አሁን መጣ ብሎ ሊያማርር ይችላል፡፡ በእነዚህ በሁለቱም ሁኔታዎች ውስጠ ግን ደረቅ መሬት ሲሆን ለደረቅ መሬት የተዘጋጀ እቅድ፣ ባህር ሲሆን ደግሞ በውኃ ላይ የሚሰራ ነገር እቅድ ይዞ የተዘጋጀ ሰው በሁለቱም ሁኔታ የሚሰራው አያጣም፡፡
ነገሮች አልሳኩ ብለውና ጠማማ ሆነው እንዳስቸገሩህ በሚገባ ተገንዝቤያለው፡፡ ብዙ አንባቢቼና እኔንም ጨምሮ ለሰዓታት ተሰልፈን የጠበቅነው ተራችን ሲደርስ ቢሮው ተዘግቷል የተባልንባቸውን ጊዜያት አንረሳውም፡፡ በመዘጋቱ ውስጥ ልናደርግ የምንችለውን ነገር አስበን ከሁኔተዘው ዘወር ከማለትና ሲከፈት ከመመለስ ውጪ ሌላ ምርጫ የለንም፡፡ እድለቢስ ነኝ ብልን ብንሄድ ግን ጉዳያችን ይቀራል እንጂ ምንም አናመጣም፡፡
ስለዚህ አይዞህ፣ በርታና ተዘጋጅ፣ አዎንታዊ ሁን፣ አንኳኳ፣ ሞክር፣ አትማረር . . . አንተና ዓላማህ መገናኘታችሁ አይቀርም፡፡
https://t.me/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623