የተዋሕዶ መፅሐፍት 📜


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


💠
እንኳን ደና መጡ
በቻናላችን ላይ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
መፅሐፍትን በPDF 📖 ያገኛሉ
💠
ለፊልም ➱ @Orthodox_film
ለበአላት ➱ @Orthodox_bealat
ለግጥም ➱ @Orthodox_poem
ለመዝሙር ➱ @Orthodox_mezemur
ለጥያቄዎች ➱ @Orthodox_question
.
💠 @EOTC_LIBRARY
💠 @EOTC_LIBRARY_BOT
.
ለአስተያየቶ
@Orthodox2_bot

Related channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Statistics
Posts filter








Forward from: Vamos fixed game
💒 ሕማማት 💒
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬


📚 ርዕስ ፦ ሕማማት
✍ ፀሐፊ ፦ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
📝 የገጽ ብዛት 528
📅 ዓ.ም ፦ 2010

👤 አዘጋጅ ➫
@eotc_book_by_pdf

🔓 Password ➫
@EOTC-books-by-PDF


⤵️ አቅራቢ ፦

💠 @EOTC_library
💠 @EOTC_library_bot




Forward from: ኦርቶዶክሳዊ ክብረ በአላት ❖
✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥

​​#ፆመ_ነነዌ

እንኳን ለፆመ ነነዌ በሰላም አደረሳቹ አደረሰን
አሜን (፫) 🙏

."አምናችሁም በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ::

📖ማቴ 21፥22

በአንድ ልብ ቀዋሚዎች በአንድ ቃል ተናጋሪዎች ሆነን ስለ ቤተ ክርስቲያን ስለ ሀገር ስለ ሰላም ስለ ፍቅር እንድንጸልይ እንጹም በልዑል እግዚአብሔር ስም ::

"እኛ ግን ለጸሎትና ቃሉን ለማገልገል እንተጋለን"

📖ሐዋ 6 ፥ 4

💠 { @EOTC_library }
💠 { @EOTC_library_bot }

✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
.




Forward from: ኦርቶዶክሳዊ ክብረ በአላት ❖
​​ጾመ ነነዌ

ጾመ ነነዌ ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዷ ስትኾን የምትጾመውም ለሦስት ቀናት ነው፡፡ ይህቺ ጾም የምትጀመርበት ዕለትም ልክ እንደ ዐቢይ ጾም ሰኞን አይለቅም፡፡ ጾሟ የምትጀመርበት ቀን ሲወርድ ወይም ወደ ኋላ ሲመጣ እስከ ጥር ፲፯ ቀን ድረስ ነው፡፡

ቀኑ ሲወጣ ወይም ወደ ፊት ሲገፋ ደግሞ እስከ የካቲት ፳፩ ቀን ይረዝማል፡፡ ጾመ ነነዌ በእነዚህ ፴፭ ቀናት ውስጥ ስትመላለስ (ከፍ እና ዝቅ ስትል) ትኖራለች፤ ከተጠቀሱት ዕለታት አትወርድም፤ አትወጣም፡፡ በዚህ ዓመትም የካቲት 15 ቀን ትጀመራለች፡፡

‹‹ጾመ ሰብአ ነነዌ፤ የነነዌ ሰዎች ጾም›› የሚለው የጽሑፋችን ርእስ እንደሚያስረዳው ይህቺን የሦስት ቀን ጾም የጾሟት በነነዌ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ከተማዋም (ነነዌ) በጤግሮስ ወንዝ ዳርቻ የምትገኝ ስትኾን መሥራቿም ናምሩድ ነው ዘፍ.፲፥፲፩-፲፪/ ፡፡ ጥንታዊቷ የነነዌ ከተማ ለአሦር መነሻ የኾነች፤ እጅግ ሰፊና ያማረች፤ የቅጥሯ ርዝመትም ፲፪ ኪሎ ሜትር የሚሸፈን ነበር፡፡ በከተማዋ ንጉሡ ሰናክሬም ብዙ ሕንጻዎችን ገንብቶባት ነበር /ዮናስ ፬፥፲፩/፡፡

በዚያ ዘመን የነበሩ የነነዌ ሰዎች ኀጢአታቸው በዝቶ እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው ሲል ቸርነትና ምሕረቱ የማያልቅበት እግዚአብሔር መክሮ፣ ዘክሮ እንዲመልሳቸውና ንስሐ እንዲገቡ ነቢዩ ዮናስን ወደ ነነዌ ሕዝብ ላከው /ሉቃ.፲፩፥፴/፡፡

ዮናስ የስሙ ትርጕም ‹ርግብ› ማለት ነው፡፡ በዳግማዊ ኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት የነበረ ነቢይ ነው፡፡ ይህ ነቢይ መኖሪያው በገሊላ በጋትሔፌር ድንበር ከተማ ነበረ፡፡ አባቱም አማቴ ይባላል፡፡ ኢዮርብዓም ሶርያውያንን አባሮ የእስራኤልን ድንበር እንዲመልስ ነቢዩ ዮናስ ትንቢትን ተናግሯል /፪ኛነገ.፲፬፥፳፭፤ ዮናስ ፩፥፩/፡፡

ነቢዩ ኤልያስ ያስነሣው የሰራጵታዋ መበለት ሕፃን ነቢዩ ዮናስ እንደ ኾነ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያስረዳል /፩ኛ ነገ.፲፯፥፲፱/፡፡ መድኀኒታችን ክርስቶስም የዮናስን ከዓሣ ኾድ መውጣት የራሱ ትንሣኤ ምሳሌ አድርጎ ነግሮናል /ማቴ.፲፪፥፲፱-፵፪፤ ሉቃ.፲፩፥፴-፴፪/፡፡

እግዚአብሔር ‹‹ሔደህ በነነዌ ላይ ስበክ›› ባለው ጊዜ ነቢዩ ዮናስ ‹‹አንተ  መሐሪ ነህ፤ ልትጠፉ ነው ብዬ ተናግሬ ብትምራቸው ሐሰተኛ ነቢይ እባላለሁ››  ብሎ ላለመታዘዝ እስራኤልን ለቆ በመርከብ ወደ ተርሴስ ሸሸ፡፡

እግዚአብሔርም ታላቅ ነፋስን አስነሥቶ መርከቧ በማዕበል እንድትመታ አደረገ፡፡ ከዮናስ ጋር በመርከቧ ተሳፍረው የነበሩ ነጋድያንም ያላቸውን ሀብት ወደ ባሕሩ መጣል ሲጀምሩ ነቢዩ ዮናስ ጥፋቱን ተገንዝቦ ‹‹ማዕበሉ በእኔ ምክንያት የመጣ ስለ ኾነ  ንብረታችሁን  ሳይኾን እኔን  ወደ ባሕር ጣሉኝ›› ብሎ ተማጸናቸው፡፡

እነርሱም ‹‹ስለዚህ ሰው ነፍስ እንዳንጠፋ፣ ንጹሕም ደም በእኛ ላይ እንዳይደረግብን አይኾንም›› አሉ፡፡

ወደ ባሕሩ ለመጣል ዕጣ በተጣጣሉ ጊዜም ዕጣው በዮናስ ላይ ስለ ወጣ ነጋድያኑ ዮናስን ወደ ባሕሩ ጣሉት፡፡ ወዲያውኑ ከእግዚአብሔር ዘንድ የታዘዘ ታላቅ ዓሣ አንበሪ ዮናስን በአፉ ተቀብሎ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት አሳድሮ ወደ ነነዌ አደረሰው፡፡

እግዚአብሔር የቅል ተክልን ምሳሌ በማድረግ ቅጠሉ በመድረቁ ዮናስ ባዘነ ጊዜ ‹‹አንተ ላልደከምክበት እና በአንድ ቀን በቅሎ ላደገ ቅል ስታዝን እነሆ በታላቂቱ ነነዌ ከተማ ያሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብና እንስሳቱ የእጄ ፍጥረቶች ስለ ኾኑ ያሳዝኑኛል›› በማለት ነቢዩ ዮናስም ውሸታም ላለመባል መኮብለሉ ስሕተት መኾኑን አስረድቶታል፡፡

ዮናስም ነነዌ መሬት ላይ መድረሱን ባወቀ ጊዜ ከእግዚአብሔር መሸሽ አለመቻሉን ተረዳ፤ የነነዌ ሰዎችንም ‹‹ንስሐ ግቡ›› እያለ መስበክ ጀመረ፡፡ የነነዌ ሰዎችም ንስሐ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር ይቅር ብሎ ከጥፋት አድኗቸዋል፡፡ ሐሰት እንዳይባልም እሳቱ እንደ ደመና ኾኖ ከላይ ታይቶአል፡፡

የታላላቁ ዛፍ ቅጠል እስኪጠወልግ ድረስ አድርቆ ለሕዝቡ አሳይቷቸዋል፡፡ ንስሐቸው በከንቱ እንዳልቀረ አስረድቷቸዋል /ትንቢተ ዮናስን በሙሉ ይመልከቱ/፡፡ ታኅሣሥ ፭ ቀን የሚነበበው የመጽሐፈ ስንክሳር ክፍል  ‹‹ወበልዐ አሐደ ኀምለ›› በማለት ንስሐ ያልገቡ አንድ አገር ያህል ሰዎች በእሳቱ እንደ ጠፉ ይነግረናል፡፡

ጾመ ነነዌ የሦስት ቀን ሱባኤ ናት፤ በሦስት ቀናት ጾምና ጸሎት ንስሐ የገቡ የነነዌ ሰዎች ከጥፋት እንደ ዳኑ ዅሉ፣ በብሉይ ኪዳን አስቴር ሦስት ቀን ጾማ፣ ጸልያ በእስራኤል ላይ የመጣውን መቅሠፍት እንዲመለስ አድርጋለች /አስ.፬፥፲፭-፲፮/፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከበዓል ስትመለስ ሕፃኑ ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ ላይ ጠፍቶአት ከሦስት ቀን ፍለጋ በኋላ በቤተ መቅደስ አግኝታዋለች /ሉቃ.፪፥፵፮/፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለሄሮድስ በሰጠው ምላሽ መልስ ሦስት ቀን የሱባኤ ፍጻሜ መኾኑን ገልጿል /ሉቃ.፲፫፥፴፪/፡፡

ጾመ ነነዌ የእግዚአብሔርን ቸርነትና መሐሪነት የምናስታውስበት ጾም ነው፡፡ ይኸውም እኛ ፍጡራኑ በበደልን ጊዜ ፈጽሞ ከማጥፋት ይልቅ ምክንያት ፈልጎ እንድንድን ያደርገናል፡፡ ዮናስ ለስብከት ፈቃደኛ ባይኾን እንኳን እግዚአብሔር በተለየ ጥበቡ እንዲሔድ አድርጎታል፡፡

በእርግጥ እግዚአብሔር ሌላ የሚልከው ነቢይ አጥቶም አይደለም፤ እርሱንም ጭምር ሊያስተምረው ስለ ፈለገ እንጂ፡፡ የነነዌ ሰዎች የተነሳሕያን ምሳሌ ናቸው፡፡ ይህም ማለት ሰው ጥፋቱን አምኖ ንስሐ ከገባ እግዚአብሔር ይቅር ማለቱን አይተውም፡፡ ለዚህም ነው ዮናስን  ‹‹አንተ  ላልደከምክበት  እና በአንድ  ቀን በቅሎ  ላደገ ቅል  ስታዝን እነሆ  በታላቂቱ  ነነዌ ከተማ  ያሉ ከአንድ  መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብና እንስሳቱ  የእጄ ፍጥረቶች ስለ ኾኑ  ያሳዝኑኛል›› ያለው፡፡

ቀደምት የቤተ ክርስቲያን አባቶቻችን ይህን እና ሌሎች አጽዋማትን እንድንጾም የወሰኑልን ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ሕጉ የተዘጋጀልን እንደ ነነዌ ሰዎች እኛም ጾመን፣ ጸልየን ከኀጢአታችን እንነጻ ዘንድ ነው፡፡ ዛሬ ዓለማችን በኀጢአት ማዕበል እየተናወጠች ባለችበት ወቅት እኛም እንደ ነነዌ ሰዎች ከበደላችን ብንመለስ እና ንስሐ ብንገባ ቸሩ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ይቅርታና ምሕረት የባሕርይ ገንዘቡ ስለ ኾነ ‹‹ወደ እኔ  ተመለሱ፤  እኔም ይቅር  እላችኋለሁ፤›› ይለናል፡፡

ስለኾነም በነቢዩ ዮናስ ላይ የተደረጉ ተአምራትንና ካለመታዘዝ የሚመጣ ቅጣት ቀላል አለመኾኑን በማስተዋል፣ ለነነዌ ሰዎች የወረደውን ምሕረት በመገንዘብ ለእግዚአብሔርም ኾነ ለሃይማኖት አባቶች እና ለወላጆቻችን መታዘዝ ይገባናል፡፡

ስንጾምም እግዚአብሔር አምላካችን መዓቱን በምሕረት፣ ቍጣውን በትዕግሥት መልሶ በኀጢአት ለጠፋው ዓለም ይቅርታውን ይልካል፡፡ በመጾማችን ራሳችን ከመዓትና ከመቅሠፍት ከመዳናችን ባሻገር በእኛ በደል ምክንያት አገራችን፣ ዕፀዋቱና እንስሳቱም ሳይቀር ከድርቅና ከቸነፈር ይተርፋሉና፡፡

✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞

✝የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አመታዊ እና ወርሃዊ✝
✝ ክብረ በዓላት እንዲሁም አፅዋማት ✝
✝ መገኛ ቻናል ✝

{{ @Orthodox_bealat }}

💠 @EOTC_library
💠 @EOTC_library_bot




Forward from: Vamos fixed game
💒 ሕማማት 💒
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬


📚 ርዕስ ፦ ሕማማት
✍ ፀሐፊ ፦ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
📝 የገጽ ብዛት 528
📅 ዓ.ም ፦ 2010

ከዚህ ቀደም የኤፍራጥስ ወንዝ
የተሠኘውን የዲያቆን ሔኖክ ሀይሌን
መፅሐፍ አቅርበን ነበር አሁን ደሞ

ሕማማት የተሠኘውን ድንቅ መፅሐፍ
በቻናላችን ላይ ልንለቅ ነው። ይለቀቅ
የምትሉ 👍 በመጫን ድጋፋችሁን አሳዩን።
አይለቀቅ ይቆይ የምትሉ 📚 ይህን ተጫኑ።

እናመሠግናለን 🙏


⤵️ አቅራቢ ፦

💠 @EOTC_library
💠 @EOTC_library_bot








Forward from: Vamos fixed game
💒 የኤፍራጥስ ወንዝ 💒
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬

📚 ርዕስ: የኤፍራጥስ ወንዝ
📝 ደራሲ: ዲያቆን ሔኖክ ሀይሌ
📅 ዓ.ም: 2013


⤵️ አቅራቢ ፦

💠 @EOTC_library
💠 @EOTC_library_bot




Forward from: የመፅሐፍ ፕሮሞሽን 3
አንዴ ብቻ ይንኩት አለማትን የፈጠረውን ጌታ በሕይወት ያመስግኑ ፣ ስትነኩት የሚወስዳችሁ ቦታ በጣም ይጠቅማቹሀል !
👇

.            ✦              ‍ ‍ ‍ ‍                  ,    

.             .   ゚     .                    .           .            

✦ ˚                     ゚     .               .      ‍ ‍ ‍ ‍ ‍ ‍ ‍ ‍ ‍ ,                * .                    .           ✦           ˚              *                      .  

.          ✦   .   ゚     .             .

      ,       .                                                              *         .           .             .                                                               ✦      ,         *          ,    ‍ ‍ ‍ ‍               .            .                                   ˚          ,                              .                 

         

             *          ✦                                .                  .        .        .                .     ✦      .            

 ˚                     ゚     .           ✦    .


🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴
🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴


Forward from: Vamos fixed game
ማልዶ ቤተ ክርስቲያን ተሳልሞ ወደ ሥራ የሚሄድ አንድ መንፈሳዊ ሰው በጉዞው ከሌላ መንገደኛ ሰው ጋር ይገናኛል። ጥቂት እንደ ተጨዋወቱ ይህ በመንገድ ያገኘው ሰው ከደረት ኪሱ የሲጋራ ፓኮ በማውጣት አንዱን መዝዞ እንዲወስድ ይጋብዘዋል። ያም መንፈሳዊ ሰው "አይ ይቅርብኝ" ሲል እምቢ አለው። ባለ ሲጋራውም "ኃጢአት ነው ብለህ ስላሰብህ ነው እምቢ ያልከኝ? ማጨስ እኮ ከአስጨናቂዋ ሕይወት ፋታ ለመውሰድና ራስን ዘና ለማድረግ ይረዳል። ግድ የለህም አንዱን ሞክር" እያለ ሊያግባባው ጣረ። በመጨረሻም መንፈሳዊው ሰው እንዲህ አለው "ግድ የለም ለእኔ ይቅርብኝ። ባይሆን አንተ ይጠቅመኛል ካልህ በቃ ሲጋራውን ከመለኮስህ በፊት አንድ "አባታችን ሆይ" ጸልይና ጀምር" አለው። በዚህ ጊዜ ያ መንገደኛ ደንግጦ እንዲህ ሲል መለሰ "ጸሎት ጸልዬማ እንዴት እንዲህ አደርጋለሁ?!"

በጸሎት ልትጀምር የማትችላቸው ማናቸውም ነገሮች ለአንተ መልካም አይደሉም። በልብህ ኃጢአት እንድታደርግ የሚገፉፉህ ክፉ ሐሳብ ሲመጣ "ይህን ጸልዬ ማድረግ እችላለሁ?" ብለህ ራስህን ጠይቅ። ከጸሎት ጋር የማይጣጣም ከመሰለህ እርሱ ኃጢአት ነውና ተወው። ጸልዮ የሚዘሙት፣ ጸልዮ የሚሰርቅ፣ ጸልዮ ባልንጀራውን የሚሳደብ፣ ጸልዮ በወንድሙ ላይ ክፉ የሚያደርግ ማን ነው?

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

⤵️ አቅራቢ ፦

💠 @EOTC_library
💠 @EOTC_library_bot




Forward from: Vamos fixed game
መዝሙረ ዳዊት.pdf
6.3Mb
📘 መዝሙረ ዳዊት PDF

📚 #በውስጡ የያዛቸው #የጸሎት አይነቶች

❖ የዳዊት መዝሙራት በጠቅላላው መቶ ሃምሳ እና የነቢያት ጸሎት በቤተክርስትያን በሰባቱ ዕለታት ተከፋፍለው ይጸለያሉ ፤ እነርሱም

✍የሰኞ ከመዝሙር 1 – 30 (ፍካሬ፥ አድኅነኒ ፥ አምላኪየ) ፤
✍የማክሰኞ ከመዝሙር 31 – 60 (ብፁዓን ፥ ከመያፈቅር ፥ ለምንት ይዜኃር ) ፤
✍የረቡዕ ከመዝሙር 61 – 80 (አኮኑ ፥ እግዚኦ ኩነኔከ)፤
✍የኀሙስ ከመዝሙር 81 -110 (እግዚአብሔር ቆመ ፥ ይኄይስ ፥ ስምዐኒ) ፤
✍የዐርብ ከመዝሙር 111 – 130 ( ብፁዕ ብእሲ ፥ ተፈሣሕኩ)፡
✍የቀዳሚት ከመዝሙር 131 – 150 (ተዘከሮ ፥ ቃልየ) እና
✍የእሑድ የነቢያት ጸሎት እና መኃልየ መኃልየ ዘሰሎሞን ናቸው።

───────────
⤵️ አቅራቢ ፦

💠 @EOTC_library
💠 @EOTC_library_bot
 ───────────



20 last posts shown.

885

subscribers
Channel statistics