𝗡𝗼 limits


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


ለአምላክ ያለህ ፍቅር የተመሠረተው በሴጣን ላይ ባለህ ፍርሃት ነው!

Related channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


Forward from: 📚ትንሽ እንወቅ📚
Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ማናባህ ነህ አንተ😳
እንዳታልፉት✌️


🫂እዉነተኛ  ጓደኛ በስኬትህ   
       ይደሰታል እንጂ  አይቀናም 
            ያራዳ  ልጅ🤝


ፍራቻ ራሱ የሚፈራቸው ሰዎች እሉ!


አንበሳ ምንም ቢራብ፣ሳር አይበላም !

(እንደ አንበሳ ሁን ለጊዜያዊ ችግር ብለህ ደረጃክን ዝቅ አታርግ)


ለመዳን እንጂ ከባዱ ለመታመም ከበቂ በላይ ምክንያቶች አሉን።


Forward from: 📚ትንሽ እንወቅ📚
በጨረቃ መሐል ሆኜ
ለፀዳልሽ ቆቤን ደፋው
ከብርሃና ሸማ አንስቼ
በመጠንሽ ቀሚስ ሰፋው
የወዟን ወንዝ ጨልፌባት
ግሩም ጠላ ጠምቂያለው
የማርያምን መቀነቷን
መንገድሽ ላይ አንጥፍያለው

ብቻ አንቺ ነይ


ሁሉን ነገር አዋቅሬ
በኮከብ ቤት ወርቅ አንጥሬ
ለመርገጫሽ ጉዝጓዝ ይዤ
መግቢያሽ ቦታ ጉም ወጥሬ
ፅዋ ቀዳው ከሰማዩ
አሰናዳው ድግስ ቤቴን
መቼም ውዴ ትመጫለሽ
ልትመስጫት አንደበቴን

ብቻ እሺ በይ

ብቻ አንቺ ነይ
መተሽ እይኝ ከድግሴ ተሳተፊ
ጠብቃለው መምጣሽን
ጎራ ሳትይ እንዳታልፊ

ይሄ ሁሉ አውደ ጥበብ
ይሄ ሁሉ ውቅረ ኹነት
ላንቺኮነው ለመምጣሽ
የሸመንኩት አውደ ነገስት


ይሄ ሁሉ ቃል ስደራ
የሌለ አለም ላንቺ ማኖር
ይሁንልሽ መገለጫሽ
አይመጥንሽ ምድር መኖር

ስለዚ
ግብዣዬን ከተቀበልሽ
ከተራመድሽ ወደኔ አለም
የጨረቃን ሸማ ቀሚስ
ልታደምቂው ሆነሽ ቀለም
ውል ልቶኚኝ ውል ልሆንሽ
አምነሽ መምጣት ብትጀምሪ
ፍቃዴ ነው በኔ አለም
ከኔ ውለሽ እንድታድሪ

ጠብቅሻለው እንዳትቀሪ


Forward from: 📚ትንሽ እንወቅ📚
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
❤️❤️ፍቀር ግን ምንድነው? ❤️❤️
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
                         |
          ❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥
          ❤️‍🔥ፍቅር መሸነፍ ነው??❤️‍🔥
          ❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥

"አዎ መሸነፍ ነው። ፍቅር መሸነፍ ነው። ፍቅር መያዝ ነው። ፍቅር ለስሜት ተገዢ መሆን ማለት ነው። 
ፍቅር ከምክንያት ውጪ ሆኖ መኖርን መቀበል ነው ፍቅር ከራስ ቁጥጥር ዉጪ መሆን ነው።
                 ስለዚ አዎ መሸነፍ ነው፤"

😍😍😍ፍቅር ያስፈራል???😍😍😍

"ፍቅር ያስፈራል።ፍቅር ፤የማይታከሙት ህመም ፤ የማይጠገን ቁስል ፤ የማያባራ እንባና ሰቆቃ ሊሆን ይችላል።
የሚያስፈራው ያፈቀራቹት ሰው ሳይሆን ፣ ማፍቀር እራሱ ነው።
             :-ካፈቀራቹ ቡሃላ😍 አኔ🧍🏼‍♂የምትሉት ሁሉ ይቀርና፣ ለራሳቹ ትርፍ ትሆናላቹ። በፍቃደኝነት ከራሳቹ የምታስቀድሙትና የምታስበልጡት ሌላ ሰው ይኖራል ማለት ነው።
             :-ፍቅር ያለውግያ መማረክ ነው ፤ እጅ መስጠት፤ወዶ መግባት፤ከራስ መነጠል፤መጥፋት፤በሌላ ሰው አለም ውስጥ ገብቶ መሰደድ አያስፈራም አትበሉ😔 ያስፈራል😣😣።
ወንድ👱🏻 ወይም ሴት👱🏻‍♀ ስለሆንን ግን አይደለም ፦ፍቅር የሚያስፈራው 👱🏻‍♀ሰው👱🏻 ስለሆንን ነው።
       ።፦ማናችንም ብኖን የህይወታችንን መንገድ መቆጣጠር ባንችል እንኳን ማቀድ እና መምራት እንፈልጋለን። አንድ ሰው ወደዳቹ ማለት ይህን ሁሉ መተው ማለት ነው።
                           ፧
                           ፧
ፍቅር 🥰 ሲይዘን ፨ምን እንደሚሆን፣
                           ፨ምን እንደሚመጣ
                           ፨ምን እንደሚፈጠር
አናቅም፤ ምክንያቱም ፍቅር ከኛ ቁጥጥር ውጪ ስለሆነ።
             አለማወቅ ደሞ ያስፈራል......."


📖📖ከመፅሐፍት መንደር📖📖
             


"አንድ ቀን ወደኋላ ተመልክቼ 'አደረኩት እላለሁ'"

ተስፋ ካልቆረጥክ እዉነቴን ነዉ ይህ ቀን እሩቅ አይደለም!




የፈራነው እና የጠላነው ደርሶብናል እንደምንም አለን እንጂ።




አንዳንዴ የ ትግስትህ ብዛት ልካቸውን እንዳያቁ ያደርጋቸዋል።


Forward from: 📚ትንሽ እንወቅ📚
በአልጎሪዝም ህግ

     2+2 = 4

በካፒታሊዝም ህግ

2 + 2 = ?
:- ፈላጊ ካለ ውጤቱ ይጨምራል
ፈላጊ ከሌለ ውጤቱ ይቀንሳል

በአልጎሪዝም ህግ አውነት ይነግሳል
በካፒታሊዝም ህግ ጥቅም ይነግሳል


ዜማሽ እንዴት አማረ ቢሏት ስለተደበደብኩ አለች።

       #ከበሮ


አንዳንድ ሰው በጣም በማህበረሰብ ሕግ በመታሰሩ የተነሳ እስኪስት ሰክሮ እንኳን ይሉኝታ ይይዘዋል።


ሰዎች ከኋላቹሁ የሚያወሩ ከሆነ፣
ከፊት ለፊታቸው እናንተ፣ በመሆናችሁ ደስ ይበላችሁ ።


ከሁሉም ተማር
ማንንም አትከተል።


መኖር ይቀጥላል ✌️


፡
‎አለኝ ያልኩት ጭላጭ ተስፋ
‎                 አይዞህ ብሎ ያፅናናኛል
‎ይለፍ ያልኩት ይህ ጊዜ አልፎ
‎                    ነገን ማየት ያጓጓኛል
‎
‎የናፈቀኝ ቀና መንገድ
‎                  ሌላ መልኬን ሌላ ገፄን
‎የነበረኝ ያን ፈገግታ
‎                     የልጅነት ያፍላ ሳቄን
‎
‎ጊዜ ደርሶ ያጎደለውን
‎                      ቀን መልሶ እስኪክሰው
‎ያጓጓኛል ነገን ማየት
‎                 እንዳሰብኩት አድርጎኝ ሰው
፡


ሲጀመር ዩናይትድ ይችላል 🤬

20 last posts shown.

243

subscribers
Channel statistics