፡
አለኝ ያልኩት ጭላጭ ተስፋ
አይዞህ ብሎ ያፅናናኛል
ይለፍ ያልኩት ይህ ጊዜ አልፎ
ነገን ማየት ያጓጓኛል
የናፈቀኝ ቀና መንገድ
ሌላ መልኬን ሌላ ገፄን
የነበረኝ ያን ፈገግታ
የልጅነት ያፍላ ሳቄን
ጊዜ ደርሶ ያጎደለውን
ቀን መልሶ እስኪክሰው
ያጓጓኛል ነገን ማየት
እንዳሰብኩት አድርጎኝ ሰው
፡
አለኝ ያልኩት ጭላጭ ተስፋ
አይዞህ ብሎ ያፅናናኛል
ይለፍ ያልኩት ይህ ጊዜ አልፎ
ነገን ማየት ያጓጓኛል
የናፈቀኝ ቀና መንገድ
ሌላ መልኬን ሌላ ገፄን
የነበረኝ ያን ፈገግታ
የልጅነት ያፍላ ሳቄን
ጊዜ ደርሶ ያጎደለውን
ቀን መልሶ እስኪክሰው
ያጓጓኛል ነገን ማየት
እንዳሰብኩት አድርጎኝ ሰው
፡