#ሆናለች_ሞልቃቃ
:
:
አንድቀን በማታ ከፍቅሬ ጋር ሆኜ
ሽቅብ ሽቅቡን ሳይ በአሳብ መንኜ
አንድ እውነት ተረዳሁ በልቤም ገነነ
ቀን በመሽ ጊዜ የሰማይ ውበቱ ኮከብ እንደሆነ።
:
:
ልክይሄ እንደገባኝ ወዲያው በሹክሹክታ
ለምወዳት ፍቅሬ እንዲ ብዬ አልኳታ።
:
:
ያለከዋክብት እንደማይደምቅ ሰማይ
እኔም ደንጋዛ ነኝ ካንቺ ውጪ ስታይ።
አንቺው ነሽ ኮከቤ ለህይወቴ ድምቀት
ሰማዩ እኔነቴን እንዳይወርሰው ፅልመት።
:
:
ይህንካልኳት ወዲ...
የሚገርመውነገር ኮከቤ
ያልኳትን ቃል በአምሮዋ ታጥቃ
ያለሷ እንደማልደምቅ
በተጠንቀቅ አውቃ
ከዛን ቀን ጀምሮ ሆናለች ሞልቃቃ።
✍አቡኪ
@halaleee
@halaleee
👆👆👆👆👆👆
SHARE & JOIN
:
:
አንድቀን በማታ ከፍቅሬ ጋር ሆኜ
ሽቅብ ሽቅቡን ሳይ በአሳብ መንኜ
አንድ እውነት ተረዳሁ በልቤም ገነነ
ቀን በመሽ ጊዜ የሰማይ ውበቱ ኮከብ እንደሆነ።
:
:
ልክይሄ እንደገባኝ ወዲያው በሹክሹክታ
ለምወዳት ፍቅሬ እንዲ ብዬ አልኳታ።
:
:
ያለከዋክብት እንደማይደምቅ ሰማይ
እኔም ደንጋዛ ነኝ ካንቺ ውጪ ስታይ።
አንቺው ነሽ ኮከቤ ለህይወቴ ድምቀት
ሰማዩ እኔነቴን እንዳይወርሰው ፅልመት።
:
:
ይህንካልኳት ወዲ...
የሚገርመውነገር ኮከቤ
ያልኳትን ቃል በአምሮዋ ታጥቃ
ያለሷ እንደማልደምቅ
በተጠንቀቅ አውቃ
ከዛን ቀን ጀምሮ ሆናለች ሞልቃቃ።
✍አቡኪ
@halaleee
@halaleee
👆👆👆👆👆👆
SHARE & JOIN