የኢትዮጵያ ነገሥታት
የኢትዮጵያ ነገሥታት ለብዙ ዘመናት ኢትዮጵያን ሲያስተዳድሩ ቆይተዋል።
በመጀመሪያ ከሰብታህ ጀምሮ እስከ ጲኦሪ አንደኛ ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ፳፭፻፵፭ እስከ ፲፱፻፹፭ ዓመት ከነገደ ካም በኢትዮጵያ የነገሡ ነገሥታት ፳፪ ናቸው፤ ዘመኑም ፭፻፷ ይሆናል።
ከክርስቶስ ልደት በፊት ነገደ ዮቅጣን መንገሥ ከጀመሩበት ፲፱፻፹፭ ዓመት ጀምሮ ቀዳማዊ ምኒልክ እስከ ነገሡበት እስከ ፱፻፹፪ ዓመት አግዓዝያን ከተባሉ ከነገደ ዮቅጣን በኢትዮጵያ የነገሡ ነገሥታት ፶፪ ናቸው። ዘመኑም ፩ ሺህ ፫ ዓመት ይሆናል።
ከክርስቶስ ልደት በፊት ቀዳማዊ ምኒልክ ከነገሡበት ከ፱፻፹፪ ዓመት ጀምሮ ክርስቶስ እስከ ተወለደበት እስከ ፩ ዓመተ ምሕረት እስከ ባዚን በኢትዮጵያ የነገሡ ነገሥታት ፷፯ ናቸው። ዘመኑም ፱፻፹፪ ይሆናል። ነገር ግን ባዚን ከክርስቶስም ልደት በኋላ ፱ ዓመት ነግስዋልና ይህ ሲጨመር ፱፻፺፩ ይሆናል።
ከባዚን ጀምሮ የቀዳማዊ ምኒልክ መንግሥት ወደ ነገደ ዛጔ እስከ ፈለሰበት እስከ ድልነዓድ ድረስ ከ፩ እስከ ፱፻፲፪ ዓመተ ምሕረት በኢትዮጵያ የነገሡ ነገሥታት ፺፬ ናቸው። ነገር ግን ባዚን ሁለት ጊዜ ያልተቆጠረ እንደ ሆነ ፺፫ ይሆናል። ዘመኑም ፱፻፲፪ (፱፻፳) ዓመት ይሆናል። ክርስትና በኢትዮጵያ የገባው በነዚሁ ዓመታት ውስጥ ከ፪፻፺፰ እስከ ፫፻፳፬ ዓ.ም. በአብርሃና አጽብሓ ዘመን ነው።
ከድልነዓድ በኋላ ከመራ ተክለ ሃይማኖት (ስመ መንግሥታቸው ዛጔ) ጀምሮ እስከ ይትባረክ በኢትዮጵያ ነገሡ የዛጔ ወገኖች ፲፩ ነገሥታት ናቸው። ዘመኑም ፫፻፴፫ ዓመት ይሆናል።
የኢትዮጵያ መንግሥት በኃይል ወደ ዛጔ ዘር ካለፈ በኋላ በ፫፻፴፫ ዓመት እንደ ገና ወደ ቀዳማዊው ምኒልክ ዘር ወደ ይኩኖ አምላክ ከተመለሰበት ከ፲፪፻፵፭ (፲፪፻፶፫) ዓ.ም. ጀምሮ የጎንደር መንግሥት እስከሚባለው ሠርፀ ድንግል እስከ ነገሡበት እስከ ፲፭፻፶፫ ዓ.ም. በኢትዮጵያ የነገሡ ነገሥታት ፳፮ ናቸው፤ ዘመኑም ፫፻፩ ዓመት ይሆናል።
ሠርፀ ድንግል ከነገሠበት ከ፲፭፻፶፫ እስከ ፲፯፻፸፯ ዓ.ም.
የጎንደር መንግሥት መጨረሻ እስከ ተክለ ጊዮርጊስ፤ በጎንደር ቤተ መንግሥት ሆነው ኢትዮጵያን የገዙ ነገሥታት ፲፰ ናቸው። ዘመኑም ፪፻፹፬ ዓመት ይሆናል።
የጎንደር መንግሥት የሚባለው ከተጨረሰበት ከ፲፯፻፸፯ ዓ.ም. ጀምሮ ዓፄ ቴዎድሮስ እስከ ነገሡበት እስከ ፲፰፻፵፭ የገዙ መሳፍንት ፲፱ ናቸው። በነዚህም መሳፍንት ዘመን ሙሉ ሥልጣን ሳያገኙ ለስሙ ብቻ ዘውድ እየጫኑ በጎንደር ቤተ መንግሥት ይቀመጡ የነበሩ ትውልዳቸው ከቀዳማዊ ምኒልክ ወገን የሆኑ ነገሥታት ፲፬ ናቸው።
ዘመነ መሳፍንት ካለፈ በኋላ ከ፲፰፻፵፭ እስከ ፲፰፻፹፩ በኃይልና በጉልበት የነገሡ የኢትዮጵያ ነገሥታት ፫ ናቸው። ዘመኑም ፴፮ ዓመት ይሆናል።
የሸዋ መንግሥት ባላባቶች ፲፭ ናቸው። የግዛታቸውም ዘመን ፪፻፸ ዓመት ይሆናል።