እንግዲህ እውነተኛ ታሪክ ነው የሰፈራችን አዛውንት ናቸው ያጫወቱኝ
ድካም ስለተጫናቸው ተደግፈውኝ ወደ በር ወጥተው ቆሙና አንድ ሱቅ አይተው ለስለስ ያለ ፈገግታ ፈገግ አሉ ባይገባኝም አብሬያቸው ፈገግ አልኩ እውነት ለመናገር እርጅናቸው ብዙ አያስታውቅም ጠየም ቢሉም ከዛ አልፎ የሚታይ ውበት አላቸው እግራቸው ላይ ባለው ቁስል ምክንያት እንጂ እንደ ጥንካሬያቸው እንኳን በ86 በ96 አመታቸው ራሱ የሚያረጁ አይመስሉም የሚያናግራቸው ሰው ስለሚናፍቁ አልያም ስሜቱ ስላልወጣላቸው አላቅም ብቻ ለመጣ ለሄደው ነው ታሪካቸውን የሚናገሩት "የዛሬን አያርገውና" የሚል የቁጭት ቃላቸውን አስከትለው ትረካቸውን ጀመሩ
"ያውልሽ ልጄ የዛሬን አያርገውና እንዴት ያለው ጥጋበኛ ነበርኩ መሰለሽ አይ ጊዜ ደጉ አይ ጊዜ ክፉው ስንቱን አሳየኝ ብቻልሽ ጥጋቤ የበረደበትንና የመላጣነቴን ታሪክ ልንገርሽ" አነጋገራቸው ፈገግ ሲያስብለኝ አብረውኝ ፈግገው ንግግራቸውን ቀጠሉ
"እንደው ሀረር ውስጥ የማላወጣት ሴት አልነበረችም ደሞ የባጃጅ ሹፌር ነበርኩ አንድ ጓደኛዬ እንደኔ ነው እሱም አንዷ ቺክ እንቢ ትለዋለች ብትደረግ ብትሰራ ወንድ አንድ ቀን ነክቷት አያቅም አልቻለም ስለሷ እያወራን ይዣት ከወጣው 20 ብር እንደሚሰጡኝ ተስማማን ብሩን ተቀብዬ የምትሰራበትን ስጠይቅ ቀበሌ 11 ነው አሉኝ ቀጥ ብዬ ወደሷ ቀለል ያለች ናት አቤት ብታይ ውበቷ አጃኢብ ነው ቀስ ብዬ ተግባባዋት እንደ ፉከራዬ ይዣት ወጣሁ ችግሩ ግን ከወዲያ ነበረ አፍቅሬያት እርፍ አልኳ ከዛ አገባዋት" ትንፋሽ ሲሰበስቡ እኔ ቀደም ብዬ "ደስ ይላል የምር አባባ ግን እግሮትን ምን ሆነው ነው"
"ወግጅ እስኪ አስጨርሽኝ ዳሩ ግን ማተራመሴን ስታውቅ ቅናት ጀመራት ኧረ በሞትኩት እኔማ ራሴን ፈራሁ አንድ ነገር አይቀራት ውሎዬን ስትተርክ በቃ ለምን ሴት ከጎንህ ተቀመጠች ስትል እሱን ትቼ ውትድርና ለመግባት እያሰብኩ ባለሁለት ላማክራት ስገባ እሷ ሆዬ እሳት ለብሳ እሳት ጎርሳ ጠበቀችኝ አይ ጉድ ለማረጋጋት ላቅፋት ስጠጋ እንደው የጣደችውን አንስታ አናቴ ላይ ስታራግፈው ፀጥ ያልኩ መሰለኝ እኔም ብን ብዬ ወታደር ሆንኩ አናቴም ተቃጠለ ፀጉር ደግሞ ላያበቅል እግሬንም እዛው ወታደር ሆኜ ነው የተመታሁት እንደው ስወዳትኮ ብታይ አሁንስ መች ፍቅሯ ወጣልኝ አላስቀርብ አለችኝ እንጂ አይ ቅናቷ ባትኖር እንዴት ያለች ዘመናይ ዝምንምን መሰለችሽ"
"ብርድ እየመጣ ነው እንግባ አባባ"
"በይ እሺ ልጄ ደግፊኝ..."
share ማድረግ አይረሳ
👉 @loves2512